Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 63

2022-07-16 15:39:44
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አስረከቡ።

በክፍለ ከተማው ወረዳ 6 የተገባው የጋራ መኖሪያ ቤት 29 አቅመ ደካማ ዜጎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 19 የሚደርሱት ህንፃው በተገነባበት ስፍራ ሲኖሩ የነበሩ ናቸዉ።

ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ ያለውን የቤት አቅርቦት ጥያቄ ለመመለስ በትጋት እየተስራ ይገኛል ብለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ አቅመ ደካማ ዜጎችን ለማገዝም ከተማ አስተዳደሩ ከበጎ ፈቃደኞችንና ባለሀብቶችን በማስተባበር መስራታችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት።ህንፃውን ገንብቶ ላስረከበው የአኢተዮጵያ ኮንስተራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበዋል ከንቲባዋ።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
712 views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 15:39:44
ከአመታዊ ብድሩ 15 ከመቶውን ለስራ ፈጣሪዎች ለማበደር ያቀደው አሐዱ ባንክ   በይፋ ዛሬ ስራውን ጀምሯል!

የብሔራዊ ባንክ ገዢ  ዶክተር  ይናገር ደሴ በተገኙበት     ቦሌ ፍላሚንጎ አካባቢ በሚገኘው   ዋና ቅርንጫፍ  የተከፈተው  ባንክ  564  ሚልየን  የተከፈለ ካፒታል ሲኖረው  10 ሺ ባለ አክስዮኖችም አሉት ተብሏል። እስከ መስከረም  ወር  ድረስ  50  ቅርንጫፎች በሀገሪቱ እከፍታለውም ብሏል።

የብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን  የመነሻ ካፒታል  አምስት ቢልየን ብርም በሶስት ዓመት ውስጥ አሟላለው ብሏል።


የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ዛሬ ከተናገሩት የተወሰደ

"ኢትዮጵያ ውስጥ ከባንክ የሚበደረው ሰው ብዛት ከ320 ሺ ሰው አይበልጥም"

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
813 views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 11:52:09
300 የሚጠጉ የኤርትራ ስደተኞች ያሉበት አልታወቀም ተባለ!

ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በስደተኞች ላይ በደረሰ ጉዳት ወደ 300 የሚጠጉ የኤርትራ ስደተኞች ገና ያሉበት አልታወቀም ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ፣ ባለፈው ኅዳር ወር ላይ በወጣው ጣምራ ምርመራ ግኝት በትግራይ ክልል የነበሩ ኤርትራውያን ጉዳት ማስተናገዳቸውን ተከትሎ፣ የተወሰኑት ወደመጡበት በግድ ሲመለሱ ሌሎች ደግሞ መበታተናቸውን አውስተው፣ ከዚያ ውስጥ 300 የሚጠጉት ያሉበት እንደማይታወቅ በሪፖርቱ ተገልጾ ነበር ብለዋል።

[Addis Maled]
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.2K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 11:52:09
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 5 ሺሕ 58 ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ፣በርቀት በማታ እና በክረምት ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው እያስመረቀ ያለው፡፡ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 1 ሺሕ 654 ሴቶች ሲሆኑ 3 ሺሕ 404 ደግሞ ወንድ መሆናቸው ታውቋል።ዩኒቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቀው ለ73ኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጣሰው ወልደሀና (ፕ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ተመራቂዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.1K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 08:40:05
ሩዋንዳ - ቤቲንግ

ሩዋንዳ በሁሉም የሀገር ውስጥ ጨዋታዎች ላይ የስፖርት ውርርድን (ቤቲንግ) ከዛሬ ጀምሮ እንዲታገድ አድርጋለች።

ውሳኔውን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመስማማት ነው ያሳለፉት።

የስፖርት ሚኒስቴር ፤ ሩዋንዳ ውስጥ ላሉ ለሁሉም የስፖርት ቤቲንግ እና የኦንላይን ጌሚንግ ድርጅቶች እንዳሳወቀው ሌላ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በሀገር ውስጥ ውድድሮች ውርርድ (ቤቲንግ) ከዛሬ ጀምሮ እንዲቆም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ኢንዱስትሪው በማች ፊክሲንግ / በእግር ኳስ አለም ውስጥ ለተቃራኒው ተገዝቶ የመስራት ውስልትና / ላይ ያለውን አደጋ የሚገመግም ሲሆን እስከዛው (ውርርድ) ቤቲንግ ታግዶ ይቆያል ተብሏል።

የሀገር ውስጥ ጨዋታ ሁሉንም ስፖርታዊ ውድድሮችን የሚመለከት ሲሆን የ1ኛ እና 2ኛ ዲቪዝዮን ሊግ እንዲሁም የወጣቶችን ውድድር የሚያካትት ነው።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.3K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 08:40:05
1.2K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:16:13
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።

ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።

ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ም/ ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።

የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውና ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰራተኞች በተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ለተለያዩ የሰራተኛ ተወካዮች ፣ የተመሰገኑ የስራ መሪዎችን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን ፤ የአየርመንገዱ ሰራተኞች የማህበሩን ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳን በማህበሩ ላስመዘገቡት ለውጥ ከፍተኛ ሽልማት እንዲሁም የአየር መንገዱን ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክቷል።

በሌላ በኩል ጉባኤው ታግዷል ፣ አተካሄደም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸትና አሉባልታ ናቸው ያለው ማህበሩ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ሲል ገልጿል።

(አብዲ ኩማ)

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
1.5K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:16:13
1.2K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:16:13
1.2K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 22:16:12
1.2K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ