Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0

የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-11-08 17:05:51
የአርቲስት አሊ ቢራ አስክሬን የትውልድ ቦታ በሆነች ድሬዳዋ ከተማ ደርሷል!

የክቡር ዶክተር አርቲስ አሊ ቢራ አስከሬን በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የእምነት አባቶች፣ የአርት ባለሙያዎች፣ የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት ሽኝት ከተደረገለት በኋላ ድሬደዋ ገብቷል።በአሁኑ ጊዜ አስክሬኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረሰ ሲሆን የድሬዳዋ ህዝብ፣ የእምነት አባቶች ለአርቲስቱን አስክሬን የክብር አቀባበል አድርገዋል።ከደቂቃዎች በኋላ የክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የቀብር ስነስርአት የሚፈጸም ይሆናል።

Via EPA
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
903 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:55 የዩክሬን የጦር መሳሪያ ክምችት እየተመናመነ እንደሆነ ተገለጸ

ምዕራባዊያን ደግሞ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መስጠት ሩሲያን የባሰ ጥቃት እንድትሰነዝር ሊያደርጋት ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተገልጿልhttps://am.al-ain.com/article/ukraine-weapon-is-dwindling
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
917 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:55
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን 9 አባላት ያሉት አዲስ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመት በዛሬው ዕለት አፅድቋል፡፡

በዚሁ መሰረት ምክር ቤቱ ብዝሃነትን እና የትምህርት ዝግጅትን መሰረት ያደረጉ ዕጩዎች ከቀረቡ በኋላ የስራ አመራር ቦርዱን ሹመት አፅደቋል፡፡

በዚሁ መሰረት
1. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የቦርድ ሰብሳቢ
2. አቶ መሳፍንት ተፈራ
3. ዶ/ር አብዱልዋሳ አብዱላሂ
4. አቶ ታረቀኝ ቡልቡልታ
5. አቶ ጃፋር በድሩ
6. ዶ/ር ንጉሴ ተፈራ
7. አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም
8. ወ/ሮ አመለወርቅ ህዝቅኤል
9. ዶ/ር ሙና አቡበክር የኢቢሲ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ሆነው ተሹመዋል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
805 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:55
ሹመት!

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለሶስት ተከታታይ ጊዜ በቦርድ በአባልነት በመሾም ብቸኛው ሆነዋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
710 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:55
ሹመት!

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የሆኑት ዶ/ር ለገሠ ቱሉ የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾመዋል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
674 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:54
ሹመት!

ዶክተር ምሕረት ደበበ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል፡፡ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት የዶክተር ምሕረትን የቦርድ ሰብሳቢነት ያጸቀደው ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 29፣ 2015 ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
652 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 15:59:54
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግል ተማሪዎች ክፍያን በእጥፍ መጨመሩ ቅሬታ አስነሳ!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለግል ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ላይ የ100 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ከተማሪዎች ቅሬታ ቀርቦበታል።

በዚህም ከፍተኛ ቅሬታ አድሮብናል ያሉት ተማሪዎቹ፣ በተለይ በዚህ ዓመት ለመማር እቅድ ይዘው የነበሩ አዲስ ተመዝጋቢዎች፣ የመግቢያ ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ የዋጋ ጭማሪውን ሲመለከቱ ብዙዎች ማቋረጣቸውን ተናግረዋል።

በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ኹለተኛ ዲግሪዋን ለመማር የተመዘገበች ተማሪ እንደገለጸችው፣ ተማሪዎች የመጀመሪያውን መግቢያ ፈተና 600 ብር ከፍለው ከተፈተኑ በኋላ፣ ያለፉት ኹለት ወር ገደማ ጠብቀው ለዲፓርትመንት መግቢያው ድጋሜ ከፍለው ይፈተናሉ።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
695 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 14:12:03 " ... ከጌታቸው ጨምሮ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ያ የተነገረው የድሮን ጥቃት የሚባለው ውሸት ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የተፈፀመ " የድሮን ጥቃት " የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።

ይህን የተናገሩት " የኢትዮጵያ ሚዲያ ሰርቪስ (ኢ ኤም ኤስ) " ለተባለና በኢንተርኔት ላይ ለሚሰራጭ ሚዲያ ነው።

" በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ አንዳንድ ክስተቶች ተፈጠሩ ሲባል መረጃ እንለዋወጣለን። ስምምነት ተፈራርመናል ስለዚህ የስልክ ችግር የለብንም። " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን በኬንያ ናይሮቢ ፤ ከእነ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ከወታደራዊ አዛዦቹም ጋር መነጋገራቸውን እና የድሮን ጥቃት ተፈፀመ የተባለው ውሸት መሆኑን  ገልፀዋል።

" #ስምምነት_ከመፈረሙ_በፊት የነበረ (incident) ክስተትን ከስምምነት በኃላም ለማምጣት የሚሞክሩ አሉ። በዚህ ግጭት ውስጥ ገንዘብ ይከፈላቸው የነበሩ ጥሩ ሃብት ያፈሩበት ሰዎች አሁንም ግጭት እንዲቀጥል የማቀጣጠል ፍላጎት ያላቸው እንዳሉ እናያለን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ፤ ከውስጥም በተለያየ መንገድ ስሜታዊ የሆነ ሰው ሊያራግበው ይችላል የትግራይ ሚዲያም ፤ የወያኔ ቴሌቪዥንም ሰርተውት ነበር" ብለዋል።

" በእኛ በኩል #ንግግሮችን ለማስተካከል ሞክረናል " ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን " አሁን ሰው ተስፋ እንዳያድርበት ወደፊትም ይሄን ነገር እንዲያመጣ ነው እንጂ ቁርሾውን በ 'Transitional Justice' በሂደት ይሄዳል ፣ በምህረት የሚታለፈው ይታለፋል መፀፀቱ ከታየ እውነት ከተናገረ ፤ የግድ በፍርድ ቤት ማለቅ ያለበት ከባድ ወንጀል የሆነ ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳል፣ ተጠያቂነትንም የማህበራዊ ህክምናንም ትስስርንም እኩል የሚያማክል መንገድ አለን እሱ ይደረሳል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ያልነበረ ነገር እያጋጋሉ የውሸት ሚፅፉ አሉ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ጌታቸውን ጨምሮ ያ የወጣው መግለጫ (የGSTS መግለጫ ማለታቸው ነው) የጋራቸው አቋም እንዳልሆነ፣  የተባለው የድሮን ጥቃትም ውሸት እንደሆነ አጣርቻለሁ " ብለዋል።

በስናይፐር ፣ በድሽቃ አልፎ አልፎ የተኩስ ልውውጥ ሊያጋጥም እንደሚችል የጠቆሙት አምባሳደሩ " ይሄ የተለመደ ነው፤ የሰላም ፊርማ ሲፈረም የተወሰኑ ቀናት እየሞተ እስከሚሄድ ድረስ የሰማም በስሜት ተውጦ እምቢ ብሎ ሊያደርገው ይችላል፣ ሳይሰማ የሚቀርም ያደርገዋል፤ ነገር ፈልጎ ነገሩ እንዲበላሽ  የሚፈልግም ሊያደርገው ይችላል በታንክ እና በመድፍ እንድካልሆነ ድረስ በድሽቃ እና በስናይፐሮች የሚደረግ አንዳንድ የተኩስ ምልልሶች እዚህም እዚያም ያጋጥማሉ " ሲሉ አስረድተዋል።

" ሰው ይሄንን (አንዳንድ ቦታዎች ላይ የሚያጋጥሙትን የተኩስ ልውውጦችን ማለታቸው ነው) ለመዘገብ የሚቸኩለውን ያህል ከTPLF ካምፕ ወደኛ ወታደር መጥቶ አብሮ በልቶ ፣ ... ፣ ተጫውቶ ፣ ፎቶ ተነስቶ የሚመለሰውን ለመዘገብ ፍላጎት የላቸውም እኛ ነን መግፋት ያለብን የሚል ነገር በሁለቱም በኩል አለ ካማንደሮቹ ይሄን ጉዳይ መልክ ካስያዙት በኃላ ሁሉ። የራሳቸውን Discipline ያሲዛሉ " ሲሉ ተደምጠዋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
839 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 14:12:02 " ... ከጌታቸው ጨምሮ ከራሳቸው ከTPLF ሰዎች አጣርቻለሁ ያ የተነገረው የድሮን ጥቃት የሚባለው ውሸት ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

759 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 14:12:02
#Tigray

ምናልባትም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ወይም በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ላይ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ ሊደረግ እንደሚችል የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ኤፒ አስነብቧል።

የህወሓት ተደራዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው የዕርዳታ አቅርቦት መቀላጠፍ በሰላም ንግግሩ እና ስምምነቱ ላይ እምነት እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የፖለቲካ ተደራዳሪዎች እና የጦር አመራሮች እየተካፈሉበት ያለው ትላንት በናይሮቢ የተጀመረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የሰላም ንግግር እስከ ረቡዕ ይዘልቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከአጀንዳዎቹ መካከል ፦

- የሰላም ስምምነቱን ሂደትና አፈፃፀም ስለመከታተል፣

- የህወሓት ኃይሎችን ትጥቅ ስለማስፈታት፣

- በትግራይ ክልል ለወራት ተቋርጦ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ስለማስቀጠል፣

- የመሠረታዊ አገልግሎቶች መልሶ ስለማስጀመር ይገኙበታል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
794 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ