Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-11-12 14:26:53
አርሶ አደሩ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር) በሀገሪቱ በቆላማ፣ ሞቃታማና መካከለኛ ቦታዎች ላይ ሰብል እየተሰበሰበ እንደሚገኝ ተናግረው በደጋማው አካባቢ ሰብል በመድረሰ ላይ እንዳለም አመላክተዋል።

የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት ትንበያ እንደሚያመለክተው በሚቀጥሉ ቀናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊቀጥል እንደሚችል አስታውቋል።

በደረሰ ምርት ላይ ዝናብ ጉዳት እንዳያደርስ አርሶ አደሩ፣ የግብርና ባለሙያው እና በየደረጃው የሚገኘው አመራር በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተያዘው የመኸር ወቅት ስንዴ አሰባሰብ ላይም የህብረት ስራ ማህበራትን ጨምሮ ተማሪዎች፣ የግብርና ሙያተኞችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በማድረግ በዘመቻ የሰብልን ብክነት ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።በ2014/2015 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከተሸፈነ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
640 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:11:14
"በወልቃይትና ራያ ጉዳይ ካለፈው የተለየ አቋም የለንም!" ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

በወልቃይትና በራያ ጉዳይ የተደራደርንበት አግባብ የለም። ካለፈው የተለየ አቋም የለንም። ወደፊትም አይኖርም። የወልቃይትና ራያ ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
666 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:11:14
659 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:11:14
#UPDATE ላለፉት ጥቂት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ውይይትን ተከትሎ በነገው እለት 5 ሰአት ገደማ በዝርዝር ስምምነት ነጥቦቹ ላይ ፊርማ እንደሚያኖሩ የታወቀ ቢሆንም ከህወሓት መንደር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ብዙዎች የተከድተናል ቅስቀሳው ከትላንት ጀምሮ እየተጎሰመ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
753 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:11:14
752 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 23:34:55
ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

“'የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የስራ አመራሮች ጋር የነበረው የጋራ ውይይት ባለመግባባት ተበተነ' ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን!”- ኮሚቴው

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
519 views20:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 22:58:47
#UPDATE ላለፉት ጥቂት ቀናት በናይሮቢ ሲካሄድ የነበረው ውይይትን ተከትሎ በነገው እለት 5 ሰአት ገደማ በዝርዝር ስምምነት ነጥቦቹ ላይ ፊርማ እንደሚያኖሩ ከኬንያ ጋዜጠኞች ማምሻውን የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል ሲል ኤልያስ መሰረት አሳውቋል።

ቸር ያሰማን
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
576 views19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 20:31:09
ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብዓዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን ተገለጸ!

ወደ ትግራይ ክልል የሚወስዱ ሁሉም ኮሪደሮች ለሰብአዊ ደጋፍ አቅርቦት ክፍት መደረጋቸውን የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች የሰሜን ኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያቀርቡ ተቋማት የየብስም ሆነ የአየር ትራንስፖርት ክፍት መደረጉን ገልጸዋል።በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ፣ በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ፤ በጎንደር አዲ አርቃይ ማይጸምሪ ሽሬ እንዲሁም የወልዲያ አላማጣ መስመሮች ሁሉም ለሰብዓዊ እርዳታ ክፍት እንደሆኑ ተናግረዋል።

በአፋር ክልል ከአብዓላ መቀሌ የሙከራ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን በሁመራ በኩል ሽራሮ፣ ሽሬ አክሱም አድዋ በኩል ከገቡ 16 ከባድ መኪናዎች መካከል ሶስቱ የሕክምና ቁሳቁስ ይዘው መግባታቸውን አመልክተዋል።“ማንኛውም የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ተቋም በአየርና በየብስ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ይችላል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
895 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 17:20:35 "ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው" የሚሉ ማጭበርያዎች እንዳሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ!

ስልክ እየደወሉ እና የተለያዩ የማጭበርበር ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ፡፡

በከተማችን አ/አበባ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ስልኮች እየተደወለ እንኳን ደስ አላችሁ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ሲስተም እያስተካከልን ነው፣ የሞባይሎትን አቅም ከ4G ወደ 5G እየቀየርን ነው፣ ከሌሎች ባንኮች ጋር ኦንላይን ሲስተም እየጀመርን ነው በሚሉ እና በሌሎች ማደናገሪያዎች በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች የማጭበርበር ወንጀል እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ የምርመራ መዛግብቶችን ዋቢ አድርጎ እንደገለፀው አንዳንዶቹም የማጭበርበሪያ ስልቶች ግለሰቦች እንዲያምኑ በኤቲም ገንዘብ ያወጡበት ትክክለኛ ቀን ተነግሯቸው የወንጀሉ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙ ሲሆን የግለሰቦች የባንክ ሚስጥር የሚወጣበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ ምርመራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ወንጀሉ በልዩ ልዩ የአፈፃፀም ስልቶች እየተፈፀመ ከመሆኑም ባሻገር ስልክ በመንጠቅና ቴክኒካል የሆኑ ዘዴዎችን በመጠቀም የግለሰቦችን የባንክ አካውንት ወደ ቴሌ ብር በማስተላለፍ ወንጀሉ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

ፖሊስ አያይዞ እንደጠቀሰው ወንጀሉን ለመከላከል ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል የተለያዩ የማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ቢተላለፉም አሁንም ወንጀሉ እየተፈፀመ ሲሆን ግለሰቦች የማያውቋቸው የስልክ ጥሪዎች እና የጹሁፍ መልዕክቶች ሲደርሷቸው ተገቢውን ማጣራት ማድረግ እንደሚገባቸው እና ጥሪው እንደደረሳቸው ወደ ተግባር ከመግባታው በፊት አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ባንክ በመሔድ እውነታውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ፖሊስ መሰል ወንጀሎችን ለመቆጣጠር ከሚሰራው ሥራ ባሻገር አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ መረጃውን ለፀጥታ አካላት በመስጠት ህብረተሰቡ ተባባሪ እንዲሆንም ጥሪውን አስተላልፏል።

[አዲስ አበባ ፖሊስ]

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 17:20:34
ሱዳን ወደ ሁለት ሀገር የመገንጠል ስጋት እንዳንዣበበባት የወታደራዊ ቡድን መሪ ተናገሩ

ሱዳን ወደ ሁለት ሀገር የመገንጠል ስጋት እንዲኖርባት አደጋ የደቀነዉ ሀገሪቱን እየመራ ያለው ወታደራዊ መንግስት "ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ ባለመሆኑ " እና በስልጣን ላይ ለመቆየት ፍላጎት በማሳየቱ ነዉ ሲሉ የሱዳን ወታደራዊ ንቅናቄ መሪ ተናግረዋል::የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ጦር መሪ አብዱላዚዝ አል ሂሉ በካርቱም ያለው መንግስት ካልተቀየረ ቡድናቸው ነፃነቱን እንደሚመርጥ ተናግሯል።

የሱዳን ህዝቦች ነጻ አዉጪ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል ኑባ ተራሮችን እንዲሁም በደቡብ-ምስራቅ የብሉ ናይል ግዛትን ተቆጣጥሮ ይገኛል፡፡አል ሂሉ ቡድናቸው “አንድነትን ይመርጣል” ሆኖም ግን የካርቱም መንግስት የቀድሞዋን ሱዳን መርጦ ጭቆናን ማስቀጠል ከፈለገ “ነጻነትን እንመርጣለን” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ኑባዎች ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ተገልለው ቆይተዋል። ተገድለዋል፣ ተሰቃይተዋል፣ ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ መደረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡የሱዳን ጦር የእርስ በርስ ጦርነትን ለመከላከልና የፖለቲካ ቡድኖች ሰላማዊ ዜጎችን በፀጥታ ሃይሎች ላይ እያነሳሱ ነዉ በሚል ከዓመት በፊት የመንግስት ግልበጣ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ወደ ሲቪል አገዛዝ ለመሸጋገር ቁርጠኛ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ተናግረው ነበር።


Via:- ዳጉ ጆርናል
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
881 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ