Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናመረጃ የእንቁላል 7 አስገራሚ የጤና በረከቶች! እንቁላል በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን | ETHIO-MEREJA®

#ጤናመረጃ

የእንቁላል 7 አስገራሚ የጤና በረከቶች!

እንቁላል በርካታ የጤና ጥቅሞች ያሉት ሲሆን የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

1. ለአእምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው!
እንቁላል ክሎሪንን ለአእምሮ በመመገብ ጤንነቱን ይጠብቃል፡፡ ክሎሪን መልዕክት አስተላላፊ በመሆን ያገለግላል፡፡ አስኳል ውስጥ የሚገኝው ፎሌት ንጥረ ነገር የነርቭ ሴሎችን በመጠበቅ አእምሮ ተግባሩን በትክክል እንዲወጣ ያደርገዋል፡፡

2. ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል!
እንቁላል የሰውነታችንን በሽታ የመከላከል አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በሳምንት ቢያንስ 6እንቁላል መመገብ በጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላችንን በ44% ይቀንሳል፡፡

3. ለአይን ጤንነት ይጠቅማል!
2 ካሮቲኖይድ፣ ሉቲይንና ዜክሳንቲን የጠራ እይታ እንዲኖረን እና አይናችን ጤናማ እንዲሆን ይረዱናል፡፡ እንቁላል ተመጋቢ ከሆኑ ከካታራክትና ከፀሃይ ጐጂ ጨረር ከመጋለጥ ይከላከልልዎታል፡፡

4. የፀጉር እና ጥፍር ጤንነትን ለመጠበቅ!
በሰልፈር የበለፀገ አሚኖ አሲድ በእንቁላል ውስጥ ይገኛል፡፡ የጥፍር ጤንነትና ጥራትን ይጨምራል፡፡ ሌሎች እንደ ብረት፣ ዚንክና ሴሊኒየም ለፀጉር ጤንነት የበኩላቸውን ድርሻ ይወጣሉ፡፡

5. የሰውነት ክብደትን ያመጣጥናል!
በፕሮቲን የበለፀገ ስለሆነ የሰውነት ክብደትን ለመጨመር ተመራጭ ነው፡፡እንቁላል ስንጠቀም ከመጠን በላይ እንዳንመገብ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

6. አጥንታችን ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል!
እንቁላል ከፍተኛ የቫይታሚን ዲ፣ ፎስፈረስና ካልሲየም መጠን አለው እነዚህ በአንድነት በመሆን የአጥንት ችግርን ይከላከላል፡፡

7. ከድንገተኛ የልብ ህመም፣ የደም መርጋትና ድንገተኛ ከሆነ የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ይከላከላል፡፡

ጠቃሚ ነውና ለወዳጆ ያካፍሉ! ሼር!
T.me/ethio_mereja