Get Mystery Box with random crypto!

ለ156 ሰዎች የሙት አመት የሚዘክሩት እናት ! እማማ ሙሉነሽ በደብረዘይት የተከሰከሰዉ #አዉሮፕላ | ETHIO-MEREJA®

ለ156 ሰዎች የሙት አመት የሚዘክሩት እናት !

እማማ ሙሉነሽ በደብረዘይት የተከሰከሰዉ #አዉሮፕላን ከተከሰተ ከሰባተኛዉ ቀን ጀምረዉ እስካሁን ድረስ አይተዋቸዉ በአካል አግኝተዋቸዉ እንኳን የማያዉቋቸዉን የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸዉን በተከሰከሰው አዉሮፕላን ህይወታቸዉን ላጡ 156 ሰዎች የሙት አመት ፍትሃት እያስፈቱ የሚገኙ አስገራሚ ባለ ቃልኪዳን እናት ናቸዉ !!

እማማ ሙሉነሽ ከአዲስአበባ ወደ ናይሮቢ በበረራ ላይ የነበረው max 8 -737 አዉሮፕላን ደብረዘይት ላይ ተከስክሶ 156 ሰዎች ህይወት ሲቀጥፍ እማማ ሙሉነሽ ግብር ለመክፈል በእግራቸው ሲጓዙ አዉሮፕላኑ እየጨሰ ቁልቁል ተምዘግዝጎ ሲወድቅ በደመነብስ እየሮጡ በጭሱ መሃል ገብተዉ የተረፈ ካለ ብለዉ ፈለጉ አላገኙም፣ በየቦታው የወደቀዉን የሰዉ አካላት በነጠላቸዉ በሻሻቸዉ ለመሸፈን ሞከሩ፣ አነቡ፣ አዘኑ፣ አለቀሱ።

እኒህ እናት ከዛን ጊዜ ጀምረዉ የሟቾቹን ሰባት፣ አስራሁለት፣ አርባ፣ ሙት አመት እየዘከሩ ፍታት እያስፈቱ ፀሎት እያስደረጉ አመታት ዘልቀዋል።እማማ ሲጠየቁ በህይወት እስካሉ ድረስ ይህንን አላቆምም፣ በየአመቱ ሙት አመታቸዉን እዘክራለሁ ብለዋል።

እማማ በዚህ በዘር በጎሳ በመንደር በምናስብበት ዘመን ሰዉ መሆንን ያሳዩ እናታችም እረጅም እድሜ ተመኘን በመኖርያ ቤታቸዉ በመሄድ ያከበራችኋቸዉ ጋዜጠኞች ምስጋና ይገባችኋል።
T.me/ethio_mereja
@ethio_mereja