Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-29 11:47:57
559 views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 16:12:09
619 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 15:24:28
የጨረታ ማስታወቂያ (መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም.)
702 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 12:02:07
የኮርፖሬሽኑ ሴት ሰራተኞች በአንድነት ፓርክ ጉብኝት አካሄዱ
በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከአራቱም ዘርፎችና ከዋና መ/ቤት የተውጣጡ ሴት ሰራተኞች በቅርቡ የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በአንድነት ፓርክ መጋቢት 15/ 2015 ዓ.ም ጉብኝት አካሄዱ፡፡
ጉብኝቱን ያዘጋጀውና ያስተባበረው የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትግስት አለማየሁ ከየዘርፉና ከዋና መ/ቤት የተወከሉ ሴት ሰራተኞች በጉብኝቱ መሳተፋቸውን ገልጸው በስራቸው የበለጠ ውጤታማ እና ጠንካራ እንዲሆኑ ለማገዝ በጽ/ ቤቱ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም ኮርፖሬሽኑ የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በጉብኝት እያከበረ መሆኑን ጠቅሰው ይህም በየዘርፉና በዋና መ/ቤት ያሉ ሴት ሰራተኞችን እርስ በርስ ለማስተዋወቅና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉና ያነጋገርናቸው ሰራተኞች በአንድነት ፓርክ በመገኘት የሀገራቸውን ታሪክና የተፈጥሮ ሃብት በመመልከታቸውና በአጠቃላይ በጉብኝቱ መዘጋጀት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
822 views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-22 14:10:57
351 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 14:35:06 የውስጥ ዕድገት/ዝውውር ማስታወቂያ
395 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-14 14:34:09
ክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ
395 views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 15:24:09 ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ሰባት ወራት 2.27 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለገበያ አቀረበ

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ሰባት ወራት በሀገር ውስጥና በውጭ ገበያ ለመሸጥ ካቀደው 2.29 ሚሊዮን ኩንታል የእህልና ቡና፣ የፍጆታ ዕቃ እና የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት 2.27 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወይም የዕቅዱን 99 በመቶ ለገበያ አቀረበ፡፡ በተለይም በሀገር ውስጥ ለመሸጥ ያቀዳቸዉ ልዩ ልዩ ሸቀጦች መጠን 1.69 ሚሊዮን ኩንታል ሲሆን በዚህ ወቅት መሸጥ የተቻለው 2.05 ሚሊዮን ኩንታል ወይም የዕቅዱን 107 በመቶ እንደሆነ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ኮርፖሬሽኑ 1.23 ሚሊዮን ኩንታል እህልና ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ፍጆታ ዕቃዎች ከሀገር ውስጥ አምራቾች ለመግዛት አቅዶ 944 ሺህ ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን 77 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የአቅርቦትና የግብይት ችግር የሚስተዋልባቸውና በአጭር ጊዜ የሚበላሹ የግብርና ምርቶች በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 211 የመገበያያ ማዕከላት ምርቶችን ከአምራቹ በቀጥታ በመግዛት ለሸማቹ እያቀረበ ይገኛል፡፡ እስከ 900 ኪሎሜትር ርቀት በመጓዝ ከፍተኛ የግብርና ምርት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች ለአምራቹ ተገቢውን ዋጋ ሰጥቶ በመግዛት የምርት እጥረት ወደ አለባቸው አካባቢዎች በማጓጓዝ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ያቀርባል፡፡ ይህም በመደረጉ አምራቾች በገበያ እጥረት ምክንያት ምርታቸው እንዳይበላሽና ባመረቱት ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትልቅ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ሸማቹ ህብረተሰብንም ከመደበኛ ገበያው የዋጋ ቅናሽ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችችን በመቀላቀልና ድረገጻችን በመጎብኘት የምርትና አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉና በፍጥነት ያግኙ!

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/etbcofficial
ቴሌግራም፡- https://t.me/etbcinfo
ዜና ኢንሥኮ አንድሮይድ መተግበሪያ፡- https://t.ly/DiXR
ዩትዩብ ቻነል፡- https://www.youtube.com/@etbcinfocom4858
አስተያየትዎን በኢሜይል አድራሻችን etbcinfo@etbc-ethiopia.com ያድርሱን፡፡
ኮርፖሬት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
755 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 15:23:52
600 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:45:42
674 viewsedited  12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ