Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-13 11:47:42 ኮርፖሬሽኑ ገበያ የማረጋጊያ ምርቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገበያ ለማረጋጋት የሚያግዙ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ወቅቱ በዓላት ተከታትለው የሚመጡበት እንደመሆኑ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

በኮርፖሬሽኑ እየተሰራጩ ከሚገኙት የፍጆታ ምርቶች መካከል ፓልም የምግብ ዘይት አንዱ ሲሆን የ5.5 ሚሊየን ሊትር ግዥ ተፈጽሞ ከጅቡቲ በባቡር ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለበአል ፍጆታ የሚውል 2.2 ሚሊየን ሊትር ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ነው፡፡ የምግብ ዘይቱ በተለያየ መጠን የቀረበ ሲሆን ባለ ሶስት ሊትር በብር 324፣ ባለ አምስት ሊትር በብር 526 እና ባለ ሃያ ሊትር በብር 2064 በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ባለ አምስት ሊትር ፈሳሽ የሱፍ ዘይት በ930 ብር ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል የስንዴ ዱቄት በ5፣ 10 እና 50 ኪሎ አማራጭ ለገበያ የቀረበ ሲሆን ባለ አምስት ኪሎ በኪ.ግ 73.29 ብር፣ ባለ አስር ኪሎ በኪ.ግ 73 ብር እና ባለ ሃምሳ ኪሎ በኪ.ግ 70.92 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ስኳር በኪ.ግ በብር 62.62 እየቀረበ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 57,408.4 ኩንታል ጤፍ በአማካኝ አንድ ኩንታል በብር 4832.53 ለህብረተሰቡ ያቀረበ ሲሆን ይህም በነጻ ገበያው በኩንታል በብር 5,128 ከተሸጠበት አማካኝ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የብር 294.98 ቅናሽ አለው፡፡ በተመሳሳይ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1,550,522.48 ኩንታል ስንዴ ለህብረተሰቡ የተሰራጨ ሲሆን አማካኝ ዋጋው በኩንታል 2,978.85 ነበር፡፡ ይህም በነጻ ገበያ ከቀረበበት የ4,211 ብር አማካኝ ዋጋ ጋር ሲነጸጸር የ 1,232.59 ቅናሽ አለው፡፡

በተመሳሳይ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በመሰራጨት ላይ ሲሆን ለበዓል ፍጆታ የሚውል የሽንኩርት ምርትም ለገበያ ቀርቧል፡፡
290 views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 15:36:24 የውስጥ ዕድገት/ዝውውር ማስታወቂያ
418 views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 08:54:49
448 views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 16:09:57 እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ አለን!

አዳዲስና ዘመናዊ አሰራር ለዘረጉ፣ የላቀና ተጨባጭ እድገት ላስመዘገቡ፣ መልካም ስማቸውን ጠብቀው ለአመታት በትጋት ለዘለቁ ተቋማት /MILESTONE, BRANDING AND REPUTATION/ አቢሲኒያ የጥራት ድርጅት እውቅና ለመስጠት ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ/ም በኢንተርሊግዠሪ ሆቴል (በቀድሞ ኢንተርኮንቲኔታል ሆቴል) ባዘጋጀው የኢንደስትሪ ሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ ዘርፍ /ኢትፍሩት/ የከፍተኛ ክብር ሽልማት የወርቅ ዋንጫ፣ የወርቅ ሜዳሊያና የከፍተኛ ክብር ዲፕሎማ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ለዘርፉ ስራ አርዓያ የሆኑ አምስት ምርጥ ሰራተኞች የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት ሲሸለሙ፣ የመካከለኛ ደረጃ ሁለት አመራሮች ደግሞ የኒሻን ተሸላሚ ሆነዋል፤ እንዲሁም የዘርፉ ስራ አስፈጻሚ የከፍተኛ ክብር (የኮርዶን) ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

ይህ በሀገራችን በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተካሄደ የመጀመሪያው የሽልማት መርሀ ግብር ሲሆን ከ57ሺህ የኢንዱስትሪ ተቋማት የተመረጡት 50 ብቻ ሲሆኑ በአጠቃላይ ተቋማዊ ውጤታቸው ላይ ከ2009-2014 በተደረገ ውጫዊ ምዘና በ24 መሰረታዊ መለኪያዎች ላይ ተመስርቶ በተገኘ ውጤት እንዲመረጡና እንዲሸለሙ መደረጉን በሽልማት መርሃ -ግብሩ ወቅት ተገልጿል፡፡
በዚህ የሽልማት ፕሮግራም ላይ የኮርፖሬሽኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሃሰን መሃመድ፣ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ እና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም በዘርፉ ጥሪ የተደረገላቸው የዘርፉ ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

ዘርፉ ይህንን ከፍተኛ ሽልማት ያገኘው በኮርፖሬሽኑ የስራ አመራር ቦርድ እና የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት በሚሰጠው ስትራቴጂካዊ አመራር በመመራት፣ የዘርፉ ማናጅመንትና ሠራተኞች ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ባደረጉት እገዛና ድጋፍ በመሆኑ ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ፤ ደስ አለን እያለ፣ ዘርፉ ይህንን ስኬት እንዲያስመዘግብ ድጋፍና እገዛ ላደረጉ የኮርፖሬሽኑ ቤተሰቦችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ስራ ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት ትኩስና ጥራታቸውን የጠበቁ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
519 views13:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 16:05:37
249 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 16:05:31 በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ

ድሎችን የማጽናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልእኮ በሚል በመንግስት በተዘጋጀ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት እና በሁሉም ንግድ ሥራ ዘርፍ ያሉ አመራርና ሰራተኞች መጋቢት 29/ 2015 ዓ.ም ውይይት አካሄዱ፡፡

በኮርፖሬሽኑ ለዋና መ/ቤትና ለእህልና ቡና ን/ሥ/ ዘርፍ አመራርና ሰራተኞች በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተገኙትና ውይይቱን የመሩት አቶ ቀጸላ ሸዋረጋ በኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የውይይት መድረኩ ዓላማ ወቅታዊውን ሃገራዊ ሁኔታ በመረዳት አመራሩና ሰራተኛው የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም እንደ ኮርፖሬሽን የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በሚገባ በመወጣት ለሃገር ያለንን አስተዋጽኦ እንዲታወቅ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በመንግስት የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ ትእዛዙ ኃ/ጊዮርጊስ የአሰራር ዘዴና አገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በገለጻቸው የለውጡ መንግስት በርካታ ስኬቶችን ማምጣቱን ጠቅሰው በአንጻሩ ለውጡ ዛሬም በውስጥና በውጭ እንቅፋቶችና ተግዳሮቶች የተሞላ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም ያጋጠሙ ፈተናዎችና አንድምታቸው እንዲሁም ፈተናዎችን ለመሻገር ቀጣይ አቅጣጫዎች በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የቀረበውን ሰነድ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች በሰራተኞች ተሰንዝረዋል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽ ለመስጠት የተሞከረ ሲሆን የተነሱ ጉዳዮች ተደራጅተው መንግስት እንዲያውቀው እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ አቶ ቀጸላ መድረኩ ጠቃሚ ውይይት የተካሄደበት እንደነበር ጠቁመው የተነሱ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት ተናግረው እንደ ኮርፖሬሽንም ራሳችንን ማየት ይገባናል ብለዋል፡፡ የተሰጠንን ተልእኮ ስንወጣ መንግስት ለተቋማችን የሚኖረው እይታ ይቀየራል ያሉት ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ የበጀት ዓመቱን ለማጠናቀቅ በቀሩት ሶስት ወራት ወጪና ጊዜ ቆጣቢ አሰራር በመከተል በተለይም ገበያ ከማረጋጋት አኳያ እየተሰራ ያለውን ሰፊ ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
254 views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:50:57
257 views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 14:08:53 የደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ
290 views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 15:36:24 የአትክልትና ፍራፍሬ እና የፍጆታ እቃዎች ሥርጭት ባለፉት ስምንት ወራት

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ 110 ሺህ ኩንታል የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ለህብረተሰቡ አቅርቧል፡፡ ከተሰራጩት ምርቶች መካከል ፍራፍሬ 37,275 ኩንታል፣ አትክልት 1,707 ኩንታል፣ የፋብሪካ ምርት 967 ኩንታል እና ስኳር 24,358 ኩንታል ይገኙበታል፡፡

ፍራፍሬ በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ40-50%፣ አትክልት በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ10-20% እንዲሁም የፋብሪካ ምርት (ቲማቲም ድልህ 850 ግራምና 1000 ግራም ብርቱኳን ማርማላት) በአማካኝ ዋጋ ከነጻ ገበያው ከ15-20% ቅናሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

በስምንት ወሩ ውስጥ 24,358 ኩንታል ስኳር ከንግድ ቢሮ ትስስር ለተፈጠረላቸው አገልግሎት ሰጪዎችና ተቋማት (ሆስፒታሎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ማረሚያ ቤቶች) እንዲሁም ባለኮኮብ ሆቴሎች መንግስት ባስቀመጠው ዋጋ ማሰራጨት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ በስምንት ወራት ውስጥ 141 ሺህ ኩንታል የፍጆታ እቃዎች ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ሸቀጦች 29,509 ኩንታል፣ የታሸጉ ምግቦች 8,575 ኩንታል፣ የቤት ንፅህና መጠበቂያዎች 8,392 ኩንታል፣ የግል ንፅህና መጠበቂያዎች 5,409 ኩንታል እና ስኳር 27,500 ኩንታል በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡
252 views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 15:49:55 ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ስምንት ወራት 2.48 ሚሊዮን ኩንታል ምርት አሰራጨ

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት እስከ የካቲት ወር በአጠቃላይ በስምንት ወራት ውስጥ 1.87 ሚሊዮን ኩንታል እህል፣ ቡና፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የፍጆታ ዕቃዎች ለመግዛት አቅዶ የነበረ ሲሆን 1.33 ሚሊዮን ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን 71 በመቶ ማከናወን ችሏል፡፡

በስምንት ወራት ውስጥ በአጠቃላይ በሀገር ውስጥና በውጭ ገበያ ኮርፖሬሽኑ 2.52 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሸጥ አቅዶ 2.48 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወይም የዕቅዱን 98 በመቶ በመፈጸም ለገበያ ሲያቀርብ በሀገር ውስጥ ብቻ ለመሸጥ ያቀዳቸዉ ልዩ ልዩ ምርቶች መጠን 2.09 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን ለገበያ ያቀረበው ግን 2.22 ሚሊዮን ኩንታል ወይም የዕቅዱን 106 በመቶ ነው፡፡

ለገበያ ከቀረቡት ውስጥ በዋነኛነት 33,371 ኩንታል ጤፍ፣ 1,408,468 ኩንታል የገበያ ማረጋጊያ ስንዴ፣ 11,786,706 ሊትር የምግብ ዘይት እንዲሁም 573,364 ኩንታል ሲሚንቶ የሚገኙበት ሲሆን ምርቶቹን ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ገበያ ለማረጋጋት ጥረት ተደርጓል፡፡
375 viewsedited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ