Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-11-10 17:58:00 ትላንት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፓርቲዉ በመግለጫዉ ካነሳቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፡-


፩. በሰላም ሥምምነቱ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ቡድኑ ትጥቁን እንዲፈታ መንግስት በሙሉ አቅሙ እና ትኩረት እንዲሰራ፤

፪. የ “ነጻ አውጭ ግንባሮች” ፖለቲካዊ ኅልውና ሕጋዊ እውቅና በሚያገኝበት ሀገር ፣ የሀገር ሉዐላዊነት ፣ የግዛት አንድነት እና ሀገራዊ አንድነት ማረጋገጥ የማይቻል በመሆኑ ፤ መንግስት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ እያለ የሚጠራው ቡድን እና መሰል “ነጻ አውጭ” ቡድኖች የፖለቲካ ኅልውናቸው እንዲከስም እንዲሰራ እና የሕግ ክልከላ ስራ ላይ እንዲያውል፤

፫. የአማራ ሕዝብ ክፋይ የሆኑት እና ከ30 ዓመት በላይ በአማራዊ ማንነታቸው ምክንያት የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች አሁን ባሉበት አማራ ክልል ሥር ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኙ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፌዴራሉ መንግስት በአፋጣኝ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ፣ እና

፬. በአሸባሪው ትሕነግ ጀማሪነት በሶስት ተከታታይ ዙር በተካሄደው የወራራ ጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ፣ አፋር እና ትግራይ አካባቢዎች መልሶ የመገንባት እና የማቋቋም ሥራ የፌደራል መንግሥቱ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት እንዲመራና እንዲያስተባብር፣ መላው ኢትዮጵያውያንም ለመልሶ ግንባታው እና መቋቋሙ ሥራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ንቅናቄዉ ጠይቋል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
730 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 17:58:00 በጅቡቲ ወደብ ከመርከብ ላይ በቀጥታ መጫን የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ሊተገበር ነው

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ የወደብ አገልግሎት ጋር በመሆን ቀደም ሲል በጭነት ማራገፍና ማጓጓዝ ረገድ ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አሰራሮችን ሊተገብሩ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ተናበው በመስራታቸው በመርከብ ጭነት አገልግሎት እና በሎጀስቲክስ ዘርፍ ውጤታማ ስራ መስራት አስችሏል ሲሉ የዶራህሌ መልቲፐርፐዝ የስራ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

የዶራህሌ መልቲፐርፐዝ የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ኦፊሰር ኢድሪስ ዶሆር አህመድ የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ግንኙነት ከጀመረበት ካለፉት 30 ዓመታት ጀምሮ በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ባህር ትራንሰፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅትና የጅቡቲ ወደብ ተናበው መስራታቸው በመርከብ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዘርፍ ውጤታማ ስራ እንዲከናወን አድርጓል ሲሉም ኃላፊው አስታውቀዋል።

ስራው በየሰዓታቱ እንድንገናኝ የሚያስገድድ እንደመሆኑ የመርከቦችን መድረሻ፣ የመርከብ ላይ ጭነት ማራገፍ፣ የየብስ ከባድ ተሽከርካሪ ጭነቶችን እና የባቡር ጭነቶችን አንድ ላይ አቅደን መስራታችን ክንውናችንን ውጤታማ አድርጎታል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ከመርከብ ላይ በቀጥታ መጫን የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ ዕውን እንደሚያደርጉ አስረድተው የ2015 የአፈር ማዳበሪያ ቀደም ሲል ሲወስደው ከነበረው ባጠረ ጊዜ ወደ ሚፈለግበት ስፍራ ማድረስ የሚያስችል አሰራሮችን መዘርጋታቸውን ገልፀዋል፡፡


Via:- ዋልታ
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
885 views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:07:57
ታደሰ ወረደ፣ ብርሃኑ ጁላ እና ባጫ ደበሌ

ሰናይ ምሽት

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.4K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:07:57
በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት መታቀዱ ተነገረ!

ከሳምንት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ለአስር ቀናት ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጲያ መንግስት እና የህወኃት ቡድን ውይይት የሰላም ስምምነት ፊርማ በማኖር መጠናቀቁን እንዳስደሰታቸው የኢትዮጲያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር አስታውቋል፡፡የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መቆያ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ከእዚህ ቀደም የኢትዮጲያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር በአፋር እና በአማራ ክልል አንዳንዳ አከባቢዎች በጦርነቱ ሳቢያ ውድመት የደረሰባቸው ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ሲያጣራ መቆየቱን አንስተዋል፡፡

ያም ሆኖ ግን አስተማማኝ ሰላም ባለመኖሩ በክልሎቹ በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙ ቅርሶች በጦርነቱ ሳቢያ ከፍተኛ ውድመት እንዳጋጠማቸው ያነሱ ሲሆን አንዳንዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡የደሴ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች የጦርነቱ ሰለባ የሆኑ ቅርሶችን ለመጠገን እና ታሪካዊ ይዞታቸውን መልሰው እንዲይዙ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በአሁን ሰዓት በፌደራል መንግስቱ እና በህወኃት መካከል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ የማጣራት እና አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አቶ መቆያ ማሞ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ከእዚህ ቀደም የነበረው አለመረጋጋት በመሰረተ ልማት ላይ ውድመት በማድረሱ እና የሰላም ሁኔታው አስማማኝ ባለመሆኑ ቅርሶች ያሉበትን ሁኔታ ለማጣራት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖ ነበር ሲሉ ሃላፊው በተጨማሪነት አንስተዋል፡፡


[ዳጉ ጆርናል]
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.4K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:06:52
የኢትዮጵያ መንግሥትና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች ናይሮቢ ላይ በዝግ እያካሄዱት ያለው ውይይት እስከ ዓርብ ድረስ እንደሚቀጥል ከዲፕሎማቲክ ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

ውይይቱ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ አንዳንድ የውጭ ዜና ወኪሎች ዘግበው ነበር። ውይይቱ የሕወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለትግራይ በሚቀርብበትና መሠረታዊ አገልግሎቶች በሚጀምሩበት ሁኔታ ዙሪያ እንደሆነ ቀደም ሲል ተገልጧል።

የሁለቱ ወገኖች ውይይት ባለፉት ሦስት ቀናት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ የውይይቱ አስተባባሪ አፍሪካ ኅብረት የሰጠው ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በኬንያጉብኝት ላይ ያሉት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎዛና የኬንያው ሩቶ ሁለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገብሩ ዛሬ በጋራ ጠይቀዋል።

Via Wazema
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.2K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 21:06:52
በዝቋላ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመለሰ!

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዞን ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው ከቆዩት ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የሳህላ ወረዳ ዝቋላ ከተማ በዛሬው ዕለት ኤሌክትሪክ አግኝታለች፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:58:07
ከሕዳር 15 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር ተገለጸ!

ከሕዳር 15/2015 ጀምሮ ኢትዮጵያ ለኬንያ 500 ኪሎ ቮልት የኤሌትሪክ ኃይል መላክ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በሳምንቱ በተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ኹነቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ጋር የኤሌትሪክ ኃይል ለመሸጥ ስምምነት ማድረጓ የሚታወቅ ሲሆን፤ ወደ ኬንያ የሚላከው የኤሌትሪክ ኃይልም በተደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑን አምባሳደሩ በማብራሪያቸው መናገራቸውን ዋልታ ዘግቧል።

የኢትዮ- ኬንያ የማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ስቴሽን ፕሮጀክት በ334 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነባ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 214 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላሩ ለኮንቨርተር ስቴሽኑና ለግራውንድ ኤሌክትሮድ መስመር የግንባታ ሥራ እንዲሁም 120 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ለማስተላለፊያ መስመሩ የዋለ ነው፡፡

የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት እስከ 2000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፍ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

አምባሳደር መለሰ አለም አክለውም በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረው ግጭት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ላይ መደረሱን ተከትሎ የተለያዩ የኢትዮጵያ ወዳጅ አገራትና ድርጅቶች በመልሶ ግንባታውና በሰብአዊ እርዳታ ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.3K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:58:06
የደራሲ በአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ አበራ አረፉ

የታላቁ ደራሲና ጋዜጠኛ የበአሉ ግርማ ባለቤት አልማዝ ዛሬ ጥቅምት 30/2015 ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው አርድተውኛል ሲል ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ አስታውቋል።

አልማዝ ባለቤታቸውን የበአሉ ግርማን ሞትና መሰወር አልቀበል ብለው የቆዩ ሲሆን፤ ሁልግዜ ጠዋት ላይ ቤታቸውን አፀዳድተው በር ከፍተው በአሉ ግርማን ይመጣል እያሉ ሲጠብቁት ኖረው በዛሬው ዕለት ህይወታቸው አልፏል።

አልማዝ አበራ ከደራሲ በአሉ ግርማ ያፈሯቸው የሦስት ልጆች እናት ነበሩ።

ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማርል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:58:06
1.0K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:58:06
300 የአየር ኢላማዎችን የመለየት ችሎታ ያለው የሩሲያው “በራሪ ራዳር”

በራሪው ራዳር “ዶራ” በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ የአየረ ላይ ኢላማዎችን የመለየት እና የመከታተል አቅም ያለው መሆኑ ተነግሯል።“ዶራ” አውሮፕላን በ600 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የአየር ኢላማዎችን በመከታተል እና በመለየት ተዋጊ ጄቶችን ወደ ኢላማዎቹ የመላክ አቅም ያለው መሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ።"በራሪው ራዳር" ለሩሲያ ተዋጊ ተዋጊ ጄት አብራሪዎች ብዙ ጠቀሜታ አለው የተባለ ሲሆን፤ የሩሲያ አየር ኃይል የጠላት የአየር ዒላማዎችን ለማጥፋት አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት ከፍተኛ ግልጋሎት ይሰጣል።

Via Al ain
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
943 views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ