Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-11-14 14:10:28
በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት ከ1.5 ሚልዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ!

ኮመዲያን እሸቱ መለሰ "በሀገረ አሜሪካ ለሚቋቋመው ግዙፍ ስፋት ያለው ገዳም ቦታ መግዣ" ከ 1,500,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ በአንድ ቀን መሰብሰብ ችሏል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳም ሥም ከ1497 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው መሬት ልትገዛ እንደሆነ ማስታወቋ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ለገዳሙ መግዣ የሚሆነው ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሜዲያን እሸቱ በትናንትናው እለት ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ከ15ሰአት በላይ በላይቭ(live) በመቆየት በአጠቃላይ ከ1.5ሚሊዮን ዶላር በላይ በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ፈጣን የገቢ ማሰባሰብ ስራን አከናዉኗል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስም የገቢ ማሰባሰቡን ያካሄዱትን ኮሜዲያን እሸቱን እና የዶንኪ ቲዩብ አባላቶችን ከልብ አመስግነዋል።

በዚህ ሰፊ ይዞታ ላይም የአብነት ትምህርት ቤት፣ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ዘመናዊ ዩኒቨርሲቲ፣ ሆስፒታል እንዲሁም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ለማቋቋም እንደታቀደ የገለጹት ሊቀ ጳጳሱ፣ ለቦታው መግዣ የሚሆነውን 8 ሚሊዮን ዶላር ከምዕመናን ለማሰባሰብ እንደታሰበም ተናግረዋል።

Via:- Fidel Post
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.2K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 14:10:28
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ  ይሰጣሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ  እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ኀዳር 06 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል።

በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 14:10:28
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ከአምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ
**********************

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ከሆኑት ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ።

የጃፓን ህዝብ እና መንግሥት ለክልሉ ልማት እያደረጉት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደንቁ ዶ/ር ይልቃል ለአምባሳደሯ ገልፀውላቸዋል።

አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ ብቁ የሰው ኃይል ለማውጣት ላለፉት 7 ዓመታት ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የጃፓን ዩኒቨርሲቲዎች ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በመስራት በትምህርት ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ የሀገሪቱ መንግሥት ባህርዳር ከተማን ጨምሮ በአማራ ክልል በግብርና፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

አምባሳደሯ በቆይታቸው በክልሉ የጤና ተቋማት የካይዘን ትግበራ ያለበትን ደረጃ ጨምሮ በመንግሥታቸው የሚደገፉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን እንደሚመለከቱ ይጠበቃል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 21:44:04 በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጸሙ "የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ምርመራ እንዲጀመር እና አጥፊዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ" አሜሪካ ጥሪ አቀረበች።

የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ግጭት ለማቆም፣ ለተቸገሩ ሁሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን፣ የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት ለመጠበቅ እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለማስጀመር የደረሱበትን ስምምነት ሊያከብሩ እንደሚገባ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ጥሪ አቅርበዋል። ኔድ ፕራስ ትላንት ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ ጥሪውን ያቀረቡት የሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት የጦር አዛዦች የፕሪቶሪያውን ሥምምነት ተግባራዊ የሚያደርግ ሰነድ ከፈረሙ በኋላ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እና የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ታደሰ ወረደ ሰነዱን ከፈረሙ በኋላ የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ በትግራይ እና አጎራባች ክልሎች ለተቸገሩ ሁሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ያለ ገደብ ለማመቻቸት ከሥምምነት መደረሱን አስታውቋል። ሁለቱ የጦር አዛዦች የተፈራረሙት ሰነድ በፕሪቶሪያ በተደረሰበት ግጭት የማቆም ሥምምነት መሠረት ለግብረ ሰናይ ሠራተኞች እና ለድርጅቶች የደህንነት ዋስትና መስጠት እንዲሁም ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ማድረግን ያካተተ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት ያወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው የትጥቅ አፈታት፣ አበታተን እና መልሶ ማዋሃድን የተመለከቱ ጉዳዮችን በዝርዝር የሚያብራራ የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም ተወስኗል። የኢትዮጵያ መንግሥት "በሰላም ሥምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበት እና መከላከያ ወደ መቐለ የሚገባበት ዕቅድ ላይ" ከሥምምነት መደረሱን ገልጿል። የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አኔተ ቬበር የትጥቅ አፈታትን በተመለከተ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ሥምምነት "ወደ ፊት የሚወስድ አስፈላጊ እርምጃ" እንደሆነ ገልጸዋል።
 ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
505 views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 16:25:24
ሸዋ ደራ ጉንዶ መስቀል  ከአድስ አበባ 220 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች!

ከህዳር 03 ቀን ጀምሮ በኦነግ ሸኔ ከበባ ውስጥ ናት።

አሸባሪ ሸኔ አምሰት የደራ ቦታ ላይ ሰፍሯል
1. ባቡ ድሬ
2. ሀርቡ
3. ራቾ አሙማ
4.ጁሩ ዳዳ
5. ሰለልኩላ ዙሪያ ቡርቃ የሚባል አካባቢ

በተለይ ጉንደ መስቀል ከተማ ውስጥ ገብተው ብዙ ሰው አግተዋል ሞተዋል። ከከበባ ለመውጣት እየተፋለመ ያለው ሚሊሻ ብቻ ነው ፤ እስካሁን በአካባቢው የመንግስት አካል የለም።

ትኩረት ለደራ  ሽዋ!

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
933 views13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-13 12:12:43 አሸባሪው ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጉንዶ መስቀል ከተማ መግባቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ መንግስት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸውም ጠይቀዋል።የሽብር ቡድኑ ከትናንት ጀምሮ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ከተማዋ እየገባ መሆኑንና ከተማዋን ሙሉ በሙሉ እንዳይቆጣጠር ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናገረዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች በቂ የጸጥታ ሀይል ባለመኖሩ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸው መንግስት በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል።

[Ethio FM]
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
531 views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:12
የዛሬው ስምምነት የተፈረመበት ዶክመንት ተያይዟል።

ዋና ነጥቦች:
- በሚቀጥሉት 7 ቀናት ወታደራዊ ሀላፊዎቹ ለወታደሮቻቸው ኦረንቴሽን ይሰጣሉ

- ከዛም የፌደራል ባለስልጣናት በትግራይ ሀላፊነታቸውን ይረከባሉ

- የከባድ መሳርያዎች ትጥቅ አፈታት በትግራይ ክልል ያሉ የውጭ ሀይሎች እና ከመከላከያ ውጭ ያሉ ሀይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ ይፈፀማል

- የቀላል መሳርያዎች ትጥቅ አፈታትን ለማሳለጥ ከሁለቱም ወገን የተውጣጣ ኮሚቴ ይቋቋማል።

Via:- ኤልያስ መሰረት
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
344 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:12
270 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:11
255 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:10
220 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ