Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etbcinfo — Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)
የሰርጥ አድራሻ: @etbcinfo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-01-03 16:03:57
ከ43 ሚሊዮን ሊትር በላይ የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ

ታህሣሥ 25/2015 ዓ.ም - ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዘይት አንዲያገኝ በጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ ካምፓኒ የ43 ሚሊዮን 37 ሺ 412 ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታውቋል፡፡

የግዢ ውሉን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ሲሆኑ ለግዢ የሚውለውን የ69 ሚሊዮን 894ሺ 440 የአሜሪካን ዶላር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና የሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑ ታወቋል፡፡

የምግብ ዘይቱ ግዢ በአንድ አመት የክፍያ ጊዜ የሚፈጸም ሲሆን ይህን የሀገር ውስጥ የምግብ ዘይት ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ የተፈጸመውን ግዢ ያስተባባረው የገንዘብ ሚኒስቴር የግዢ ውሉን ለተፈራራሙት ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅቶች በላከው ደብዳቤ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ እሽግ የፓልም ምግብ ዘይት የመሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው አሳውቋል፡-

የአዲስ አበባ የፓልም ምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ
• ባለ 3 ሊትር በጄሪካን …… ብር 314
• ባለ 5 ሊትር በጄሪካን …… ብር 510
• ባለ 20 ሊትር በጄሪካን …… ብር 2003 መሆኑ ታውቋል

ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ከተሞችን በተመለከተም ርቀትን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በኩንታል 60 ሳንቲም በአንድ ኪ.ሜ መሆኑ ታሳቢ ተደርጎ ሽያጭ እንዲከናወንና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርም በተለመደው መልኩ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን የስርጭት ኮታ በመመደብ ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት እዲያሳውቅ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

(የገንዘብ ሚኒስቴር)
711 views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-02 13:49:17 በለውጥ ስራዎች ትግበራ ዙሪያ የአካል ምልከታ ተካሄደ
በኮርፖሬሽኑ የለውጥ ስራዎች (ቢ ኤስ ሲ፣ ካይዘን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ የመመሪያዎች አተገባበር እና መሰል ተያያዥ ጉዳዮች) አተገባበር ዙሪያ የአካል ምልከታ (ሱፐርቪዥን) በማካሄድ ከሚመለከታቸው የዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም በቀጣይ ይበልጥ የተጠናከረ የለውጥ ስራዎች ትግበራ ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የአካል ምልከታው ኣላማ ኮርፖሬሽኑ ከካይዘን ልህቀት ማእከል ጋር አስቀድሞ ባደረገው የካይዘን ትግበራ ስምምነት መሰረት ችግር ፈቺ የትግበራ አካሄድን ለመተግበር እንዲያስችል ነው፡፡
በአካል ምልከታው የኮርፖሬት የህግ፣ ማህበራዊ ጉዳይና አሰራር ማሻሻያ ም/ዋ/ሥ/ አስፈጻሚ አቶ ይርጋሸዋ ተሸመ፣ የኮርፖሬት የአሰራር ዘዴና የአገልግሎት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ትእዛዙ ኃ/ ጊዮርጊስ እንዲሁም የካይዘን ልህቀት ማእከል የስራ ኃላፊና የካይዘን አማካሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ የቡና ማእከል፣ የእህል ማከማቻና ማደራጃ ማእከል፣ የፍጆታ እቃዎች ንግድ ስራ ዘርፍ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ስራ ዘርፍ እና የሎጀስቲክስና ቴክኒክ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምልከታው የተካሄደባቸው ዘርፎች ናቸው፡፡
783 views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 15:55:13 ሚኒስቴሩ ከጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ ገለጸ

ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ስራ አቁመው የነበሩ የስኳር ፋብሪካዎች ምርት ማምረት መጀመራቸውን ተከትሎ ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስኳር አቅርቦት እጥረት እንደሚቀረፍ ጠቁሟል፡፡
በጸጥታ ችግር እና በመለዋወጫ እጥረት ምክንያት የስኳር ፋብሪካዎች ማምረት በማቆማቸው እና በውጪ ምንዛሪ እጥረት ከውጪ ተገዝቶ ባለመግባቱ ላለፉት ጥቂት ወራት የስኳር እጥረት መከሰቱ ይታወሳል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብም በአሁኑ ሰዓት ወንጅ፣ ኦሞ 2 እና 3 እንዲሁም ፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎች ማመረት ጀምረዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም በቀጣይ ለሚከበረው የገና በዓል ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ሌሎችም ስኳር የሚጠቀሙ ተቋማት የኮታቸውን 25 በመቶ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በሀገር ውስጥ ከሚመረተው በተጨማሪ ከውጪ የሚገባውም ግዥ የተፈጸመ ሲሆን ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የስርጭቱን ኮታ መቶ በመቶ ማዳረስ እንደሚቻልና አሁን የተስተዋለው የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት ይቀረፋል መባሉን ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ታኅሣሥ 21/2015 (ዋልታ)
457 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 16:04:24 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል ተባለ

የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎት እንዲጣጣም ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት እንደሚገባቸው ተገለጸ::
የሲሚንቶ አምራቾች ማህበርና የሲሚንቶ አምራቾች ባለቤቶች ማህበር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም÷በተለያዩ የፀጥታ ችግሮችና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ምርት ያቆሙና በሙሉ አቅማቸው የማያመርቱ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ገልጸዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታም መፋጠን እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
ምርት አቁሞ የነበረው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል::
ፋብሪካው በቅርቡ ስራ እንዲጀምር ለማድረግም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንደሚላኩ ተመላክቷል፡፡
የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት ማቆሙ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እንዲቀንስ አድርጎት እንደነበረም ነው የተገለጸው ።
ቸርቻሪዎችም የሚሸጡበትን የሲሚንቶ ዋጋ የመለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው::
ምንጭ፡- ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት፤ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ/ም
644 views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 11:38:46 የዝውውር/ደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ
688 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-29 11:37:59 የዝውውር/ደረጃ ዕድገት ማስታወቂያ
676 views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 10:10:02
498 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 14:06:42
ኮርፖሬሽኑን ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽንን በቅርቡ ለተቀላቀሉ አዲስ ሰራተኞች የትውውቅ ስልጠና ታህሳስ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ተካሄደ፡፡ ስልጠናውን ያዘጋጀው የኮርፖሬት የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጸጻም አመራር ቡድን ሲሆን የስልጠናው ዓላማ ለአዲስ ሰራተኞች የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ ገጽታ እና አሰራር ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በኮርፖሬሽኑ የሰው ሃብት ልማትና ሥራ አፈጸጻም አመራር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ይመር አዲስ ሰራተኞች ኮርፖሬሽኑን ሲቀላቀሉ ስለድርጅቱ አወቃቀር፣ የሥራ ሂደት እንዲሁም ከሥራ ባልደረቦች ጋር የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ ገልጸው በዚህም መሰረት የዛሬው ስልጠና መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡

አቶ ምክረ ተክሌ፣ ከፍተኛ የሰው ሃብት ባለሙያ በኮርፖሬሽኑ የህብረት ስምምነትና በሃብት አመራር መመሪያ ላይ የተቀመጡ የሰራተኞች መብትና ግዴታዎችን ለአዲስ ሰራተኞች ያብራሩ ሲሆን አዲስ ሰራተኞች በመመሪያ የተደገፉ መብትና ግዴታቸውን አውቀው መስራት እንደሚገባቸውና በተቻለ መጠን የሥራ ዲሲፕሊን ጠብቀው መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናውን የተመረጡ የስራ ክፍሎች ማለትም የኮርፖሬት ሰው ሃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት የህግ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት፣ የኮርፖሬት የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት እና የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሰጥተዋል፡፡
508 views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 11:00:59
712 views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 10:04:20 ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ (ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም)

የሥራ መደቡ መጠሪያ:- ነገረ ፈጅ
ደረጃ:- 8
ደመወዝ: 6,062.00
የትምህርት ዝግጅት:- ከታወቀ የት/ርት ተቋም በህግ፣ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ 10ኛ ክፍል+2፣10ኛ ክፍል+3 አጠናቆ በቅደም ተከተል የመካከለኛ ምሥክር ወረቀት ደረጃ 2 ወይም ዲኘሎማ ያለው/ያላት የደረጃ IV ከፍተኛ ዲኘሎማ ያለው/ያላት
የሥራ ልምድ:- ከምረቃ በኋላ በሙያው መስክ 6/4/0 ዓመት የሰራ/ች
ክህሎት:- አማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋ የሚችል/የምትችል
የሰው ሀይል ብዛት:- 1
የሥራ ቦታ:- አ/አ
የሥራ ዘርፍ (ክፍል):- ዋናው መ/ቤት

ማሳሰቢያ
• መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠየቀው መስፈርት መሠረት ያላችሁን የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም መታወቂያ ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እና ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በመያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት የምዝገባ ቦታዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
• በአካል ቀርበው መመዝገብ ለማይችሉ የክልል አመልካቾች የተጠቀሰው የመመዝገቢያ ጊዜ ገደብ ሳያልፍ የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድና መታወቂያ ኮፒ፣ ካሪኩለም ቪቴ ከማመልከቻ ጋር በማያያዝ በፖስታ ሣጥን ቁጥር 3321 በመላክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
• የገቢ ግብር መከፈሉን የማያረጋግጥና ደመወዝ ያልተጠቀሰበት የሥራ ልምድ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፡፡
• በሙያው ልምድ ያለው ይበረታታል፡፡
• የአመልካች ዕድሜ ከ50 ዓመት መብለጥ የለበትም፡፡
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

የምዝገባ ቦታዎች
• ደብረዘይት መንገድ በቅሎ ቤት ከጠመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት በሚገኘው በኢትዮጵያ የንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት የሰው ሀብት አቅርቦትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 506 በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
• ለተጨማሪ መረጃ 0114-66-39-48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
• የፈተና ጊዜ፡- በውስጥ ማስታወቂያና በተሰጠው የስልክ አድራሻ ጥሪ ይደረጋል፡፡
• የፈተና ቦታ፡- አዲስ አበባ

የመመዝገቢያ ሰዓት
• ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት
• ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት
• ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡

ስለ ኮርፖሬሽኑ ዝርዝር መረጃ ለማወቅ እና የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎችን በቀላሉ ለማግኘት facebook.com/etbc.official ፣ Telegram: t.me/etbcinfo እና ድረ-ገፅ www.etbc-ethiopia.com ይጎብኙ፡፡
728 viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ