Get Mystery Box with random crypto!

Bekulu Entertainment

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment B
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio27info — Bekulu Entertainment
የሰርጥ አድራሻ: @ethio27info
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.54K
የሰርጥ መግለጫ

ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-12 22:06:10
212 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:10
203 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:09
በኬኒያ ናይሮቢ የተከናወነው የፊርማ ስነስርዓት ሙሉ ፕሮግራም።

ስምምነቱን አስመልክቶ የተሰጠው መግለጫ፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጄ/ል ታደሰ ወረደ ያደረጉት ንግግር፣ ዋና አደራዳሪዎቹ ኦባሳንጆ እና ኡሁሩ ስለ ድርድሩ ሂደት እና ሁለቱ የጦር አዛዦች ምን አሉ።

ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ያስተላለፉት መልዕክት፣ እንዲሁም ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ።

#ሼር
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
203 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:09
የኢትዮጵያ መንግሥት እና የሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች በናይሮቢ ሲያካሂዱት የቆዩትን ውይይትን በስምምነት አጠናቀዋል።

የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሄኑ ጁላ እና የሕወሃት ኃይሎች ዋና አዛዥ ጀኔራል ታደሠ ወረደ ሁለቱ ወገኖች የደረሱበትን የጋራ መግለጫ ስምምነት ዛሬ ማምሻውን ፈርመዋል።

ሁለቱ ወገኖች የደረሱበትን ስምምነት በማስመልከትም አጭር የጋራ ፕሬስ መግለጫ በጽሀፍ ተነቧል።

የጋራ መግለጫ ስምምነቱ አንኳር ጉዳዮች፣ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እና አጎራባች ክልሎች ያለ ገደብ እንዲገባና የረድዔት ሠራተኞች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና የሕወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱባት ሁኔታ ላይ በቀጣይ ለመነጋገር የሁለቱ ወገኖች ወታደራዊ አካላት የጋራ ኮሚቴ ለማቋቋም መስማማታቸው እንደሆኑ ተገልጧል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
209 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:09
የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በተታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው።

በዚህም መሠረት በመከላከያ ሥር ወዳለው አብዛኛውየትግራይ አካባቢ ርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ነው።

ወደተለቀቁት አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እየተጀመሩ ነው።

በሌሎች አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንዲቻል በታጣቂዎች የወደሙመሠረተ ልማቶችን ለመጠገን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢመክረዋል።

በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል።

ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል። ለዕቅዱተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መንግሥት ያሳስባል።

Via FBC
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
262 views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 15:46:41
ነገ በመዲናዋ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ!!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ አደረገ፡፡

በነገው ዕለት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የነገው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
• ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
• ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
• ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከአፍሪካ ህብረት ወደ ቡልጋሪያ
• ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
• ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
• ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
• ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
• ከሐራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል
• ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
• ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
883 views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 15:46:41
የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅትን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
745 views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:26:53
" ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን "

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፦

" በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የቆዩት ግጭቶች #በሰላማዊ_መንገድ የመጨረሻ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ በተደራጀ ኃይል ውስጥ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደማህበረሰቡ በዘላቂነት እንዲቀላቀሉና ሰላማዊ ኑሮ መምራት እንዲችሉ ለማድረግ፣ በአገሪቱ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲሳተፉ ለማስቻል ብሔራዊ የተሃድሶ ኮሚሽን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለም/ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ "

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
826 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:26:53
712 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 14:26:53 ነገ በአዲስ አበባ የሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች


በነገው ዕለት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

ከዚህ ቀደም በርካታ ህዝብ በብዛት የተሳተፈባቸው ተመሳሳይ ሩጫዎች በሰላም መጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የነገው የጎዳና ላይ ሩጫም ውድድር በሰላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
 
የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራ ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ውድድሩ ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ፡-
• ከቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን  ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአጎና ሲኒማ  ወደ መስቀል አደባባይ
• በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
• ከዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
• ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
• ከትንባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
• ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
• ከልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
• ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
• ከሐራምቤ ሆቴል  ወደ መስቀል
• ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
• ከካዛኝቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በውድድር መስመር ግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info
675 views11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ