Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2022-12-21 10:03:27 ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

የሥራ መደቡ መጠሪያ:- ነገረ ፈጅ
ደረጃ:- 8
ደመወዝ: 6,062.00
የትምህርት ዝግጅት:- ከታወቀ የት/ርት ተቋም በህግ፣ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ 10ኛ ክፍል+2፣10ኛ ክፍል+3 አጠናቆ በቅደም ተከተል የመካከለኛ ምሥክር ወረቀት ደረጃ 2 ወይም ዲኘሎማ ያለው/ያላት የደረጃ IV ከፍተኛ ዲኘሎማ ያለው/ያላት
የሥራ ልምድ:- ከምረቃ በኋላ በሙያው መስክ 6/4/0 ዓመት የሰራ/ች
ክህሎት:- አማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋ የሚችል/የምትችል
የሰው ሀይል ብዛት:- 1
የሥራ ቦታ:- አ/አ
የሥራ ዘርፍ (ክፍል):- ዋናው መ/ቤት

ማሳሰቢያ
• መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠየቀው መስፈርት መሠረት ያላችሁን የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም መታወቂያ ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እና ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በመያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት የምዝገባ ቦታዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
• በአካል ቀርበው መመዝገብ ለማይችሉ የክልል አመልካቾች የተጠቀሰው የመመዝገቢያ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድና መታወቂያ ኮፒ፣ ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በማያያዝ በፖስታ ሣጥን ቁጥር 3321 በመላክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
• የገቢ ግብር መከፈሉን የማያረጋግጥና ደመወዝ ያልተጠቀሰበት የሥራ ልምድ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
• በሙያው ልምድ ያለው ይበረታታል፡፡
• የአመልካች ዕድሜ ከ50 ዓመት መብለጥ የለበትም፡፡
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

የምዝገባ ቦታዎች
• ደብረዘይት መንገድ በቅሎ ቤት ከጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት የሰው ሀብት አቅርቦትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
• ለተጨማሪ መረጃ 0114-66-39-48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
• የፈተና ጊዜ፡- በውስጥ ማስታወቂያና በተሰጠው የስልክ አድራሻ ጥሪ ይደረጋል፡፡
• የፈተና ቦታ፡- አዲስ አበባ

የመመዝገቢያ ሰዓት
• ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት
• ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት
• ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

ስለ ኮርፖሬሽኑ ዝርዝር መረጃ ለማወቅ እና የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀላሉ ለማግኘት facebook.com/etbc.official ፣ Telagram: t.me/etbcinfo እና ድረ-ገፅ www.etbc-ethiopia.com ይጎብኙ፡፡
683 viewsedited  07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:20:39
ዓለም አቀፉ የጸረ-ሙስና፣ ነጭ ሪባንና ኤች አይ ቪ ቀን ተከበረ

ኮርፖሬሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚታሰቡትን የጸረ-ሙስና፣ ነጭ ሪባንና ኤች አይ ቪ ቀንን በልዩ ልዩ መርሃ- ግብር ታህሳስ 1/ 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል አከበረ፡፡ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም ትርፋማ ለመሆን ጤናማ ሰራተኛ ያስፈልገዋል፡፡ በመሆኑም የሰራተኛውን ደህንነት መጠበቅ ይገባል፡፡ አያይዘውም ሴቶች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው እነርሱን ከጥቃት መከላከል፤ ህብረተሰብን ከችግር መከላከል በመሆኑ በዓሉን ከማክበር ባለፈ የባህሪ ለውጥ ልናመጣ ይገባል ብለዋል፡፡ ከሙስና ጋር በተያያዘ ሴቶች በነበረው ባህልና ታሪካዊ አመጣጥ ለኢኮኖሚ ችግር የተጋለጡ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ እያንዳንዱ ተቋም ሙስናን የመከላከል ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ በነጭና ቀይ ሪባን፣ ኤች አይ ቪ/ ኤድስና ጤና ነክ ጉዳዮች ላይ በባለሙያ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በሙስና እና ብልሹ አሰራር ምንነት ዙሪያ ሰፊ ሰነድ በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡ በሰነዱ በአሁኑ ጊዜ ሙስናና ብልሹ አሰራር በሃገራችን ስር እየሰደደ በመምጣቱ የሃገሪቱ የህልውና ስጋት እስከመሆን መድረሱ ተመላክቷል፡፡ በኤች ኤ ቪ/ ኤድስ ዙሪያ አጭር ሪፖርት በኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም በመድረኩ ሴቶችን ብቻ ያሳተፈ የጥያቄና መልስ ውድድር ተደርጓል፡፡ እንዲሁም በስራቸው ታማኝነትን ላሳዩ ሰራተኞች ደግሞ እውቅናና ሽልማት የመስጠት ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
695 views08:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 11:19:20
613 views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 13:42:59 የውስጥ ዝውውር/ዕድገት ማስታወቂያ
709 views10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 14:35:07
823 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 16:11:15 ማስታወቂያ ለሲሚንቶ ደንበኞች

የንፋስስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ የሲሚንቶ ሽያጭ ፕሮግራም ከመስከረም 30 ቀን 2015 የተጀመረ መሆኑ ይታወቃል ፤ ሆኖም ባጋጠምን የሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ከህዳር 06 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መስተንግዶ ማቆማችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መጠነኛ ሲሚንቶ መግባት የጀመረ ስለሆነ በምንረከበው የሲሚንቶ መጠን ማክሰኞ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም የሚስተናገዱ ደንበኞች ከዚህ በታች ተገለፀ ሲሆን ፣ በቀጣይ የሚስተናገዱ ደንበኞች ከቆምንብት ማለትም ከንፋስ ስልክ ክፍለከተማ ተመዝግባው እና ፋይል አስገብተው ከሚጠባበቁ ደንበኞች የምንቀጥል ይሆናል ፤ ስለሆነም ማስታወቂያውን በተሌግራም፣ በፌስቡክ እና በማስታወቂያ ሰሌዳ እንድትከታተሉ በማክበር እናሳውቃለን፡፡

27/03/2015 ዓ.ም ሽያጭ የሚከናወንላቸው ደንበኞች ስም ዝርዝር

466 በቀለች ኃይሌ
467 ቴዎድሮስ አውግቸው
468 አምድያሁን ጠቅላላ ንግድ
469 አሰበ ኃይሉ
470 ያስሚን ጀማል
471 አትራጎ ጋርመንት
472 ንጋቷ ታፈረ
473 አብርሃም ባዬ
474 ጽጌ ግፍኦም
475 ሰለሞን ማሞ
476 ደዳኔ ጀዛ
477 ምናላ በቀለ
478 አማረ ጥሩዬ
479 አለም አባተ
480 ቄስ ደሴ አበራ
481 አኑሌ ዶሎሮ
482 ታዬ ሽፈራው
483 አበበች ተሾመ
484 ኪነጥበብ አለማየሁ
485 አበበ አንዱነህ
486 አጀቡሽ ሰንደቅ
487 ይድነቃቸው ደምቡ
488 እነ አሰለፍ ያርደው

489 ገነት በልሁ
490 አዳነ ንጉፊ ህንፃ ተቋራጭ
491 ቲ.አያ አፖርትመንት
492 ሎሚ ገላና
493 ውብአለም አበራ
494 ግራንድ ፈረጀት
495 ሲሳይ አረጋይ
496 ተዋበች ይመር
497 አየለች ፈለቀ
498 ቤተልሄም ስምዖን
499 ዘመቻ ነጋ
500 ተዋበች ተሰማ
501 ፍቅሬ ወሚሶ
502 እነሣራ ተከስተ
503 ታደሰ ገብሩ
504 ኪዳኔ ብርሃኔ
505 ንጉስ መንገሻ
506 ሰርካለም ሀ/ማሪያም
507 አባይነሽ ተኮላ
508 ጌጤነህ ዋሲሁን
509 ዘሪሁን ተምትሜ
510 አቡሻ እሸቴ
511 ጋዲሴ ደበላ
512 አብዲልሃፊዝ ሙደሲር
513 እምነት ፈረደ
514 አብነት ሙሄ
515 መስቤት ጀነራል ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማ
516 ብርቱካን ተሾመ
517 ህይወት ጌታቸው
518 ጌታቸው መኮንን
520 ሰለሞን ብሩ ቶሌራ
521 ሰለሞን ብሩ ቶሌራ
523 ምዕልቲ ተ/ማሪያም
524 አስፋ አበበ
525 በሽራ መረዳጃ እድር
526 የምሩ አበበ
527 አስኩ ታደሰ መንገሻ

528 ከፍያለው ታምራት
529 አየለ ፋንታ በላቸው
530 ድረስ መኩሪያ ይዘንጋው
531 ቃልቂዳን ሚደቅሳ
532 አዲስ አለም አሥራት
533 ከብቱ አንቄ እና ሲሳይ አንቄ
534 ካሜል አሊ ኸሊል
535 ጌታቸሙ ወልዱ ባቦሳ
536 ያየሽ ዳጉ ዳምጠው
537 ተስፋዬ ለማ በየነ
538 ቤተልሄም በኮን ቦንቱ
539 አለማየሁ ከተማ
540 ሳድያ በሽር ኢስማን
541 ህዱወ ደ/ን
542 አማን ደምሴ
543 ያኔት ጥሩነህ በዳዳ
544 አበበች መልካም
545 ሀረገወይን መሃመድ አሊ
546 ቶሎሳ ሄይ ብሩ
547 ወሰነ ዳዲ እንደኤዥ
548 እነ አዱኛ ቃበቶ ሸቦ
549 ዘውዲቱ ሳህለይ ተ/ሐይማኖት
550 ሰናይት አስማማው እና 4 ወራሾች
551 ብርቱካን መኩሪናያ አለማየሁ
552 ፍቅረዮሐንስ ለማ
553 ሙሉ ሀ/መስቀል
554 ገበያነሽ ጌታነህ ካሳ
555 ሲቲና ሀሠን
430 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 15:56:13 የውስጥ ዝውውር/ዕድገት ማስታወቂያ
479 views12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 11:21:44
529 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 16:07:43 የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በሲሚንቶ ግብይትና ስርጭት ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደ ።

ህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ የክፍለ ከተማ ንግድ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የመንግሥት ፕሮጀክት አስገንቢ ተቋማት እንዲሁም ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎችና አከፋፋዮች በተገኙበት በሲሚንቶ ግብይት፣ ስርጭትና ቁጥጥር ላይ ውይይት አካሂዷል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አሁን እየታየ ያለውን የሲሚንቶ ምርት እጥረትና ሰው ሠራሽ የሆነ የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በዋናነት የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መስራት መሆኑን ገልፀው የፋብሪካዎችን ምርት ማሳደግና ስርጭቱ ላይ ከፍተኛ ክትትል በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል ።

አቶ አደም ኑሪ የከተማው ንግድ ቢሮ ሃላፊ በበኩላቸው ለተፈጠረው የሲሚንቶ እጥረትና ሰው ሠራሽ የዋጋ ንረት ምክንያት በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚፈልጉ አካላት የፈጠሩት መሆኑን ገልፀው፤ ለከተማው የተመደበውን ኮታ አጠቃቀም ለማሳደግና የቀረበውን ምርት ለታለመለት ዓላማ ለማዋል ያስችላል ያሉትን አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ የማንሳት አቅምን ከፍ ለማድረግ የመንግስት ፕሮጀክት የሚያስገነቡ ተቋማት፣ ሲሚንቶን በግብዓትነት የሚጠቀሙ አምራቾችና ስትራቴጂክ ፋይዳ ያላችው የግሉ ሴክተር በቀጥታ ከፋብሪካ እንዲያነሱ፤ በሌላ በኩል አነስተኛ ፍጆታ ያላቸው ተጠቃሚዎች ከኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት አቅራቢ ልማት ድርጅትና ከኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን እንዲያነሱ በተጨማሪም በቅድመ ክፍያ ያልተነሳ ምርት ያላቸውን አከፋፋዮች የሚያነሱት በተተመነ ዋጋ በቸርቻሪዎች በኩል ለህዝብ እንዲደርስ የስርጭት መስመር የተዘረጋ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በዚህ መልኩ በከፍተኛ ጥረት ወደ ከተማው የሚገባው ምርት ለታለመለት ፕሮጀክት ብቻ እንዲውል ፋብሪካዎች፣ አስገንቢ ተቋማት፣ አከፋፋይ ድርጅቶችና የንግድ ቢሮ በቅንጅት ክትትል ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡ አላስፈላጊ ተጠቃሚነትን ለመከላከል የምርት ስርጭቱ ኦዲት እንደሚደረግና ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የክትትል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡ በመጨረሻም ውዝፍ ምርት የሚያነሱ አከፋፋዮች ቢሮው ያዘጋጀውን የስርጭት ውል ተዋውለው ወደ ስራ እንዲገቡ ጥሪ አስተላልፈው ከዚህ ውጪ ለሚንቀሳቀሱት በሚኒስቴሩ እና በፋብሪካዎች በኩል ተገቢው እርምት እንዲወሰድ ጠይቀው ይህ ሳይሆን ቀርቶ ምርት ሲያዝዋውር የተገኘ አካል መስከረም 05/2015 በወጣው የህዝብ ማስታወቂያ መሰረት እንደሚወረስ አክለው ገልፀዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተወካይን ጨምሮ በመድረኩ የተሳተፉ አካላት ለስርጭት እጥረትና ለዋጋ ንረቱ መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ሃሳብ አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ምንጭ፡- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
569 views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 09:41:12
579 views06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ