Get Mystery Box with random crypto!

የፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራ ዘርፍ በ 2014 በጀት ዓመት ውጤታማ መሆኑን በማስመልከት የምስጋና መር | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የፍጆታ ዕቃዎች ንግድ ሥራ ዘርፍ በ 2014 በጀት ዓመት ውጤታማ መሆኑን በማስመልከት የምስጋና መርሃ-ግብር አዘጋጀ

በኮርፖሬሽኑ የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ በ2014 በጀት ዓመት ባስመዘገው ውጤትና ትርፍ አስተዋጽኦ ላደረጉ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ/ም የምስጋናና የምሳ ግብዣ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡

የምስጋና መርሃ ግብሩን አስመልክተው አቶ ተውፊቅ ይመር የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ ባደረጉት ንግግር 2014 ዓ/ም ለዘርፉ የስኬት ዓመት እንደነበር ገልጸው፣ ለስኬቱ መገኘት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠራተኞችን በማመስገን ለተገኘው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጤታማ ከሆኑ ዘርፎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይህ የሆነው በኮርፖሬሽኑ ድጋፍ፣ በዘርፉ አመራርና ሠራተኞች የጋራ ርብርብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ከተሠራ፣ ጥረት ከተደረገ ውጤት እንደሚመጣ ዘርፉ አሳይቶናል ብለዋል፡፡ የተገኘው ውጤት በ12015 በጀት ዓመትም እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

የፍጆታ ንግድ ሥራ ዘርፍ በቀድሞው ስሙ የኢትዮጵያ የንግድ ድርጅት (አለ በጅምላ) ሲመሰረት ለሥራ ማስኬጃና ለንግድ ሥራው ከባንክ የተበደረውን 596 ሚሊየን ብር ዕዳ ይዞ ኮርፖሬሽኑን የተቀላቀለ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያለበትን ብድር ከወለድ ጋር እስከ መስከረም 30/ 2015 ዓ/ም ብቻ 621 ሚሊየን ብር ከፍሏል፡፡ የንግድ ሥራ ዘርፉ በአመራሩና በሠራተኛው ጠንካራ ጥረት ያለበትን እዳ እየከፈለና የመነገጃ ካፒታል እጥረት ተቋቁሞ ለሕብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የፍጆታ ሸቀጦችን በማቅረብ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ብር 108 ሚሊየን 147 ሺ 527 ብር ትርፍ አግኝቷል፡፡