Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-11-21 15:43:08
የፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራ ዘርፍ በ 2014 በጀት ዓመት ውጤታማ መሆኑን በማስመልከት የምስጋና መርሃ-ግብር አዘጋጀ

በኮርፖሬሽኑ የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ በ2014 በጀት ዓመት ባስመዘገው ውጤትና ትርፍ አስተዋጽኦ ላደረጉ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ/ም የምስጋናና የምሳ ግብዣ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡

የምስጋና መርሃ ግብሩን አስመልክተው አቶ ተውፊቅ ይመር የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ ባደረጉት ንግግር 2014 ዓ/ም ለዘርፉ የስኬት ዓመት እንደነበር ገልጸው፣ ለስኬቱ መገኘት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠራተኞችን በማመስገን ለተገኘው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጤታማ ከሆኑ ዘርፎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይህ የሆነው በኮርፖሬሽኑ ድጋፍ፣ በዘርፉ አመራርና ሠራተኞች የጋራ ርብርብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ከተሠራ፣ ጥረት ከተደረገ ውጤት እንደሚመጣ ዘርፉ አሳይቶናል ብለዋል፡፡ የተገኘው ውጤት በ12015 በጀት ዓመትም እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ በቀድሞው ስሙ የኢትዮጵያ የንግድ ድርጅት (አለ በጅምላ) ሲመሰረት ለሥራ ማስኬጃና ለንግድ ሥራው ከባንክ የተበደረውን 596 ሚሊየን ብር ዕዳ ይዞ ኮርፖሬሽኑን የተቀላቀለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያለበትን ብድር ከወለድ ጋር እስከ መስከረም 30/ 2015 ዓ/ም ብቻ 621 ሚሊየን ብር ከፍሏል፡፡ የንግድ ሥራ ዘርፉ በአመራሩና በሠራተኛው ጠንካራ ጥረት ያለበትን እዳ እየከፈለና የመነገጃ ካፒታል እጥረት ተቋቁሞ ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የፍጆታ ሸቀጦችን በማቅረብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብር 108 ሚሊየን 147 ሺ 527 ብር ትርፍ አግኝቷል፡፡
621 views12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 16:08:04
ለእህል ጥራት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተመለከተ

የእህል ጥራትን ማስጠበቅ ዓላማው ያደረገ ስልጠና ከህዳር 07-09/ 2015 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በውስጥ አቅም በኮርፖሬሽኑ የእህል ጥራትና ቁጥጥር እና የክምችት እንክብካቤ ቡድን እየተሰጠ ሲሆን 90 በእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ የሚገኙ የምርት ጥራት ባለሙያዎች እንዲሁም የግብይትና ክምችት ሰራተኞች ስልጠናውን በመካፈል ላይ ናቸው፡፡

በስልጠናው ለእህል ግዢ ጥራት ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን እህል በሚገዛበት ወቅት የደንበኞችን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ መስፈርቱን የማያሟላ ምርት ግዢ መፈጸም እንደሌለበትም አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ በስልጠናው መድረክ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ማቅረብ ኮርፖሬሽኑ የተቋቋመበት ተልእኮ መሆኑን አስታውሰው፣ ለዚህም ጥራትን ማእከል ያደረገ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን እንደሚከተል ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም የደንበኛን ፍላጎት ለማርካት በግዢ፣ በአጫጫን፣ በአያያዝ፣ በአከመቻቸትና በሽያጭ ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም ዋጋ፣ ጥራትና ተደራሽነት ታሳቢ በማድረግ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ባለሙያዎች የእህል ምርትን ለማስጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ ስልጠናው መነሻ በመሆኑ የጎደለውን በመሙላት ባለው አቅም ሁሉ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ህዳር 09/ 2015 ዓ.ም በኮርፖሬሽኑ የእህል ማከማቻና ማደራጃ ማእከል የተግባር ላይ ስልጠና በማካሄድ ይጠናቀቃል፡፡
374 views13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 10:04:18 የደረጃ ዕድገት (ዝውውር) ማስታወቂያ
447 views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 14:43:55
495 views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 16:03:16
ለምርት ጥራት፣ ክምችትና ክብካቤ ባለሙዎች ሥልጠና ተሰጠ

ምርትን ከተባይ ለመከላከል እንዲያስችል በእህል እጥነት (fumigation) ዙሪያ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጠ፡፡ ሥልጠናውን ያዘጋጀው በኮርፖሬሽኑ የሰው ኃብት ልማትና ሥራ አፈጻጸም አመራር ቡድን ሲሆን ስልጠናውን የሰጠው ደግሞ ኬምቴክስ ኃ/የተ/የግል ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተባይ ማጥፊያ ኬሚካል አቅራቢ ነው፡፡

በሥልጠናው የመጋዘን ተባዮችና አያያዝን ጨምሮ ሌሎች ርእሰ ጉዳዮች የተካተቱ ሲሆን ከሁሉም ክልል ግብይት ማዕከላት፣ ከኮርፖሬሽኑ የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና ከዋናው መ/ቤት የተውጣጡ የእህልና ቡና የምርት ጥራት ክምችትና ክብካቤ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ የሥልጠናው ዓላማ የእህል ክምችትን የመንከባከብ ሥራን በአግባቡ ለማከናወን እንዲቻል እንዲሁም ምርት ሳይባክንና ሳይጎዳ ጥራቱን እንደጠበቀ ለማቆየት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ ሰልጣኞች የተለያዩ ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን ለእህል ጥራት ሥራቸው አጋዥ ሥልጠና ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናውን ሲያስተባብሩ የነበሩት አቶ ጌታቸው ይመር የሰው ኃብት ልማትና ሥራ አፈጻጸም አመራር ቡድን መሪ ባስተላለፉት መልእክት ሠልጣኞች ያገኙትን ዕውቀት ተግባር ላይ እንዲያውሉና ከስራቸው ያሉ ባለሙያዎችን እንዲያበቁ አደራ ብለዋል፡፡
531 views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 10:08:13 ማስታወቂያ

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሲሚንቶ ሽያጭ ፕሮግራም መስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል:: ሆኖም በአሁኑ ሰዓት ከፋብሪካ የምናገኘው የሲሚንቶ መጠን በጣም አነስተኛ በመሆኑ የደንበኞችን ፍላጎት መሟላት አልተቻለም፡፡ ለዛሬ ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ/ም የሚስተናገዱ ደንበኞች በተረከብነው የሲሚንቶ መጠን ከዚህ በታች ተገለፀ ሲሆን፤ በቀጣይ የሚስተናገዱ ደንበኞች ከቆምንብት ማለትም ከንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ተመዝግበውና ፋይል አስገብተው ከሚጠባበቁ ደንበኞች የምንቀጥል ይሆናል፡፡ ስለሆነም ማስታወቂያውን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ እና በማስታወቂያ ሰሌዳ እንድትከታተሉ በማክበር እንገልጻለን፡፡

06 03 2015 ዓ/ም ሽያጭ የሚከናወንላቸው ደንበኞች ስም ዝርዝር

456 ያሬድ መለሠ
457 ረህሚም አልአዛር (መሀመድ ሁሴን)
458 ሰላም መንግስቱ
459 ፊቬን ሳህሌ
460 ሙሉጌታ ዘርጋው
461 ሰናይት ቢፋ
462 ወንደሰን ብርቅነህ
463 ዘነቡ አምዴ
464 ፋሲል ሙላቱ
465 ሙህዲን ጀማል
509 viewsedited  07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:12:36
296 views08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 09:37:55 የሀሰት ሰነድ በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል በፈጸሙ ሠራተኞች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

በእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ የደብረማርቆስ ግብይት ማዕከል ኃላፊና ሠራተኞች በሀሰት የተዘጋጀ ሰነድን ህጋዊ ማስረጃ በማስመሰል ህጋዊ ላልሆኑ ሸማች ማህበራት መጠኑ 236.62 ኩንታል በቆሎ በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው በማስረጃ በመረጋገጡ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው፡፡

የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አስፈላጊውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማደራጀት ለምዕራብ ጎጃም ፖሊስ የሙስና ወንጀል ምርመራ መምሪያ አቅርቧል፡፡ የሙስና ወንጀል ምርመራ መምሪያውም በቀረበለት ማስረጃዎች መሠረት አስፈላጊውን የምርመራ ሥራ አጠናቆ ግለሰቦቹ በህግ እንዲጠየቁ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ዓቃቢ ሕግ አቅርቧል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድ ቤቱ ሲታይ ቆይቶ ነሐሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ የውብዳር ታከለ እና 2ኛ ተከሳሽ አቶ ጎራው ደሳለኝ እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ሲቀጡ፤ 3ኛ ተከሳሽ አቶ መስፍን ንጋቱ በ3 ዓመት ከ7 ወር እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በተከሰሱበት የፍትሐብሔር መዝገብም በአማ/ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደብረማርቆስ ተዘዋዋሪ ችሎት ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በክሱ መሠረት በጋራ ብር 688,632 ለኮርፖሬሽኑ እንዲከፍሉ መወሰኑን የኮርፖሬት ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡
312 views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 10:43:42
220 views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-08 14:33:54
327 views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ