Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-11-11 17:20:34
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የደንበኞቹን ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገለፀ!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በነሐሴ ወር ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ900 ሺህ በላይ ደንበኞችን በኢትዮጵያ ማፍራት እንደቻለ አስታወቀ።

የሳፋሪኮም ኩባንያ ዛሬ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በናይሮቢ በቀረበበት መድረክ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ “በኬንያ እና በኢትዮጵያ እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆል እና ፈጣን ያልሆነ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት የመሳሰሉ ከማክሮ ኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ተግዳርቶች አጋጥመውናል” ብለዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ከአዲስ ዘይቤ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመድረኩ እንደተናገሩት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከ933 ሺህ ደንበኛ ማፍራት ተችሏል ብለዋል። “ቁጥሩ በየጊዜው የሚቀያየር ነው፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከ900 ሺህ የተሻገርን ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ሚልየን ደንበኞች እንደርሳለን” ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት አንዋር ሶሳ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከጦርነቱ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመድረስ እቅድ አለን ብለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
783 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 17:20:34
Breaking : 70% የትግራይ ክልል በመከላክያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ሆኗል።

በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ ነው አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

በትግራይ ክልል አገልግሎቶች ዳግም እየጀመሩ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ እና የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።

በክልሉ 70 በመቶ በሚሆኑ አካባቢዎች ዕርዳታው ከመቼውም ጊዜ በላይ እየደረሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ዕርዳታውን በሌሎች ቀሪ አካባቢዎችም ለማዳረስ በ35 ተሽከርካሪዎች ምግብ እና በ3 ተሽከርካሪዎች መድኃኒት ተጭኖ ሽሬ ገብቷል ብለዋል።

ወደ ክልሉ በረራ መፈቀዱን የገለጹት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የሰብአዊ ዕርዳታን በተመለከተ ምንም ዓይነት መሰናክል አይፈጠርም ብለዋል።

አንዳንድ አካላት የአፍሪካውያን ዕውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት ደስተኛ እንዳልሆኑ ጠቁመው፣ ይህንን መልካም መንፈስ ለማወክ ሲጥሩ ይታያሉ ሲሉም ገልጸዋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
767 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 17:20:34
የቻይና “J-20” ስውር ተዋጊ ጄቶችን ምን የተለየ ያደርጋቸዋል?

የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ መካሄድ ላይ ሲሆን፤ “J-20” ስውር ተዋጊ ጄት ለእይታ ቀርቧል።

ለቻይና ኤር ሾው ላይ የቻይና አየር ሃይል ተዋጊዎች እና "የአየር ኤሮባቲክስ" ቡድን በዙሃይ ታላቅ የአየር ትርኢት ቢያቀርቡም አራት ጄ-20 ስውር ተዋጊዎች የተመልካችን አይን ስበዋ ነው የተባለው።

በሰዓት እስከ 2 ሺህ 100 ኪሎ ሜትር ድረስ መብረር ይችላል የተባለለት “J-20” ተዋጊ ጄት፤ 19 ሺህ 390 ኪሎ ግራም ክብደት አለው ተብሏል።

Via Al ain
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
842 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 20:09:24
እስራአል ዳንሳ በጥይት ተመታ

ሐዋርያው እስራአል ዳንሳ ከአዲስ አበባ 590 ኪሜ የምትገኘው በኦሮሚያ ክልል የምትገኘው ነጌሌ ቦረና ኮንፍረስ አገልግሎ ሲመለስ ለአዲስ አበባ 140 ኪሜ ርቀት ያላት መቂ ከተማ  አካባቢ ሲደርስ ባልታወቁ የታጠቁ ሰዎች በአካባቢው በከፈቱት የተኮስ ሩምታ በሐዋርያ እስራኤል ዳንሳ ላይ እግሩ ላይ በጥይት ተመቷል።

መቂ አካባቢ በታጠቁ ሰዎች በተከፈተው ተኮስ የሞቱ ሰዎች እና በርካታ መኪናዎች ተቃጥለው ነበር ።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.2K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:12:38
#Somalia #Eritrea

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በ3 ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ  ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ለ4 ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኤርትራ፣  አስመራ መግባታቸው ታውቋል።

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው የሶማሊያ አቻቸውን ተቀብለዋቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሀሙድ ወደ ፕሬዜዳንትነት የስልጣን መንበር ከመጡ በኃላ ወደ ኤርትራ በስራ ጉብኝት ሲያቀኑ ይህ ሁለተኛቸው ነው።

ከሶስት ወር በፊት ነበር ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ሄደው የነበር።

በወቅቱ በዛው በኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን (ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ ጋር) እንደጎበኙ ፣ ከጉብኝቱ በኃላ ወታደሮቹን ወደ ሀገራቸው ሶማሊያ ለመመለስ በሚቻልበት መንገድ ላይ እየሰሩ መሆኑን ፤ በኤርትራ ከነበራቸው ቆይታ በኃላ ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅትም በኤርትራ ያሉትን 5,000 የሶማሊያ ጦር አባላትን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የአሜሪካን ድጋፍ እንደጠየቁ አይዘነጋም።

ፕ/ት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን መግለፃቸው እና ኤርትራ የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.2K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:12:38
959 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:12:37
#Ethiopia #EU #UNICEF

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የተደረገው ድጋፍ የህፃናትና ሴቶች ኑሮ ለማሻሻልና በግጭቱ ሳቢያ ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ እንዲሁም የጤና አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ለማድረግ ነው።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
916 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 18:12:37
765 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 17:58:00
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲፈታ ተወሰነ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ወንጀል ችሎት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ወስኗል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከዚህ ቀደም በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲወጣ የፈቀደለት ቢሆንም፤ ዐቃቤ ህግ በውሳኔው ቅር መሰኘቱን በመግለጽ ለፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ መጠየቁ ይታወሳል።

በዚህም በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ 3 ተደራራቢ ክሶች ስለቀረቡበት ፍ/ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል በማለት ሂደቱ እንዲቀጥል ያዘዘ ሲሆን፤ ጥቅምት 30/2015 ፍ/ቤት ቀርቦ መዝገቡ ለውሳኔ በሚል ለዛሬ ህዳር 1/2015 መቀጠሩ አይዘነጋም።

Via Ethio FM
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
782 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 17:58:00
በአዲስ አበባ ከተማ ከአራት ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው የመታወቂያ እድሳት አገልግሎት በዛሬው ዕለት ጀምሯል።

የመታውቂያ ዕድሳት አገልግሎት አሰጣጡ ለሕግ ወጥ ድርጊት ተጋልጦ የነበረ በመሆኑ እና የተለያዩ የሰላምና ፀጥታ ስጋት ጭምር በመፍጠሩ አገልግሎቱ መቋረጡ ይታወሳል።

አገልገሎቱ ተድቅኖበት የነበረውን ችግር በማረም እና በማስተካከል ዳግም የመታውቂያ እድሳት በዛሬው ዕለት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።

Photo: EBC
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
724 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ