Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-09 13:50:03
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም 2ኛው ምዕራፍ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ርዕሠ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፣  የባህል እና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመስገን ጥሩነህ ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ባለሀብቶች እና የስፖርት ቤተሠቦች የተገኙበት ነው።

የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ፣ ስታዲየሙ ሳይጠናቀቅም አገልግሎት እየሠጠ የሚገኝ ባለድል ስታዲየም መሆኑን ገልፀው፣ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአማካይ 40 ጨዋታዎችን ማስተናገዱን አንስተዋል።

ስታዲየሙ የካፍን ማሟያዎች ባለማሟላቱ ተጥሎበት የነበረውን እገዳ ማስነሳትን ጨምሮ ከጣራው ውጭ ሁሉንም የስታዲየሙ ቀሪ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ 1.1 እስከ 1.8 ቢሊየን ብር የሚጠይቀውን ግንባታ በክልሉ መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ትብብር የግንባታ ስምምነቱ የሚፈፀም መሆኑን ገልፀዋል።

የአማራ ክልል ለባህርዳር ስታዲየም ማጠናቀቂያ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ 300ሚሊየን ብር ተጨማሪ ድጋፍ ነው ግንባታው የተጀመረው።

52ሺ ሠዎችን የሚያስዲያስተናግደው ግዙፉ የባህርዳር ስታዲየም ግንባታ በ2002 ዓ.ም በ780 ሚሊየን ብር በጀት የተጀመረ ሲሆን ሳይጠናቀቅ በመቆየቱ ሁለተኛው ዙር ግንባታ በሜድሮክ ኮንስትራክሽን እና በኤም ኤች አማካሪ ድርጅት የሚከናወን ነው።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
938 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:50:03
860 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 13:50:03
የአማራ ክልል መንግስት ለባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ማጠናቀቂያ 700 ሚሊዮን ብር መደበ!

ዛሬ የማጠናቀቂያ ሥራው ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በተገኙበት እንደሚጀመር የአማራ ሚድያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ዘግቧል።
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
847 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 07:42:05
#ቤንሻንጉል!

ከአሶሳ ወደ ህዳሴ ግድብ መሄጃ በሲርባ ወረዳ በህዳሴ ግድብ ቃንቁር ካምፕ በሚባል የቤህነን አማፅያን  በወሰዱ እርምጃ ብያንስ 3 በላይ የፀጥታ ሃይሎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። አሶሳ ከተማ ከወትሮ በተለየ አኳሃን ቁጥራቸው ከነዋሪው በማይተናነስ ኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና የመከላከያ ሃይል ብዛት ተጨናንቃለች።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
366 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 07:42:05
የወልድያ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ደብዳቤ ፃፈ!

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር የከተማዋ አስፓልት መንገድ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት በአስቸኳይ እንዲጀመር ሲል ጠየቀ።

ከተማ አስተዳደሩ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሀገሪቱን የመንገድ አውታር ለማሻሻል በአዋጅ ቁጥር 80/1989 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከሚያሰራቸው መንገዶች መካከል የወልዲያ አስፓልት መንገድ ከሀገር ውስጥ ስራ ተቋራጭ ዉል በመግባት የግንባታ ሰራው ከ4 ዓመት በፊት ተጀምሮ በተቋራጩ ውስንነትና አካባቢው በወረራ በመያዙ ምክኒያት ስራው ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ መቆየቱ እንደሚታወቅ ገልጿል ።

ከወራ በኋለም ባቀረብነው ጥያቄ ስራውን የጀመረው ኮንትራክተር በነበረበት የአቅም ውስንነትና በሌሎችም ምክኒያቶች የስራ ውሉ ተቋርጦ ስራው ለሰሜን ሪጅን ኮምቦልቻ አካባቢ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽ/ቤት እንደተሰጠ ቢነገረንም እስካሁን ስራው አልተጀመረም ብሏል ።

ስራው በወቅቱ ባለመጀመሩም በአስፓልት ስራው መክኒያት ከይዞታቸው የተነሱ ባለይዞታዎች የካሳ ክፍያ ባለመጠናቀቁ ለችግር እየተዳረጉ መሆኑና አካባቢው ከፍተኛ የትራንስፖርት መዳረሻ በመሆኑ በዝናብ ወቅት ለጭቃ በበጋ ወቅት በሚፈጥረው አቧራ የከተማዋ ማህበረሰብ ለተለያዩ በሽታዎች እየተዳረገ መሆኑን በመጥቀስ ስራው ቅድሚያ ተሰጥቶት በአስቸኳይ እንዲጀመርልን ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርን ጠይቋል።

ለኢፊድሪ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስተር፣ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና መንገድ ቢሮም አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
351 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 20:46:37
የባህርዳር ስታዲየም የጣራ ማልበስ ስራ ሊጀመር ነው። ስታዲየሙ ሲጠናቀቅም ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀትና ውበት እንደሚጨምርላት ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
823 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 20:46:37
የድርድሩ ስምምነት ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በፓርላማው ለውይይት ጸድቆ እንዲቀርብ እናት ፓርቲ ጠየቀ!

ባለፈው ሳምንት አጋማሽ በመንግሥት እና በሕወሓት መካከል የተፈረመው ስምምነት ወደ ትግበራ ከመግባቱ በፊት በፓርላማው ለውይይት ጸድቆ አእንዲቀርብ እናት ፓርቲ የጠየቀው ዛሬ ጥቅምት 29፣ 2015 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ፓርቲው በመግለጫው በሁለት ፓርቲዎች መካከል የተደረገ ነው ባለው በድርድሩ ያልተወከሉና በጦርነቱ ቀጥተኛ ተጎጂ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ኢትዮጵያ አሸንፋለች” ብሎ ደጋግሞ በመናገር ለማሳመን ከመጣር ይልቅ የሚያመጣላቸውን በረከት፣ የሚያመጣባቸውን መዘዝ በተለይ የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆነውን ማኅበረሰብ በግልጽና በዝርዝር ቀርቦ ማናገር እንደሚያስፈልግ ገልጧል፡፡

ሁለት ዓመት ያስቆጠረውን የመንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት በሠላም ለመቋጨት የሚያስችለው የስምምነት ፊርማ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጥቅምት 23 በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ እንደተፈረመ ይታወቃል፡፡

የቀዳሚው ስምምነት አካል የሆነው ተከታይ ውይይት ትላንት ጥቅምት 28፣ 2015 በኬንያ ናይሮቢ በጦር ጀነራራች መካከል የተደረገ ሲሆን፣ ውይይቱ እስከ ነገ ረቡዕ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

ከሰሞኑ ከተደርጉ ስምምነቶች በኋላ የአገር መከላከያ ሠራዊት እና የሕወሓት ወታደሮች በአንዳንድ ቦታዎች በጋራ ምግብ አንደተመገቡ እንዲሁም የሞቱትን በጋራ መቅበራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን ተናግረዋል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
814 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 20:44:13 ዋይ-20ኤ" የተሰኘው ግዙፉ የቻይና ወታደራዊ አውሮኘላን

ዋይ - 20ኤ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ቤጂንግ ሰራሽ የጦር አውሮፕላን በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ሀገራት ድጋፍን አድርሷል።የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ መካሄድ ሲጀምርም ግዙፉ አውሮፕላን ለእይታ ቀርቧል።ቻይና በራሷ አቅም የሰራችው ግዙፍ አውሮፕላን ረጅም ክንፎቹን ዘርግቶ መብረር ጀምሯል።

የ2022 የቻይና የአየር ትርኢት በደቡባዊ የሀገሪቱ ከተማ ዡሃይ ከተማ ዛሬ ሲከፈት አውሮፕላኑ ትኩረትን ስቧል።ከ43 ሀገራት ከ740 በላይ ኩባንያዎች በትርኢቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።ከ100 በላይ አውሮፕላኖችም ለእይታ መቅረባቸው ነው የተነገረው።

በተለይ ቻይና ስሪት የሆነው "ዋይ - 20ኤ" ግዙፍ አውሮፕላን የበርካቶችን ቀልብ መሳቡ ተገልጿል።የዚህ አውሮፕላን ክንፎች ከዋናው የአውሮፕላን ክፍል ወይም ቦዲ በላይ የተሰራ ነው።ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱት ክንፎችም አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ መነሳትም ሆነ ማረፍ ያስችሉታል ተብሏል።

ፓኪስታን በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ነሃሴ ወር በጎርፍ አደጋ ስትጠቃ ይሄው ግዙፍ አውሮፕላን ከ3 ሺ በላይ ድንኳኖችን ጭኖ ጉዞ አድርጓል።በዚሁ አመት ሰኔ ወር ላይም አፍጋኒስታን በርዕደ መሬት ስትጠቃ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ነፍስ አድን ድጋፎችን አድርሷል "ዋይ - 20ኤ"።በቶንጋ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ በደረሰበት ወቅትም ከ30 ቶን በላይ የምግብና የመጠጥ ውሃ ድጋፎችን በማመላለስ የጭንቅ ጊዜ ደራሸ ሆኗል።

ቻይና በዚህ አውሮፕላን የቴክኖሎጂ እድገቷን እና ቀጣይ አቅሟን አሳይታበታለች።አንዳንዶች ስለ አዲሱ የቤጅንግ አውሮፕላን አድናቆታቸውን ለመግለፅ ቻይናውያን በአፈታሪክ ከሚጠቅሱት ግዙፍ ወፍ ጋር እያገናኙት ነው።ዋይ - 20ኤ" የቻይና መከላከያ ሃይል በትልቅ መሰረት ላይ መቀመጡንም ያሳያል የሚሉ ባለሙያዎች በርካታ ናቸው።

እስያዊቷ ሀገር ከምዕራባውያን በተለይ ከአሜሪካ ጋር በገባችው የንግድ ጦርነት ሊገጥማት የሚችለውን ፈተና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሷን ለመቻል የጀመረቻቸው ጥረቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ይነገራል።በዛሬው እለት የተጀመረው አለም አቀፍ ትርኢትም አዳዲስ ፈጠራዎቿን እንደምታስተዋውቅበት ይጠበቃል።

Via Al ain
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
696 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 20:44:13
545 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 20:44:13 ማሊ ሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በታጣቂዎች እጅ ዉስጥ ገብቷል መባሉን አስተባበለች

የማሊ ጦር ሃይሎች በነሀሴ ወር የፈረንሳይ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው ከወጡ በኋላ የሰሜን ምስራቅ ሜናካ ግዛት በአይ ኤስ ቡድን ታጣቂዎች እጅ ዉስጥ ወድቋል የሚለውን ዘገባ ውድቅ አድርጓል።"ይህ እውነት አይደለም እነዚህ የውሸት ወሬዎች የፕሮፓጋንዳ ሙከራዎች ዋንኛ ዓላማቸዉ የማሊ ታጣቂ ሀይሎችን ለማተራመስ ነዉ ፤ ሜናካ አልተከበበም” ሲሉ የማሊ ጦር ሀይሎች የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል ኮለኔል ሱለይማን ዴምቤሌ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ሰራዊቱ በተደጋጋሚ በክልሉ በመዘዋወር ጥበቃ እያደረገ እንደሚገኝ አክለዋል፡፡ ተናግረዋል። በጋኦ የሚገኙ የሰራተኛ ማህበራትን  እየጨመረ ያለውን የታጣቂዎች ጥቃት በመቃወም የማሊ ወታደራዊዉን መንግስት ጥቃቱን ማስቆም አልቻለም በሚል የሁለት ቀን የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እቅድ መያዛቸዉን ተከትሎ የማሊ ጦር ሀይሎች መግለጫ ለማዉጣት ተገዷል፡፡

በታጣቂዎቹ የተነሳ በማሊ ድንበራማ አካባቢዎች አፈና፣ የታጠቁ ወንበዴዎች ዝርፊያ  እና የእንስሳት ስርቆት በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል፡፡ታዋቂው የመንግስት ደጋፊ ሚሊሻ የኢምጋድ ቱዋሬግስ እና አጋሮቻቸው ማሊ የሚገኙ የቱዋሬግ ማህበረሰብ አባላት እና አጎራባች ሀገራት አይኤስን በመዉጋት እንዲተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የቱዋሬግ ሚሊሻዎች ከመጋቢት ወር አንስቶ በሜናካ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን በጅምላ ገድሏል ከተባለዉ የአይ ኤስ ቡድን ጋር በመዋጋት ግንባር ላይ ይገኛሉ።


Via:- ዳጉ ጆርናል
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
632 views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ