Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-03-12 19:44:46
የወንጀል ሕጋችን፣ ከጥንቆላና ከድግምት ጋር በተያያዘ ያስቀመጠው ዐሳብ ግልጥ ነው። ጠንቋይ ወይም ደጋሚ ወይም ተመሳሳይ ይዘት ባለው መንገድ፣ አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ከፈጸመው ብቻ ነው ወንጀል የሚኾነው።

ሊድያ ይህን ተግባር መፈጸሟን ያሳየ አካል የለም። ይባስ ብሎ እንደ "ትልቅ" ወንጀል ወይም ጊዜ ቀጠሮ እንደሚያስፈልገው ወንጀል ጊዜ ቀጠሮ 14 ቀን ተጠይቆ ሙሉ ተሰጥቶ ሰምተናል። ለውስብስብ ወንጀል 14 ቀን በማይሰጥበት ለዚህች ብላቴና ይህ መኾኑ ያሳዝናል። በአጭር ቃል ግን እንዲህ ልበል፣ ኢየሱስ ጌታ ነው ማለትና ጥንቁልና አይገናኝም!
566 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 18:55:17
የእስር ነገር ከተነሳ መታሠርና ወደ ወህኒ ቤት መጣል የነበሩት፣ የለየላቸው አጭበርባሪ "ነቢያትና ሐዋርያት ነን፣ ጸበል አጥማቂ ነን" እያሉ ሕዝቡን ዘርፈው የነጠጡትን ነበር። እንዲህ ያለችውን በትክክል አጥፍታ ቢኾን እንኳ፣ በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ተናገሩት ከምርመራ በኋላ መኾን ይገባው ነበር። በወንጀል ያልተጠቀሰን ድርጊት፣ ወንጀል ብሎ ማሰር ነውርም ሕገወጥነትም ነው። ኢየሱስ ጌታ ነው ማለት ማንን ሊያስቆጣ እንደሚችል እናውቃለን!
923 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 17:18:48 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ክርስቶስ የትኛውንም ጥምና ረሃብ የሚመላ እርካታና ጥጋባችን እንደ ኾነ ይመሰክርልናል፤ የመጽሐፍ ቅዱሱ የተሰቀለው ክርስቶስን እከተለዋለሁ፤ ማራን አታ!
452 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 10:48:19
የፕሮቴስታንት "ዘማሪያን" ከነጋሽ አዲሱ ወርቁ፣ ጋሽ ተስፋዬ ጋቢሶና ከተወሰኑት በቀር፣ "የስህተት መምህራን አጋፋሪና አጫፋሪዎች" ናቸው። ከዚያ ወዲህ መጥተው የወንጌል ቤተሰብ ነን ሲሉ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ነው። የጃፒ ደቀ መዝሙር የኾነው በጋሻው ደሳለኝን አጅበው የመጡት የምናውቃቸው "ዘማሪ ተብዬዎች" ናቸው!

ከዓመታት በፊት በጋሻው ደሳለኝንና እንክርዳድ የኾነውን የእምነት እንቅስቃሴ የተባለውን የተሰቀለውን ክርስቶስን ተቃዋሚ ትምህርት በዚህ መጽሐፌ በቃለ እግዚአብሔር ተቃውሜ ነበር።
471 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 04:26:43 የ“ምኵራብ” አገልግሎት ቢቀጥልስ?


የምኵራብ አገልግሎት፣ ባቢሎናዊው ንጉሥ ናቡከደነጾር፣ የአይሁድን መቅደስ አፍርሶ፣ ሕዝቡን ማርኰና አፍልሶ ወደ ባቢሎን ሲወስድ፣ ሕዝበ እስራኤል ከአምልኮ ማዕከል ከኢየሩሳሌምና ከመቅደሱ ፍጹም በመራቃቸው፣ ለጸሎትና ለማኅበርተኛነት ልዩ ቤት(ምኵራብ) መሥራትንና በዚያ ጸሎትና ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ለማምለክ ምኵራቦችን አስቀድሞ በባቢሎን ኋላም ደግሞ በኢየሩሳሌም መሥራት እንደ ጀመሩ ይታመናል፤ (ሕዝ. 11፥16)።[1]



ምንም እንኳ እስራኤል እንደ ደንበኛው አምልኮ፣ በምኵራቡ ውስጥ መሥዋዕትን ባያቀርቡም፣ ነገር ግን ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና መተርጐም ብሎም በዚያ መጸለይን ያዘወትሩ ጀመሩ። ምኵራብ ለመሥራትና ምኵራባዊ አገልግሎትም ለመመሥረት፣ ዐሥር ጐልማሳዎች በአንድ አከባቢ ካሉ፣ አንድ ምኵራብ በመሥራት የጋራ አምልኮ ይፈጽሙ፤ ኅብረትም ያደርጉበት ነበር።

የእስራኤል ቅሬታዎች ይህን በማድረጋቸው፣ የኪዳኑን ቃላት አልዘነጉም፤ ያህዌ ኤሎሂም ለእነርሱ የሰጣቸውን ተስፋዎች ከማሰላሰል ቸል አላሉም፤ ምድረ ርስትን አልረሱም፤ በኅብረት መያያዝን አልጣሉም፤ በቅዱሳት መጻሕፍት ንባብና በማንበብም ማምለክን አልሰለቹም፤ ይልቁን ተጉ፤ በረቱ፤ ጨከኑ፤ የያህዌ ተስፋ እስኪፈጸም በብርቱ መቃተት ቃተቱ!

ይህን የምኵራብ አገልግሎትን የሚመስል አገልግሎት፣ በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ እንደ ነበረ የሚያሳዩ ዋቢዎች አሉ፤ አንዳንዶች በታሪክ ጥናታቸው በአባ ሰላማ ወይም ፍሬምናጦስ እንደ ተጀመረ ሲያወሱ፣ ሌሎች ደግሞ በደቂቀ እስጢፋኖሳውያን መጀመሩን ይናገራሉ። አቡነ ጐርጐርዮስ፣ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ” በሚለው መጽሐፋቸው ላይ፣ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ፣ ካህናት የንስሐ ልጆቻቸውን በያሉበት መንደር ሄደው “ወንጌል” ሊያስተምሩ እንደሚገባ አዝዘዋል ብለው ጽፈዋል።

ያም ኾነ ይህ፣ ምኵራባዊ አገልግሎት ከዋናው የመቅደስ አገልግሎት በቁጥር አነስ ያሉ አማኞች የሚገናኙበትና አብረው በአንድነት አምልኮ የሚፈጽሙበት ዐውድማ ነው፤ በተሐድሶአውያን ዘንድ በተለምዶ የማኅደር አገልግሎት ተብሎ የሚጠራም ነው። ይህም ማለት በአንድ አከባቢ ያሉ አማኞች፣ ቁጥራቸው ከኹለት እስከ አሥራ ኹለት የሚጠጉ ኾነው፣ በአንድነት በአከባቢያቸው ባለ አንድ ስፍራ ተገናኝተው የሚጸልዩበት፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን የሚያነብቡበትና የሚያጠኑበት ነው።

ይህ እጅግ ብዙ ጥቅም አለው፤ ለምሳሌ፦ አማኞች ለአምልኮ የሚገናኙት በእሁዱ ወይም በተመረጡ ቀናት ብቻ አይደለም፣ ጸጋ ይከፋፈላሉ፣ ማን ምን ጸጋ እንዳለው ያስተውላሉ፣ በችግሮቻቸው ይወያያሉ፣ ይረዳዳሉ፣ ኅብረት በማድረግ ለእግዚአብሔር ክብርን ያመጣሉ፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ያጸናሉ … ወዘተ።

እናም እንደ አይሁድ ያለ፣ ወንጌል የምናጠናባቸው፣ የምንጸልባቸው፣ ጸጋ የምንከፋፈልባቸው … ክርስቲያናዊ የምኵራብ አገልግሎቶች ቢኖሩንና ብንጠቀምባቸውስ? ቢስፋፉስ? …

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ኹሉ ጸጋ ይኹን፤ አሜን” (ኤፌ. 6፥24)።

My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/03/blog-post.html
My Twitter link - https://twitter.com/Diyakon.../status/1626836348475940864...
445 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 01:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 22:22:07 ሰውነት ወደ እግዚአብሔር አያድግም፤ እግዚአብሔርነት ወደ ሰውነት አይወርድም። እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ሰው ደግሞ ፍጡር!
411 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:58:22
የብልጽግና "ወንጌል" አጋፋሪና አቀኝቃኝ መምህር ከኾንህ፣ ለሕዝባቸው ርኅራኄ አልባ ከኾኑት አብዛኞቹ ፖለቲከኞች እኩል ቅንጡ መኪና "ትሸለማለህ"፤ አገር በእርዛትና በረሃብ በሚታመስባት ምድር ላይ፣ የሚሊዮናት መኪና ስላቅን ሕዝብን በመናቅ የሚቀርብ ስድብ ነው። ይህን እያዩ እንኳ ለአገልጋይ ምርጡ ይገባል የሚሉ ስንት ተላላዎች አሉ?!
146 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 19:19:36
“... እናንተ የምትንቁ፥ እዩ ተደነቁም ጥፉም... ” (ሐ. ሥ.13፥40-41)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰባክያን "በፖለቲካና በዓለማዊ መድረኮች" ላይ ቀርበው፣ ዲስኩር መደስኮርን ተያይዘውታል። አሳዛኙ ነገር ደግሞ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ ግን የመጽሐፉን ቃል ሳይተረጉም የልባቸውን ዲስኩር ብቻ ደስኩረው ይወርዳሉ። አለመታደል!

ከሰሞኑ የአድዋ በአል መታሰቢያ ላይ፣ በአንድ ወቅት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርብ የነበረው ዶክተር ዮናስ ከላይ የጠቀስኩትን ጥቅስ ጠቅሶ ደሰኮረ።

ቃሉ የተነገረው በትንቢተ ዕንባቆም ምዕ. 1፥5 እና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ነው። ዕንባቆም ይህን ቃል የተናገረው፣ እግዚአብሔር ኀይል የተሞላበትን ሥራ ለመግለጥ በሚውል አገላለጥ ነው። ይሁዳ ስለ በደሏ ትቀጣለች፤ ለመቅጣት ደግሞ ጨካኝ ባቢሎናውያንን ያመጣል፤ ይህ ለዕንባቆም የማይታመን ቢኾንም፣ እግዚአብሔር ግን ቢነገራቸው ለማይሰሙ የማይቀረውን ፍርድ ይናገራል።

በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ደግሞ የተጠቀሰው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ለመሲሑ እንደ ተጠቀሰ በማውሳት ነው። ስለዚህም የኢየሩሳሌም ሰዎች በዕንባቆም የተነገረው ትንቢት፣ በእነርሱ እንዳይፈጸም ቅዱስ ጳውሎስ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ የተናገረው የመደምደሚያ ቃል ነው። የመሲሑን እውነት ቢንቁና ባይቀበሉ፣ ከይሁዳ በከፋ ኹኔታ የሚገጥማቸው አደገኛ ጠንቅ ነው።

ቃሉ እንዲህ ሊነገር ሲገባው፣ ዶክተሩ ግን ይህ ችላ ማለቱ ያሳዝናል። እናም ዲስኩርነትና የቃለ እግዚአብሔር ቃል ጠቀሳ ቢቀር ምናለ?! "ሰባኪዎች" ዲስኩር ባይደሰኩሩስ? የደጋፊ ጩኸትና ፉጨት ጥማት ካለብን ከቃሉ ሳንጠቅስ ሌላ "መድረኩን የሚመጥን ተራ ዲስኩር" ማቅረብ አይቻልም?

በቃለ እግዚአብሔር አትዘብቱ፤ ያውም ለመሲሑ በተነገረው ቃል ላይ አትቀማጠሉ!

ይልቁን፤ በመሲሑ ቃል ላይ፣ እንደ ቧልት የምትደሰኩሩ፣ እዩ ተደነቁ ጥፉ!
295 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 04:16:04 ቅንጡ "water parks"፣ የተንጣለለ ቤተመንግሥት፣ በሚሊዮናት የሚገዙ አውቶብሶች... ድብቅ ነውራችንን፣ ሰላም ጠልነታችንን፣ በጠኔ የጠወለገ ሕዝባችንን መልክ አያስውበውም! ከቁስ ይልቅ ሰው ይቅደም!
218 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 01:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 21:08:07 እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል በራልኝ፤ ስለዚህም አወቅኹት። እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ባይገለጥልኝ መቼም አላውቀውም ነበር!
የእኔ ጌታ ተባረክ
190 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ