Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-03 13:44:08
449 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 08:51:40 የሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች ሽያጭ አፈፃፀም

ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥ ገበያ ኮርፖሬሽኑ ብር 4,101,217,587 ዋጋ ያለው 1,281,411 ሚሊዮን ኩንታል ምርትና እና የአገልግሎት ሽያጭ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ አቅዶ ብር 3,273,864,897 ቢሊዮን ዋጋ ያለው 999,481 ኩንታል ምርት እና የአገልግሎት ስርጭት በማከናወን የዕቅዱን በመጠን 78 በመቶ በዋጋ ደግሞ 80 በመቶ አከናውኗል፡፡ የአቅርቦትና ስርጭት አፈፃፀም ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 5 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በሀገር ውስጥ የፍጆታ ምርቶች ግብይት ሽያጭ ኮርፖሬሽኑ ያገኘው ገቢ ብር 5,822,656,134 ሲሆን ይህም በገቢ ድርሻ ሲታይ፡-
እህልና ቡና 65.42%፣
የምግብ ዘይት 16.29%፣
ስኳር 2.8%
የኮንስትራክሽን ግብአቶች 7.2%፣
የአትክልትና ፍራፍሬ ስርጭት 2.5 በመቶ በድምሩ 94.1% ድርሻ ሲኖራቸው ቀሪው 5.9% የሌሎች ፋብሪካ ምርቶችና አገልግሎት ሽያጭ ገቢ ድርሻ ነው፡፡

የውጭ ሀገር ሽያጭ አፈፃፀም

ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ላይ በውጭ ገበያ /ኤክስፖርት/ 10,290 ኩንታል እህልና ቡና በብር 80,185,520 ለመሸጥ አቅዶ 6,577 ኩንታል የተለያዩ የብርዕ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ቡና እና ፍራፍሬ በብር 77,460,788 በመሸጥ የዕቅዱን በመጠን 64 በመቶ በዋጋ ደግሞ 97 በመቶ አከናውኗል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ኤክስፖርት ከተደረገው ምርት ሽያጭ 1,484,418.70 የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
493 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 10:44:38 የደረጃ ዕድገት/ዝውውር ማስታወቂያ
626 views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 11:31:36 የመሠረታዊ ፍጆታ ምርት አቅርቦት ግዥና ሽያጭ አፈፃፀም
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2015 በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ውስጥ ያከናወነው የመሰረታዊ ግዥና ሽያጭ አፈጻጸም በዋናነት የሚከተለውን ይመስላል፡፡
የአጠቃላይ ግዥ አፈጻጸም
ኮርፖሬሽኑ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ላይ ከሀገር ውስጥ ሊገዛው ያቀደው መሠረታዊ የምርት አቅርቦት መጠን ብር 2,452,146,728 ዋጋ ያለው 590,075 ኩንታል ሲሆን በዚህ ወቅት ብር 1,693,176,828 ዋጋ ያለው 764,606 ኩንታል በመግዛት የዕቅዱን በመጠን 130 በመቶ በዋጋ ደግሞ የዕቅዱን 69 በመቶ አከናውኗል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የሀገር ውስጥ ግዥ መጠን ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ግዥ ጋር ሲነፃፀር 62 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

የሽያጭ አፈፃፀም
ኮርፖሬሽኑ የ2015 ግማሽ በጀት ዓመት ላይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ብር 5,998,054,369 ዋጋ ያለው 1,833,327 ኩንታል መሠረታዊ ምርትና አገልግሎት ለማሰራጨት አቅዶ ብር 5,900,116,922 ዋጋ ያለው 2,036,415 ኩንታል ምርትና አገልግሎት በማሰራጨት የዕቅዱን በመጠን 111 በመቶ በዋጋ ደግሞ 98 በመቶ አከናውኗል፡፡ ከተገኘው ጠቅላላ ሽያጭ ገቢ 93.1 በመቶ ከሀገር ውስጥ ሽያጭ ገቢ የተገኘ ሲሆን ቀሪው 6.9 በመቶ ከኤክስፖርት የተገኘ ገቢ ነው፡፡
የግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ ሽያጭ መጠን ከ2014 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሽያጭ ጋር ሲነፃፀር 41 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
765 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 11:45:37
885 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 11:45:26 የማህበራዊ ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባዔና የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ

በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን የማህበራዊ (social) ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባኤ እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ በጡረታ ለተገለሉና በተለያየ ምክንያት ለለቀቁ ሰራተኞች የሽኝት ፕሮግራም ጥር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በዓመታዊ ጉባዔው ላይ የማህበራዊ ኮሚቴ አባል ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ከጥር 20/2014 ዓ.ም እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ/ም. በአንድ ዓመት ውስጥ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራት ማለትም የአባላት ምዝገባ፣ በመተዳደሪያ ደምቡ መሠረት የተሰጡ አገልግሎቶች፣ የተሰበሰበ ገንዘብና የወጡ ወጪዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና የመፍትሔ ሐሣቦችን ያካተተ አጭር ሪፖርት ቀርቦ ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡ ከተመሰረተ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ማህበራዊ ኮሚቴ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ብቻ 60ሺ 500 ብር ለሃዘን፣ ለወሊድና ለጋብቻ ወጪ እንዳደረገ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡ የማህበሩ ካፒታልም ብር 217,078 መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ማህበራዊ ኮሚቴው 427 ሰራተኞች በአባልነት ያቀፈ ሲሆን የአባላቱን ቁጥር ለማብዛት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ሪፖርቱን ያቀረቡት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ታደሰ የማህበራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ሳይሰስቱ ከልብ ሲያገለግሉ ለነበሩ የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለማህበሩ እዚህ ደረጃ መድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው በማለት በኮሚቴው አባላት ስም የከበረ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑን በጡረታና በገዛ ፈቃዳቸው ለለቀቁ ስምንት ሰራተኞችም ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል፡፡ አሸኛኘት የተደረገላቸው ሰራተኞችም የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ለኮሚቴው የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የኮርፖሬት የህ/ማ/ጉ/አሰ/ማ/ ም/ዋና ሥ/ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ሰራተኛው እርስ በርሱ የሚረዳዳበት መንገድ ይፈጠር በሚል ኮርፖሬሽኑ ማኅበሩ እንዲመሠረት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው በቀጣይም ድጋፉ እንደማይቋረጥ አስረድተዋል፡፡ የአባላቱን ቁጥር ለማብዛት መሰራት እንዳለበትም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡
703 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 16:44:11
838 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 11:44:40
የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ተግባር አከናወኑ
የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና የእህልና ቡና ንግድ ስራ ዘርፍ ሰራተኞች በዋና መ/ቤት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ጥር 19/ 2015 ዓ.ም አከናወኑ፡፡
የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ ሮ ትግስት አለማየሁ በ2014 ዓ.ም እንደ ኮርፖሬሽን ከ2ሺ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ 250 የሚሆኑት በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የተተከሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ ቅመማ ቅመም፣ አበባ፣ እንዲሁም እንደ ቡናና ሙዝ ያሉ የዛፍ ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም በዛሬው እለት የተካሄደው መርሃ ግብር የተከልናቸውን ችግኞች በቀጣይነት ለመንከባከብና ሰራተኛው ወደፊትም በባለቤትነት እንዲንከባከቡ ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ በሆለታ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ስራ እንደሚሰራ ገልጸው ዘርፎችም በዚህ መነሻነት በዘርፋቸው የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
874 views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 11:43:25
ወደ ኋላ የዘገዩ የሂሳብ ምዝገባዎችን ማጠናቀቅ፣ የሂሳብ ማጥራት እና የIFRS ትግበራ ማፋጠንን አስመልክቶ ማሳሰቢያ ተሰጠ
በኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች (ፋይናንስ፣ ኦዲትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ውስጥ የሚገኙ የፋይናንስ ባለሙያዎችን ጨምሮ የአራቱም ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የዘርፉ ሃብት መምሪያ ኃላፊዎችን ያካተተ የጋራ መድረክ ጥር 18/ 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ የመድረኩ ዓላማ ኮርፖሬሽኑ ያለውን ሃብት፣ ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ለመከታተልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የመንግስት የበላይ አካል ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ሁኔታ አውቆ ውሳኔ ለመስጠት እንዲችል መሆኑን መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ገልጸዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው ወደ ኋላ የዘገዩ የሂሳብ ምዝገባዎችን ማጠናቀቅ፣ የሂሳብ ማጥራት እና የIFRS ትግበራ ማፋጠንን አስመልክቶ ከሂሳብ ምዝገባ፣ ሂሳብ ማጥራትና IFRS ትግበራ ጋር በተያያዘ ውዝፍ ስራዎች መኖራቸውን በመግለጽ ውዝፍ ስራዎቹን ኮሚትመንት በመጨመር በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም የተሟላ መረጃ በማቅረብና በቁጭት ስሜት ከዚህ በፊት የተሰጡ የኦዲት ኮሜንቶች መስተካከል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ዘርፎች ያጋጠማቸውን ችግርና ከችግሩ እንዴት እንውጣ፣ ማን ምን ይስራ በሚል ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ እያንዳንዱም ዘርፍ የደረሰበትን ለመድረኩ ሪፖርት ያደረገ ሲሆን ውዝፍ ስራውን እጅግ በፈጠነ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንዲቻል ታክስ ፎርስ እና ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡
776 views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 15:51:27
863 views12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ