Get Mystery Box with random crypto!

ወራዙት(Orthodox Youth)

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo_haymanotae — ወራዙት(Orthodox Youth)
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahdo_haymanotae — ወራዙት(Orthodox Youth)
የሰርጥ አድራሻ: @tewahdo_haymanotae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 873
የሰርጥ መግለጫ

A Church without Youth is a Church without a future. Moreover, Youth without a Church is Youth without a future.
Pope Shenouda III

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 15:02:13

https://t.me/+YZYAOpgOgns2Njdk
https://t.me/+YZYAOpgOgns2Njdk
https://t.me/+YZYAOpgOgns2Njdk
672 viewsedited  12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:11:34
ኦርቶዶክስ ኖት ?

ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።

➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው።

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 🇯 🇴 🇮 🇳  █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
2.8K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 22:24:41 የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ
ይፈልጋሉ? የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት
መፅሐፉን ያግኙ። መልካም ንባብ



መጽሐፍ ቅዱስ
እመጓ
ዝጎራ
መርበብት
ዴርቶጋዳ
ዮራቶራድ
ዣንቶዣራ
መጽሐፈ ሄኖክ
ቤተክርስቲያንህን እወቅ
ፍኖተ አእምሮ
አዳም እና ጥበቡ
ዝክረ መስቀል
ሰይፈ ሥላሴ
ፍትሐ ነገስት
መጽሐፈ መነኮሳት
ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
ህግጋተ ወንጌል
ነገረ ማርያም ቤተከርስቲያን
ድርሳነ ሚካኤል ወገብርኤል
ውዳሴ ማርያም
የወጣቶች ህይወት
መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
የዋልድባ ገዳም ታሪክ
መጽሐፈ አክሲማሮስ
14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት
መልክዓ መለኮት
መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት
ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
ሐይማኖተ አበው
ራዕየ ማርያም
የመናኝ ጉዞ
መልክዓ እግዚአብሔር
ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
ፍካሬ ኢየሱስ
መርበብተ ሰሎሞን
የቶ መስቀል ትርጉም
መጽሐፈ ፈውስ
ባሕረ ሐሳብ
ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
የ666 ሳይንሳዊ ምስጢር
ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
ህይወተ ቅዱሳን
ነገረ ቅዱሳን

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒
▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒
▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒
▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
3.3K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-07 13:03:01
3.2K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-04 08:26:11
3.1K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 16:45:11 ፨የናቁሽም ሁሉ፨
ዛሬ የናቁሽ ሁሉ
ወደ እግርሽ ጫማ ሰግዳሉ
ይላል ቅዱስ ቃሉ፡፡
ታዲያ ዛሬ የሚንቋት ሁሉ
ጽዮን ተራራ ናት በድፍረት ይላሉ
ኧረ ለመሆኑ ከመቼ ወዲህ ነው
ግዑዙ ተራራ የ’ግር ጫማ ያለው?
ደግሞስ ጭፍን ብለው
ተራራ ነው ያሉት
የታለና ዛሬ ከጽዮን ተራራ
3.2K viewsedited  13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 16:44:16
3.0K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 07:16:17 ህዳር 12
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ስላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ የገናናው ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው። በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)
የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት “… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ.5፡13) ይለናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ አለ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱም ዘንዶውን ተዋጉት፥ ዘንዶውም አልቻላቸውም፥ ከዚያም በኋላ በሰማይ ቦታ አልተገኘለትም። ራእ 12፤7 ነብዩ ዳንኤልም እንዲህ አለ "በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል" ዳን ፲፪፥፩።
አዲስ አበባ ውስጥ ከተተከሉት አብያተክርስቲያናት ቀዳሚው የካ አንቆርጫ የሚገኘው የካ ሚካኤል(ዋሻ ተክለሃይማኖት )ነው፤ የተተከለው በ 4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአብርሃና አጽብሃ ሲሆን ታቦቱ የመጣው ከታቦተ ጽዮን ጋር አብሮ ነው፤ በአሁኑ ሰዓትም የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ሾላ በሚገኘው የካ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይገኛል።
ለዚህም ይመስላል አንዳንድ ምዕመናን አጥቢያቸው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እያለ የካ ሚካኤል ድረስ ሄደው የሚያነግሱት፤
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክርቡ
አሜኝ
3.1K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-14 10:28:44 ተፈፀ ተፈፀመ ተፈፀመ

" ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር
ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር”
※ ※ ※ ※ ※ ※
የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ በዕቅፍሽ እንዲጠጋ እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ በርሱ ዐማጽኚ።

እመቤታችን ሁላችንን በምልጃዋ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣ከመርገም ወደ በረከት፣ ከርኵሰት

እንኳን አደረሰን


// ከሀሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ክብርት ቅድስት ቤተክስቲያን እናምናለን //


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Dnkedametsega27
@Dnkedametsega27
2.6K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 05:35:48
#የእግዚአብሔር_ትዕዛዛቱ_ቀላል_ናቸው!!

ልጆቼ! የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደሆነ የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም ታስሬ አስፈትታችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ታምሜ አድናችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ተርቤ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መዓድ ሳይሆን አንዲት ዳቦ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መጠጥ ሳይሆን አንዲት ቀዝቃዛ ኩባያ ውኃ አጠጥታችሁኛልና ነው የሚለን፡፡

በጣም የሚያቀለው ደግሞ እነዚህን ቀላል ትእዛዛት በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸው አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በቃሉ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ስለሚለን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን ነው፡፡ እንግዲያውስ ድሀ ስለሆንኩ እነዚህን ማድረግ አልችልም ብለን ራሳችን ሰነፎች የምናደርግ አንሁን፡፡ ሺህ ጊዜ ደሀ ብንሆን ሁለት ሳንቲም ከሰጠችው መበለት በላይ ድሀ ልንሆን አንችልምና፡፡ ስለዚህ ስንፍናን ከእኛ እናርቅ፡፡

ልጆቼ! እነዚህን በእርሱ እርዳታ ስላደርግንስ ምን እንደምንባል ትገነዘባላችሁን? “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን!” ካላደረግንስ? “እናንተ ርጉማን ከእኔ ዘንድ ሂዱ!” እንግዲያውስ ለእኛ ሳይሆን ለሰይጣንና ለመላእክቱ የተዘጋጀውን እሳት ከሚያገኘን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለእኛ የተዘጋጀውን መንግሥት እንወርስ ዘንድ ዛሬ አብዝተን ዘይት የምንገዛ እንሁን፡፡ እንደነዚያ ሰነፍ ደናግላን እዚያ መግዛት በማይቻልበት ቦታ ሄደን ከምንጠይቅ ዛሬ ሳይመሽብን የሚበቃንን ያህል ዘይት እንግዛ፡፡ ዘይቱ የሚገዛውስ የት ነው? የታመሙት ጋር፤ እስረኞች ጋር፤ ቁርና ሀሩር በሚፈራረቅባቸው ወንድሞቻችናነ እኅቶቻችን ጋር፡፡

ልጆቼ! እንደ ነዌ እዚህ ምድር ባለጸጎች ሆነን ያኔ ከምንለምን ዛሬ አልዓዛርን ልናስበው ይገባል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@Dnkedametsega27
2.5K views02:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ