Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-11-08 14:12:02
782 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:33
በሰላም ስምምነቱ መሰረት ፦

በኢትዮጵያ ውስጥ #አንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ይኖራል።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት መሰረት የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና ወደ ማኅበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀል የሚያስችል ዕቅድ ተነድፎ ተግባራዊ የሚሆንበትን ዝርዝር ይዘጋጃል።

ከስምምነቱ መፈረም በኃላ የመንግስት እና ህወሓት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ይነጋገራሉ (የጦር አመራሮች የስልክ ንግግር ማድረጋቸው መነገሩ ይታወቃል) ።

ስምምነቱ በተፈረመ በአምስት ቀናት ውስጥ በክልሉ ካለው ተጨባጭ ፀጥታ ሁኔታ በመነሳት ስብሰባ በማዘጋጀት የጦር አመራሮች የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ላይ ይነጋገራሉ ፤ ስለሂደቱም ዝርዝር ያወጣሉ። (ይህ ከሰኞ ቀን 28/2/2015 ጀምሮ በኬንያ፣ ናይሮቢ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ከህወሓት ጄነራል ታደሰ ወረደ በተገኙበት ተጀምሯል)

ከፍተኛ የጦር መኮንኖች #ከስምምነት ላይ ከደረሱ በኋላ ባሉት #አስር_ቀናት ውስጥ የከባድ መሳርያ ትጥቅ የመፍታቱ ሂደት #ይጠናቀቃል። የተቀመጠው አስር ቀናት ጊዜ ገደብ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በሚሰጡት ሀሳብ እና በሁለቱ ወገኖች አጽዳቂነት ሊራዘም ይችላል።

ከስምምነቱ በኋላ ባሉ 30 ቀናት ቀላል የጦር መሳርያዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል።

የህወሓት ታጣቂዎችን የማሰናበት እና መልሶ ወደ ማኅበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ሂደት የክልሉን ሕግ እና ፍላጎት መሠረት ያደርጋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
122 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:33
99 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:32
91 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:32
" ... ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ቅዳሜ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ የሰላም ስምምነት በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት " ህወሓት "ን ትጥቅ ስለማስፈታት እና በትግራይ ክልል ውስጥ ምርጫ ተከናውኖ የክልል መንግስት የሚመሰርተው አካል ክልሉን ለመጠበቅ መሳሪያ የመታጠቅ መብቱን በመጠቀም ረገድ ላይ ግርታ ሊኖር እንደማይገባ አስረድተዋል።

አምባሳዳር ሬድዋን በትግራይ በምርጫ ስልጣን የሚይዘው አካል ልክ እንደ ሌሎቹ ክልሎች በቂ የፀጥታ ኃይል እንደሚያደራጅ አረጋግጠዋል። 

መንግስት ህወሓት በሽብርተኝነት የተፈረጀበትን ድንጋጌ መልሶ እንዲመለከተው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብም አምባሳደር ሬድዋን ጠቁመዋል። 

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በተያያዘ የተናገሩት ፦

" ህወሓትን ትጥቅ ማስፈታት ብለን ስንናገር እና የትግራይ ክልል የፀጥታ ኃይል ያደራጃል ስንል ወዳጆቻችን ግርታ ሊገባቸው ይችላል።

ክልሎች የራሳቸው #የተመጠነ የፀጥታ ኃይል አላቸው ትግራይ ክልልም የክልሉን ግዛት እና ህዝቡን ለመጠበቅ በቂ የፖሊስ ኃይል፣ በቂ ልዩ ኃይል ፣ በቂ ሚሊሻ ይኖረዋል ከዚህ ጋር ነው መታየት ያለበት።  አሁንም ደግሜ የምለው ግን ይህ የሚሆነው ለትግራይ ክልላዊ መንግስት እንጂ ለአንድ የፖለቲካ ፓርቲ አይደለም። "

Credit : Journalist Solomon Muchie / ዶቼ ቨለ
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
90 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:31
76 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:31
" ... እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ህወሓትን በመወከል በፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ላይ የተሳተፉት እና በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ  ዛሬ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ከኬንያ ሆነው በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" ሰላም ህዝባችን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ነገር ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ "  የሕዝባችንን ጥቅም ለማስጠበቅ የገባውን ቃል ማክበር መቻላችን ጊዜ የሚፈታው ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ፅሁፍ ላይ ፤ " ወደ ጦርነት የገባነው ፈልገነው ሳይሆን እንደ ህዝብ ህልውናችን አደጋ ውስጥ በመግባቱ ነው" ብለው " የሰላም ስምምነት መፈረም የትግራይን ሕዝብ ሕልውና የሚያስጠብቅ ከሆነ ፣ #ለሰላም ለምን ዕድል አንሰጠውም ? " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ በናይሮቢ የተጀማረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የሰላም ንግግር (በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች መካከል) ተሳታፊ ናቸው ይኸው ውይይት ለቀጣይ ቀናት ይቀጥላል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
78 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:31
74 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:30
ፎቶ ፦ በግብፅ ፣ ሻርም አል-ሼይክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ከ100 በላይ የሀገራት መሪዎች እየተካፈሉ ነው።

ዶክተር ዐቢይ ፤ ከጉባኤው ጎን ለጎን  ከበርካታ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።

ከአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋርም በጋራ የትኩረት  ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ የምትጋራ ሲሆን፣  የመፍትሔዎች አንድ አካል ለመሆን  ቁርጠኛ ናት። " ብለዋል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
76 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-07 23:41:30
76 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ