Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-08 15:45:28
646 viewsedited  12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 09:42:46 ኮርፖሬሽኑ ባለ አምስት ሊትር የምግብ ዘይት በማሰራጨት ላይ ይገኛል

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገራችን ያለውን መሠረታዊ የምግብ ፍጆታ ምርቶች አቅርቦት እጥረትና የዋጋ ንረትን ለመቋቋም የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በማከፋፈል ገበያውን ማረጋጋት እና የሃገር ውስጥ አምራቾችን ማበረታታት ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በመሆኑም ኮርፖሬሽኑ ከፊቤላ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የ26 ሺህ ሊትር የሱፍ የምግብ ዘይት ግዢ በመፈጸም ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ 6 ሺህ ሊትር በኮርፖሬሽኑ የአትክልትና ፍራፍሬ ሱቆች በኩል ለህብረተሰቡ ፍጆታ እንዲውል የተደረገ ሲሆን ቀሪው 20 ሺህ ሊትር ደግሞ በቅርቡ የሚሰራጭ ይሆናል፡፡ ባለ አምስት ሊትር የሱፍ የምግብ ዘይቱ በ930 ብር በአዲስ አበባ እና በክልሎች እየተሸጠ ሲሆን ይህም ገበያ ላይ ካለው ዋጋ ጋር ሲነጻጸር 13 በመቶ ያህል ቅናሽ ያለው ነው፡፡
605 views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 14:44:45
626 views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 09:23:47
601 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 16:28:19
593 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 16:28:08 በኮርፖሬሽኑ ማቀዝቀዣ መጋዘንን የያዘ ሁለገብ ሕንጻ ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ ተጣለ

የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርት ጥራቱና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ የሚያስችል ማቀዝቀዣ መጋዘንን ጨምሮ ሁለገብ ሕንጻ ለማስጀመር የሚያስችል የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ-ስርዓት የካቲት 25/2015 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሺ ቶታል ነዳጅ ማደያ አጠገብ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ይዞታ ውስጥ አከናወነ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የሁለገብ ህንጻው ግንባታ ከ 1.24 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሚሰራና የሕንጻው ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አያይዘውም በተለይም የማቀዝቀዣ ግንባታው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሳይበላሹ፣ ጥራታቸውን እንደጠበቁ እና በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚው ጋር እንዲደርሱ ለማድረግ እና አምራቹ ምርቱ ገበያ እንዲያገኝ ለማበረታታት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮርፖሬሽኑ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሀሰን ሙሁመድ በበኩላቸው የሚገነባው ህንጻ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም መሆኑን በመጠቆም የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን እለት ታሪካዊ ቀን ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ህንጻው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች በትጋት እንዲሰሩ ጠይቀው የስራ አመራር ቦርዱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

የሚገነባው ሕንጻ ሁለት መሰረት ያለው ባለ አስር ወለል ቅይጥ የአገልግሎት ህንጻ እና ዘመናዊ ባለማቀዝቀዣ መጋዘን የያዘ ሲሆን በተጨማሪም የገበያ ማዕከል፣ ላቦራቶሪዎች እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራን ያካተተ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተግበር የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች አቅርቦትን በጥራት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ በስነ-ስርዓቱ ወቅት ተመላክቷል።
587 views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 11:22:59
ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲያካሂድ የነበረውን ዓውደ ርዕይ አጠናቀቀ

በአዲስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ከየካቲት 16-20/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው በዚሁ ርዕይ ላይ ኮርፖሬሽኑ ባደረገው ተሣትፎ ከአገር ውስጥ አምራቾች በተወዳዳሪ ዋጋ የሚረከባቸውንና ከውጭ አስገብቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች ለዕይታ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ባሉት ሰፊ የእህልና ቡና ማደራጃ አውታሮች አዘጋጅቶ ለውጭ ገበያ የሚያቀርባቸው የተለያዩ የቡና ዓይነቶችና የቅባት እህሎች ለተሳታፊ ለሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት ዕይታ ቀርበዋል፡፡
በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ የንግድ መስኮች የሚሠሩ ተቋማት ተሣታፊ በሆኑበት በዚህ ዓውደ ርዕይ ላይ ኮርፖሬሽኑ ምርትና አገልግሎቱን ማስተዋወቅ ከመቻሉ ባሻገር የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን ለተሣታፊው በአነስተኛ ዋጋ አቅርቧል፡፡

የየዘርፉ ባለሙያዎች ርዕዩ ምርትና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ በቂ ጊዜና አመቺ ቦታ እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡ የዓውደ ርዕዩ ጎብኚዎች በሰጡት አስተያየት የኮርፖሬሽኑ ምርቶች ዋጋ ገበያ ላይ ካለው ዋጋ አኳያ ቅናሽ ያለው መሆኑን እንደተገነዘቡ በመግለጽ ኮርፖሬሽኑ ይህንኑ አሠራሩን አጠናክሮ እንዲጥል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
346 views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 11:47:58
ኮርፖሬሽኑ እየተሳተፈበት የሚገኘው ዓውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከየካቲት 16-20 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የኤግዚቢሽን ማዕከል እያካሄደ ያለው "Enhanced Export for Sustainable Development" አውደ ርዕይ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በአውደ ርዕዩ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርትና አገልግሎቱን ማለትም ኮርፖሬሽኑ ለገበያ የሚያቀርባቸው ጥራታቸውን የጠበቁ የቡና፣ የቅባት እህል፣ የጥራጥሬና ቅመማ ቅመም፣ ልዩ ልዩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን፣ በፋብሪካ የተቀነባበሩና የግብርና መሠረታዊ ምርቶችን፣ ለህብረተሰቡ ፍጆታ የሚውሉ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ የንጽህና መጠበቂያዎች፣ የህጻናት ወተት፣ የታሸጉ ምግብና መጠጦች፣ የጽህፈት መሣሪያዎችን እና ሌሎች ምርቶችን ለጎብኚዎች ባለፉት ቀናት ሲያስተዋውቅ ቆይቷል፡፡

አውደ ርዕዩ የአገራችንን የግብርና እና ኢንዱስትሪ ምርቶችን በአጠቃላይ ለአገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ተሳታፊ ለሚሆኑ ጎብኝዎች ማስተዋወቅን ዓላማው አድርጓል፡፡ በኤግዚቢሽኑ ላይ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት አምራቾች በመሳተፍና ግብይት በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
452 views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 11:35:42
218 views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 15:47:35
350 views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ