Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑ ገበያ የማረጋጊያ ምርቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ኮርፖሬሽኑ ገበያ የማረጋጊያ ምርቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገበያ ለማረጋጋት የሚያግዙ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ወቅቱ በዓላት ተከታትለው የሚመጡበት እንደመሆኑ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

በኮርፖሬሽኑ እየተሰራጩ ከሚገኙት የፍጆታ ምርቶች መካከል ፓልም የምግብ ዘይት አንዱ ሲሆን የ5.5 ሚሊየን ሊትር ግዥ ተፈጽሞ ከጅቡቲ በባቡር ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለበአል ፍጆታ የሚውል 2.2 ሚሊየን ሊትር ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ነው፡፡ የምግብ ዘይቱ በተለያየ መጠን የቀረበ ሲሆን ባለ ሶስት ሊትር በብር 324፣ ባለ አምስት ሊትር በብር 526 እና ባለ ሃያ ሊትር በብር 2064 በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ባለ አምስት ሊትር ፈሳሽ የሱፍ ዘይት በ930 ብር ለሽያጭ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል የስንዴ ዱቄት በ5፣ 10 እና 50 ኪሎ አማራጭ ለገበያ የቀረበ ሲሆን ባለ አምስት ኪሎ በኪ.ግ 73.29 ብር፣ ባለ አስር ኪሎ በኪ.ግ 73 ብር እና ባለ ሃምሳ ኪሎ በኪ.ግ 70.92 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ስኳር በኪ.ግ በብር 62.62 እየቀረበ ይገኛል፡፡

በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 57,408.4 ኩንታል ጤፍ በአማካኝ አንድ ኩንታል በብር 4832.53 ለህብረተሰቡ ያቀረበ ሲሆን ይህም በነጻ ገበያው በኩንታል በብር 5,128 ከተሸጠበት አማካኝ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የብር 294.98 ቅናሽ አለው፡፡ በተመሳሳይ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1,550,522.48 ኩንታል ስንዴ ለህብረተሰቡ የተሰራጨ ሲሆን አማካኝ ዋጋው በኩንታል 2,978.85 ነበር፡፡ ይህም በነጻ ገበያ ከቀረበበት የ4,211 ብር አማካኝ ዋጋ ጋር ሲነጸጸር የ 1,232.59 ቅናሽ አለው፡፡

በተመሳሳይ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በመሰራጨት ላይ ሲሆን ለበዓል ፍጆታ የሚውል የሽንኩርት ምርትም ለገበያ ቀርቧል፡፡