Get Mystery Box with random crypto!

በሽብርተኛው ሸኔ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመልካ ጉባ ድልድይ ተገንብቶ ተጠናቀቀ በሽብርተኛው የ | ETHIO-MEREJA®

በሽብርተኛው ሸኔ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመልካ ጉባ ድልድይ ተገንብቶ ተጠናቀቀ

በሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ ኃይል ጉዳት ደርሶበት የነበረው የመልካ ጉባ ድልድይ መገንባት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በቦታው የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ተናገረዋል። ሰራዊቱ በዳዋ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመፈፀም የነበረውን ተግዳሮት መፍታት ተችሏል።

በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል ብርሃነ ልጃለም እንዳሉት ከዚህ ቀደም የሸኔን ታጣቂ ሃይል ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ የዳዋ ወንዝ ለተልዕኮ ችግር እንደነበር ጠቁመው የድልድዮ ዳግም መገንባት በሁሉም ቀጠናዎች ተንቀሳቅሶ ለድል የሚበቃ ሰራዊት የመገንባት አንድ አካል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል። በዕዙ የሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ገበረ ጋሞ በበኩላቸው ግንባታው የሰራዊቱን ድካም በመቀነስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተልዕኮን በብቃት የመወጣት ስራ የሚያቀላጥፍ ከመሆኑ ባሻገር የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ህዝቦችን ትስስር የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነ ተናግረዋል።

ለአመታት አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን እንደምሽግ በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናውን የቆየውን የሸኔ ቡድን ለመደምሰስ ቅንጅታዊ ስራ ተግባራዊ መደረጉ ለተገኘው ድል ወሳኝ ሚና እንዳለው የገለፁት፣ በኦሮሚያ ልዩ ሃይል የሬጅመንት አዛዥ ኢንስፔክተር ጅብሪል አደም በዘመቻው ወቅት ፈተና የነበረው የዳዋ ወንዝ ሙላት አሁን ላይ በተረጋገጠው ሰላም የድልድይ ግንባታ ተሰርቶለት መላው የፀጥታ ሃይል ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መደረጉን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተገነባው የብረት ድልድይ የሶማሌ ክልል ዳዋ ዞንን እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጅና ቦረና ዞኖችን የሚያዋስን መሆኑን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
@ethio_mereja