2022-07-15 21:16:47
ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ !
የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፤ የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
" የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
ጌዲኦም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ ሲሆን፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት ነው።
ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በተጨባጭ ተረጋግጧል።
በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ ሲሆን ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ ይገኛሉ።
እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሠቦችና ቡድኖች #ቤት_ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ፤ ይህም ባግብረኃይሉ ተደርሶበታል።
ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅር አማካኝነት ተለይተው ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ይህን በማስገንዘብ፤ ከጥፋት ተልዕኳቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እናስጠነቅቃለን። "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.4K views18:16