2023-01-14 17:36:03
አቮካዶን ይመገቡ
አቮካዶ ለጤና ተስማሚ የሆነ የፍራፍሬ አይነት ሲሆን በውስጡ ጥሩ የሚባለውን ፋት ይዟል ይህም ፋት በከባድ በሽታዎች የመጋለጥ እድላችንን ይቀንሳል። በውስጡ ያሉት ጠቃሚ የምግብ ንጥረ ነገሮች በእሳት ወይም በዝግጅት ጊዜ አይበላሹም። አቮካዶ በቫይታሚን ኤ፣ ሲ፣ ኢ የበለጸገ ሲሆን እንደ ፖታሲየም ያሉ ንጥረ ነገሮች ይዟል:: በተጨማሪም ፎሌት፣ ሞኖሳቹሬትድ ፋት እና አንቲኦክሲዳንት ይዟል።
10 አቮካዶን እንድንጠቀም የሚያደርጉን ምክንያቶች ፦
1. አቮካዶ የደም ግፊትንና የደም ዝውውርን የሚያስተካክለውን ፖታሲየም (Potassium) የተሰኝውን ንጥረ ነገር በብዛት ይዟል፡፡ በአቮካዶ ውስጥ የሚገኝው ፖታሲየም ሙዝ ውስጥ ከሚገኝው በ10% ይበልጣል።
2. አቮካዶ ፎሌት የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ የያዘ ሲሆን ለእርጉዝ ሴቶች በጣም ጠቃሚና ለህፃኑ የአእምሮና አካላት እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በተጨማሪም በእርግዝና ወቅት የሚመጣውን ማቅለሽለሽ የሚከላከል ቫይታሚን ቢ6 ይዟል።
3. በአቮካዶ ውስጥ ያለው ሞኖሳቹሬትድ ፋት (Monosaturated Fat) ለልብ ህመም የሚያጋልጠውን ኮሌስትሮል በመቀነስ ጤናን ያስተካክላል፤ በተጨማሪም ለስኳር ህሙማን በደም ውስጥ ያለውን ትራይግላይሴራይድ (Triglycerides) በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የጎላ ነው።
4. አቮካዶ ኦሊይክ አሲድ በውስጡ ይዟል፡፡ ይህ አሲድ የጡት ካንሰርን ይከላከላል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አቮካዶ ጤነኛ ሴሎችን በመተው በካንሰር የተያዙ ሴሎችን እድገት ይገታል።
5. አቮካዶ ሊየቲን የተባለ ቫይታሚን ሲኖረው ይህ ቫይታሚን የካሮቲን ቫይታሚን ከሆነው ቫይታሚን ኤ ዝርያ የሚመደብ ሲሆን ለአይን ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው።
6. አቮካዶ ከፕሮስቴት ካንሰር የሚከላከሉና የተጐዱ ሴሎችን የሚጠግኑ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ይዟል።
7. አቮካዶ የአፍ ካንሰርን ከመከላከሉ ባሻገር ለመጥፎ የአፍ ጠረን አይነተኛ መፍትሄ ነው።
8. በአቮካዶ ውስጥ ያሉት ኢንዛይምና የምግብ ንጥረ ነገሮች ሰውነታችን የካሮቲን ቫይታሚንና የምግብ ንጥረ ነገሮችን እንዲመጥ የማድረግ ብቃቱን ይጨምሩለታል፡፡ እነዚህ ኢንዛይሞች የተጐዱ የጨጓራና የትንሹ አንጀት ግድግዳዎችን በማለስለስ ወደር አይገኝላቸውም።
9. በአንቲ ኦክሲዳንት (Antioxidant) የበበለፀገ ስለሆነ ከእርጅና ጋር ተያይዘው የሚመጡ ምልክቶችን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም ግሉታቲዩን የተባለ ንጥረ ነገር እርጅና እንዳይከሰት ያደርጋል። የሰውነታችንን በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል፡፡ የነርቭ ስርዓት ጤናማ እንዲሆን ያደርል።
10. አቮካዶ በቫይታሚን የበለፀገ ሲሆን ቆዳችንን ከፍሪራዲካልስ ይከላከላል።
ምንጭ፡- ሜዲካል ኒውስ ቱዴይ ድረገጽ
ያስታውሱ፡-ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች ባሉት የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ሱቆች ጎራ በማለት አቮካዶን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት ይችላሉ፡፡
311 viewsedited 14:36