Get Mystery Box with random crypto!

ከአድማስ ወዲህ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yohanneslali — ከአድማስ ወዲህ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yohanneslali — ከአድማስ ወዲህ
የሰርጥ አድራሻ: @yohanneslali
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 139
የሰርጥ መግለጫ

የወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ምንጭ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-06 14:59:41 ሂዩማን ራይትስ ዎች ላወጣው ሪፖርት ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መንግሥት የተሰጠ ምላሽ

ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጁን 1 ቀን 2023 (ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም) በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ አካባቢን መርጦ ደጋግሞ ሪፖርት በማዘጋጀት በሰብዓዊ መብት አጀንዳ ሽፋን የተለየ የፖለቲካ ተልዕኮዉን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። የመብት ጥሰት ተፈጽሟል ለማለት የቀረበው ሪፖርት ይዘት ሲታይም ተገቢው ምርመራ ያልተደረገበት እና በበቂ ማስረጃ ያልተደገፈ ከመሆኑ አንጻር እምነት የሚጣልበት አይደለም።

በአጠቃላይ በድርጅቱ የቀረበው ሪፖርት የተዛባና በአካባቢው ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽ፣ ለዘመናት አብረው የቆዩ ሕዝቦችን አብሮ የመኖር እሴት የሚያጠለሽ፣ በሕዝቦች መካከል ግጭት ቀስቃሽ የሆነና ሀገራችን እያደረገች ያለውን የእርቅ እና ምክክር ሂደት የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተፅዕኖ ያለው ሪፖርት ሆኖ አግኝተነዋል።

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ መሆኑ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ ድርጅቱ አንድ አከባቢን ለይቶ በመምረጥ ሪፖርት ማውጣቱና ሪፖርቱም ሀገራችን የእርቅ ሂደቱን በተሟላ መልኩ በመተግበር ላይ እያለች በመሆኑ ድርጅቱ ድብቅ አጀንዳውን በሀገራችን ላይ ለማራመድና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተዛባ ዕይታ እንዲኖረው ለማድረግ እየሰራ ለመሆኑ ማሳያ ነው።

ሀገራችን ኢትየጵያ የሰብአዊ መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር የሚያስችሉ የህግ እና ተቋማዊ አደረጃጀቶች ያሏት ሀገር ስትሆን ይህንኑ ክትትል ለማድረግም እንደ የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያሉ ነጻና ገለልተኛ ተቋማትን አቋቁማለች።

መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሞ የማይታገስ በመሆኑ ምክንያት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ግጭት ተፈጸሙ የተባሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት ጥምር የምርመራ ቡድን እንዲያጣሩ አስፈላጊውን ሁኔታ በማመቻቸትና ሪፖርቱም ሲወጣም በሪፖርቱ የተሰጡ ምክረ-ሃሳቦችን ለመተግበር የሚኒስቴሮች ጥምር ግብረ-ኃይል በማቋቋም መጠነሰፊ የሆኑ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም፣ ተፈጸሙ የተባሉ የመብቶች ጥሰቶች ምርመራ እና የህግ ማሻሻያ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል የነበረውን ግጭት ለማቆም በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማስፈጸም ብሎም በሀገራችን የሚታዩ አለመግባበቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮችን በማዘጋጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ውይይት እየተደረጉ ይገኛሉ።

የቀረቡ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አማራጮች ላይ ከመንግስታዊ ተቋማት፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሰፊ ምክክሮችና የግብአት ማሰባሰቢያ ስራዎች ተሰርተዋል፤ እየተሰሩም ይገኛሉ፡፡ የሽግግር ፍትህ ሂደቱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የፈጸሙ ወገኖች ላይ ተገቢው ማጣራትን በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈንን ጨምሮ እውነትን የማፈላለግ እና ተጎጂዎችንም መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል ማእቀፍ ይፈጥራል። በተጓዳኝ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሀገራችን የሚታዩ ግጭት እና አለመግባባቶችን ከስር መሰረታቸው በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

በሀገራችን ያሉ ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ በራስ አቅም እየተሰሩ ካሉ ስራዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተ.መ.ድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽ/ቤት ጥምር የክትትል ቡድን ተደራጅቶ ግጭቱ በነበረባቸው አካባቢዎች ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እንዲያደርጉ በመጋበዝ መንግስት በሀላፊነት መንፈስ እየሰራ ባለበት ወቅት ይህንን ከግንዛቤ ሳያስገባ እና በቂ ማስረጃ በሌለበት ከላይ በተጠቀሰው ድርጅት የወጣው ሪፖርት ገንቢ ያልሆነና ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው።

ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
10 viewsYohannes Mulugeta, 11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 12:30:43
ፑቲን ዋስትና ተሰጥቷቸዋል

የደቡብ አፍሪካ መንግስት ለብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ እና የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊ ለሚሆኑት ቭላድሚር ፑቲን እና ለሚመለከታቸው ባለስልጣናት "ያለመከሰስ መብት" ሰጥቷል።

የሀገሪቱ መንግስት መደበኛ ነው ባለው እንቅስቃሴ፤ በነሀሴ ወር ለሚካሄደው ጉባኤ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነው ተብሏል።

በዩክሬን እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (የአይ ሲሲ) ክስ የተመሰረተባቸው የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጉባኤው መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል።

የአይ ሲ ሲ አባል የሆነችው ደቡብ አፍሪካ በጉባኤው ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቁትን ፕሬዝዳንት ፑቲንን አሳልፋ ለመስጠት ትገደዳለች ሲባል የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ግን ሀገሪቱ ሙሉ ዋስትና እንደምትሰጥ አረጋግጣለች።
27 viewsYohannes Mulugeta, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 10:26:43
ክሊኒክ ዘው ብሎ የገባው ጅብ መርፌ ተወግቶ ወጥቷል
በምዕራብ ሀረርጌ በገላምሶ ትናንት የተሰማው ዜና አስገራሚ ነው። ጠዋት ሲነጋ አንድ ጅብ ሚልኪ የሚባል የግል ክሊኒክ ዘው ብሎ ይገባል። በክሊኒኩ የሚሰራ ነርስ የተከሰተውን ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ እንዲህ ሲል ተናግረዋል እንደሚከተለው በፋስት መረጃ ይቀርባል።

"ጠዋት አራት ሰዓት አካባቢ ነው። የክሊኒካችን በር ክፍት ነበር። ሥራ እንኳን አልጀመርንም። ጅቡ በቀጥታ በተከፈተው በር ገብቶ ወደ ላቦራቶሪ ክፍል ገባ፣ ይህን ያዩ ሰዎች ደንግጠው ዱላ ይዘው ሊደበድቡት ነበር፣ የክሊኒኩ ባለቤት ግን ሰዎችን አረጋግቶ እንዳይመቱት አደረገ።

ጅቡ ወደ ላቦራቶሪ ክፍል ከገባ በኋላ ተጠቅልሎ እንደተኛ የገለፁት ሐኪሙ፣ ሁኔታው ታሞ እንጂ ሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የሚያደርስ አይመስልም ብለዋል።

“ጅቡ ታሞ ሊሆን እንደሚችል ጠረጠርን። ከዚያም የእንስሳት ሐኪም ደወልኩ እሱም መጥቶ ‘Antirabies’ መርፌ ስጡት አለ፣ ከዚያም ወደ ፋርማሲ ሄጄ መድሃኒቱን ገዛሁና ቀስ ብዬ መርፌ ሰጠሁት” ይላል ነርሱ።

ጅቡም መርፌ ከተወጋ ከ20 ደቂቃ በኋላ ተነስቶ ሄዷል። ጅቡ የገባበትን የላብራቶሪ ክፍል በማጽዳት ክሊኒኩም መደበኛ ስራውን እና የሰው ልጅ ህክምናውን እንደቀጠለ ተናግረዋል(BBC Amharic)።
36 viewsYohannes Mulugeta, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-22 14:51:32
የልዕል አለማየሁ አስክሬን እንደማይመለስ እንግሊዝ አሳወቀች!

#Ethiopia | የልዑል አለማየሁን አስክሬን እንድትመልስ ጥያቄ የቀረበላት እንግሊዝ ከንጉሣውያን ጎን በመቀበሩ አጽማቸው ያረፉት ሳይረብሹ ለማውጣት አዳጋች ስለሆነ አልቀበልም አለች።

ባኪንግሃም ቤተ መንግሥት በዊንድሶር ካስል ውስጥ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተቀበረውን የኢትዮጵያዊ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስን አጽም እንዲመለስ የቀረበለትን ጥያቄ እንደማይቀበል ገለፀ።

ቤተሰብ፣ የልዑሉ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ እና መንግሥት የልዑሉ አጽም ወደ ትውልድ አገሩ እንዲመለስ ከየትኛውም ጊዜ በላይ አጥብቀው ቢጠይቁም፣ የእንግሊዝ ንጉሥውያን መልስ ግን “ለጥያቄው ምላሽ መስጠት አይቻለንም” የሚል ሆኗል።

የባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ልዑል አለማየሁ ተቀብሮ ባለበት ስፍራ “አርፈው የሚገኙት ሳይረበሹ አጽሙን ማውጣት የሚቻል አይደለም፤ ስለዚህ ለጥያቄው ምላሽ መስጠት እንደማንችል እናሳውቃለን” ሲል ቢቢሲ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።

ልዑል አለማየሁ እግሩ የእንግሊዝ ምድርን ሲረግጥ ገና የሰባት ዓመት ታዳጊ የነበረ ሲሆን፣ እናቱ በጉዞ ላይ መሞታቸውን ተከትሎ ወላጅ አልባ ሆኖ ነበር።

በጎንደር ያሉት የልዑሉ ቤተሰቦች ግን አጭር ዕድሜውን በሰው አገር በብቸኝነት አሳልፎ በሐዘን ሕይወቱ ያለፈው ልዑል፣ ከእንግሊዝ ነገሥታት ጎን መቀበሩ ብቻ “ለነፍሱ እረፍት አይሰጥም” ይላሉ።

በጎንደር የሚገኙ የአጼ ቴዎድሮስ ሦስተኛ እና አራተኛ ትውልድ ቤተሰብም ልዑሉ “የዘላለም እረፍት” ያገኝ ዘንድ አጽሙ ወደ ትውልድ አገሩ መመለስ አለበት ሲሉ ለባኪንግሃም ቤተ መንግሥት ይፋዊ ጥያቄ አቅርበው ነበር።የአጼ ቴዎድሮስ አራተኛ ትውልድ ቤተሰብ የሆነው ፋሲል ሚናስ፣ ልዑሉ ማረፍ ያለበት በባዕድ አገር ሳይሆን በአባቱ አገር ጎንደር ነው ይላል።


BBC Amharic
33 viewsYohannes Mulugeta, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 13:32:19 የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።
ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
39 viewsYohannes Mulugeta, 10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 09:48:18
አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
*********************

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ባደረባት ሕመም በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ወደ ሙዚቃው ዓለም በ1949 ዓ.ም እንደገባች እና ረጅም የሙዚቃ ጊዜዋን በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ እንዳሳለፈች የሕይወት ታሪኳ ያስረዳል።

ሂሩት በቀለ በተለይ “ኢትዮጵያ” በሚል የተጫወተችው ዘፈን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ እና ትንሽ ትልቁ በሀገር ፍቅር ስሜት የሚያዜመው ነው።
49 viewsYohannes Mulugeta, 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 09:50:51
አንድ ሰው በኬኒያ ሀገር ለመታከም ወደ መንግስት ሆስፒታል አቅንቷ 'X-ray' ከተነሳ በኋላ ፣ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለች በረሮ ልቡ ውስጥ እንዳለች ይነገረዋል ።

ወደ ሲንጋፖር ሄዶም መታከም እንዳለበት ይነግሩታል ።
ታማሚውም ወደ ሲንጋፖር ሄዶ ሲታይ ፣ የታየው በረሮ ልቡ ውስጥ ሳይሆን 'X-ray' ከሚያነሳው ማሽን ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያስረዱታል ።

ብዙ ግዜ የምንያበትን ነገር ሳናፀዳ አሊያም የምንመለከትበት መስታወት ሳነነፃ የሌላውን እድፍ ለመናገር እንሮጣለን ፣ እድፉ እኛ ምንለው ነገር ሳይሆን አስተሳሰባችን ወይም የምናይበት መነፅር ነው !
33 viewsYohannes Mulugeta, 06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 10:47:49
ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው አረፈ

 ከአርቲስት መርአዊ ስጦት ቀጥሎ የመጣውና በቅርቡ ለስራ ወደ ጣሊያን ሀገር የተጓዘው ትንግርተኛው ክላርኔት ተጫዋች ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በተኛበት ክፍል ሞቶ ተገኘ ። የጣሊያን ፖሊስ የአሟሟቱን ሁኔታ እያጣራ ሲገኝ አስከሬኑን ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት በፈረንሳይ ሀገር የምትገኘው አርቲስት Blen Getachew እና የሙያ አጋሮቹ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ።

ለቤተሰቡ ፣ ለወዳጆቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን ።

የወንድማችንን ነፍስ ይማር ።
ቴድሮሰ ተክለአረጋይ
42 viewsYohannes Mulugeta, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:05:43
በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በማስወገድ ሰላምን ለማምጣት ያለመውና በታንዛኒያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ውይይት የመጀመሪያ ምዕራፍ ዛሬ መጠናቀቅን መንግሥት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ÷ ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው የውይይት ምዕራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም ብሏል፡፡

ግጭቱን በዘላቂነትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማስቆም እንዲቻል ሁለቱም አካላት የሰላም ውይይቱን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑ ላይ ተግባብተዋል ብሏል መግለጫው።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትና እስካሁን ሲመራባቸው በነበሩ መሠረታዊ መርሖች መሠረት ግጭቱን በሰላማዊ መልኩ ለመፍታት መንግስት የጸና አቋም እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡

ይህንን መልካም አጋጣሚና በውይይት ችግሮችን የመፍታት በጎ ጅምር በመጠቀም÷ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ፅኑ አቋም ዳግም ያረጋግጣል ብሏል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው፡፡

የሰላም ውይይቱን ላመቻቹና ላስተናገዱ አካላት የኢፌዴሪ መንግሥት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
33 viewsYohannes Mulugeta, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 17:48:03
ኢትዮዽያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ሚሊዮን እግረኛ ሰራዊት ያላት የአፍሪካ ግዙፍ የሰራዊት ባለቤት ልትሆን ነው ሲል ኦን ዘደይ ዘገበ። ከዚህ በፊት በ600ሺ ወታደር ብቻ ከአፍሪካ ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀነጠችው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኢትዮዽያ በመጭው 2024 አንድ ሚሊየን ጦር ያላት አገር ትሆናለች ብሏል የኦን ዘደይ ጋዜጣ። አገሪቱ የክልል ልዮ ሀይሎችን አፍርሳ ወደ አገር መከላከያ ስትቀይር 400ሺ ተጨማሪ ሀይል ታሰልፋለች ብሏል።
Ethio Today
38 viewsYohannes Mulugeta, 14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ