Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የደንበኞቹን ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገለፀ! ሳፋሪ | Bekulu Entertainment

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ሳምንት የደንበኞቹን ቁጥር አንድ ሚልየን እንደሚገባ ገለፀ!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በነሐሴ ወር ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ900 ሺህ በላይ ደንበኞችን በኢትዮጵያ ማፍራት እንደቻለ አስታወቀ።

የሳፋሪኮም ኩባንያ ዛሬ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በናይሮቢ በቀረበበት መድረክ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንዴግዋ “በኬንያ እና በኢትዮጵያ እንደ የዋጋ ግሽበት፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሽቆልቆል እና ፈጣን ያልሆነ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት የመሳሰሉ ከማክሮ ኢኮኖሚ ጋር የተያያዙ ተግዳርቶች አጋጥመውናል” ብለዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዋር ሶሳ ከአዲስ ዘይቤ ለቀረበላቸው ጥያቄ በመድረኩ እንደተናገሩት ከነሐሴ 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ከ933 ሺህ ደንበኛ ማፍራት ተችሏል ብለዋል። “ቁጥሩ በየጊዜው የሚቀያየር ነው፤ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከ900 ሺህ የተሻገርን ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ሚልየን ደንበኞች እንደርሳለን” ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አንዋር ሶሳ ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራቱን ይቀጥላል ያሉት አንዋር ሶሳ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ከጦርነቱ ነፃ የሆኑ አካባቢዎችን ለመድረስ እቅድ አለን ብለዋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም. በድሬደዋ ከተማ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የሚታወስ ነው።

[Addis Zeybe]
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info