Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-08 23:23:16 ከኢየሱስ በቀር በማስተዋል ብርሃን ሕዝቡን የሚመራ ንጉሥ ሌላ የለም፤ አሜን።
383 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 21:39:33 ዕቅበተ እምነት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ወጥና በፍቅር የታነጸ ድፍረት ሲላ*በስ እንጂ "ጨዋ መሳይ[ዕውቀት ቀመ*ስ] ልዝ*ብ*ነትን ሲደ*ርት" ይጎ*ፈንናል!
189 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 14:51:54 ኢየሱስን በዓይነ ሥጋዬ ባላየውም እንኳ፣ እጅግ እወደዋለሁ፤ እጅግም እታመንበታለሁ። (1ጴጥ. 1፥8)
394 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 06:57:56
ኢትዮጵያ የምትባል አገር ውስጥ፣ ቢሊዮናት ብር ወጥተው የቱሪስት ማዕከላት ይገነባሉ፣ ቅንጡ የመዝናኛ ስፍራዎች ይታነጻሉ፣ ትንንሽዬ ቤቶች ካሜራ ተደቅኖባቸው ፈርሰው "በመንግሥት በጀት ተሠሩ" ተብሎ ትልልቅ ወሬ ይሠራባቸዋል...። ከካሜራ ጀርባ ግን ትውልድ ይፈርሳል፣ ሕፃናት እንደ አረጋዊያን በተስፋ መቁረጥ ይተክዛሉ፣ ቅጥ ያጣ ሐዘን በየሥፍራው አለ። ኢትዮጵያንም ኾነ መላለሙን የሚያድን እጅ፣ ክፉዎችና አስመሳይ ግብዞችን ደግሞ የሚቀጣ ክንድ ከሰማይ ስለ መኖሩ፣ ያስተዋለ ምንኛ የታደለ ነው!
432 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 20:32:10 “የሴት ትሸፈን” ትእዛዝ፣ ለአገልጋዮች ምን መልእክት አለው?


ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው “ሥርዓታዊ ትእዛዞች” አንዱ፣ “ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።” (1ቆሮ. 11፥6) የሚል ነው። “ሥርዓታዊ ትእዛዙ”፣ በአምልኮ ሰዓት ሴቶችም “ኾኑ ወንዶች” ተገቢውን ልብስ ለብሰውና የባሕርይ ሥርዓትን መከተል እንዳለባቸው የሚያሳስብ ነው።



አንዳንዶች፣ ይህ ሥርዓታዊ ትእዛዝ ለቆሮንቶስ ብቻ የተጻፈ እንጂ የእኛን ዘመን ቤተ ክርስቲያን አይመለከትም ቢሉም፣ ሌሎች ግን የእግዚአብሔር ቃልና ሐዋርያዊ ትውፊቶች ዘመን ዘለቅ ናቸውና የእኛንም ዘመን ቤተ ክርስቲያን ይመለከታታል በሚል ጐራ መሳ ለመሳ ቆመው ይሟገታሉ። ይህ አጭር ጽሑፍ እነዚህ ኹለቱ ሙግቶች መልስ ለመስጠት የተጻፈ አይደለም፤ ይልቁን የታዘዘበት ዓላማ ላይ በማተኰር ለእኛ ያለውን መልእክት ለማስታወስ እንጂ።

በአዲስ ኪዳን ጅማሮ ላይ ከነበሩት አብያተ ክርስቲያናት፣ እንደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ያለ በችግርና በታወቁ ኀጢአት የተመላ አልነበረም፤ የዚያኑ ያህል እንደ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በጸጋ የተምነሸነሸና ጸጋን የታደለ የለም ብሎ መናገር ይቻላል። በቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ከነበሩት ችግሮች ወይም ለጳውሎስ ከቀረቡለት ጥያቄዎች አንዱ የአለባበስ ጉዳይ ነበረ። ለዚህ ችግር ምንጩ ደግሞ፣ በተለይ “ረጅም ጸጉር” የነበራቸው ሴቶች፣ ፀጉራቸውን ሳያስይዙ ወይም ሳይሸፍኑ አዘናፍለው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መገኘታቸው ነው። በዘመኑ ኹለት ዓይነት ሴቶች ነበሩ፣ አንደኛዎቹ ባሎቻቸውና ልጆቻቸው ላይ ትኵረታቸውን ያደረጉ፣ ራሳቸውንም በመሸፈን የሌሎችን ትኵረት የማይስቡ ሲኾኑ እኒህ “ማትሮን” ይባላሉ፤ ብዙ ከበሬታም ነበራቸው። ኹለተኛዎቹ ግን “ሔታይራይ” የሚባሉት ሲኾኑ፣ ሳያገቡ ወይም ነጻ ኾነው ብዙ ወንዶችን በቤታቸውን የሚያስተናግዱና በውጭ ሲታዩም የማይሸፋፈኑ፣ ፀጉራቸውን ቀለም የሚቀቡ ወይም እጅግ ባጌጠ ሹርባ በመሠራት የወንዶችን ትኵረት በመሳብ የአመንዝራነት ጠባይ ያላቸው ናቸው። በርግጥም በዚያ ዘመን አለመሸፋፈን፣ የአልቃሽነት ወይም የዘማዊነት ምልክት ነበር።

በሌላ ንግግር በወንጌል ያመኑ አንዳንድ ሴቶች፣ መሸፈኑን ያልወደዱት ልክ አንዲት አመንዝራ ወይም ጋለሞታ ሴት በመጋላለጥዋ የሌሎችን ወንዶች ትኵረት ለመሳብ እንደምታደርገው እነርሱም የሌሎችን ትኵረት ለመሳብ መሸፋፈንን ወይም መከናነብን ተዉ። ነገር ግን አማኝ ሴቶች የሚገባቸው፣ እንደ አመንዝራ ሴቶች የሌሎች ትኵረት እነርሱ ላይ እንዲኾን ከመፈለግ ይልቅ፣ በማናቸውም መንገድ ሰዎች ትኵረታቸው ኹሉ ወደ ክርስቶስ እንዲኾን መሥራትና መትጋት ነበረባቸው።

ቅዱስ ጳውሎስ የሴትን ልጅ መሸፋፈን በመደገፍ፣ መደገፉንም በጥቂቱ በኹለት ምክንያቶች ያስረግጣል፤ አንደኛው የሴት ልጅ መሸፈን ተፈጥሮአዊ ነው፤ በሌላ መልኩ ግን ሴት ስትሸፈን፣ “እኔ ትኵረት ልኾን አይገባም፤ ክርስቶስ ብቻ እንጂ!” ማለትዋም ነው። የሚገላለጡና የማይሸፋፈኑ ሴቶች፣ ባጌጠ ሹርባና በደመቀ ቀለም የሚዋቡ ሴቶች “እኛ ትኵረት ልንኾን ይገባል” እያሉ ነው፤ በወንጌል ለሚያምኑ ሴቶች ይህ የተገባ አይደለም፤ ቅዱስ ጴጥሮስም፣ “ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የኾነ ሽልማት አይሁንላችሁ፥” (1ጴጥ. 3፥3) በማለት መክሮአል።

ለአማኞች ኹሉ ትልቁ ትኵረትና ድምቀታቸው ክርስቶስ ሊኾን ይገባል፤ ክርስቶስን በማላቅና በማተለቅ አገልግሎት ውስጥ እኛ ልንሰወርና ልንጠፋ ይገባናል። ነፍሱን ስለ ክርስቶስ የሚያጠፋ እርሱ ያገኛታል፤ ነፍሱን ከክርስቶስ ይልቅ ለማተለቅ፣ ሳስቶ ለማኖርና መኖርዋንም ለሌሎች ለማሳየት የሚጥር ነፍሱን አያያትም! አገልጋዮች ሆይ! እናንተ ወይስ ክርስቶስ ትኵረት እንዲኾን ትፈልጋላችሁ? እናንተ ተሸፋፍናችሁና ተደብቃችሁ ክርስቶስ ግን እንዲታይና እንዲገለጥ፤ ከፍ እንዲልም ትፈልጋላችሁ? ከዝማሬያችሁ፣ ከስብከታችሁ፣ “ከተናገራችሁት ትንቢት”፣ ካመጣችሁት መልእክት በኋላ … ራሳችሁን ፈጥፍጣችሁ መጣል ይሻላችኋል ወይም በኹሉ ነገራችሁ ክርስቶስ ዋና ትኵረትና ድምቀት እንዲኾን ትፈልጋላችሁ? … የቱ ይሻላችኋል? ክርስቶስ ብቻ ቢደምቅ ወይስ እናንተ ብትሸፈኑና ብትሸፋፈኑ?!

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/04/blog-post.html
600 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 12:05:47 “እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባል” (ዮሐ. 3፥30)


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪደተ እግሩ ተመላልሶ ባስተማረበት ወቅት፣ ስለ ራሱ የሰጠውን ምስክርነት የተቀበሉ ጥቂቶች ናቸው። ምስክርነቱን ያልተቀበሉት እርሱ እውነተኛ ስላልኾነ ሳይኾን፣ ብዙዎች ከኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ይልቅ የጨለማ ሥራን በመምረጣቸው ነው፤ (ዮሐ. 1፥6-11)። መጽሐፍ እንደሚል፣ ኢየሱስን የደኅንነታቸው ምንጭ አድርገው የተቀበሉ ሰዎች፥ እግዚአብሔር ለዘላለም ለልጆቹ የሚሰጠውን ልዩ ሕይወት ያገኛሉ። ይህን የማይቀበሉ ግን ለዘላለም ፍርድና ቍጣ የሚጠብቃቸው ናቸው።



መጥምቁ ዮሐንስ በዚህ ረገድ ስለ ኢየሱስ የተናገረው ምስክርነት ግልጽና የማያወላዳ ነው። ስለ ራሱ ሲናገር፣ ራሱን በመካድና በኢየሱስ ፊት ፍጹም በማሳነስ ነው። የመሪዎችና የአማኞች ትልቁ ችግር ራስ ወዳድነት ነው። ሰው ራሱን ካልካደ በቀር ኢየሱስን ማላቅና ከፍ አድርጎ ማክበር አይችልም።

ራስ ወዳድነት ፈርጀ ብዙ ነው፤ አንዳንዶች የራስ ወዳድነት ምንጫቸው ራሳቸውን ከማተለቅና ከገንዘብ መውደድ ሊመነጭ ይችላል። ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ሥራ ለማበላሸትና ራሳቸውን ከፍ ለማድረግ ከሚሠሩት ሥራ የተነሣ እጅግ ራስ ወዳድ ሊኾኑ ይችላሉ። እኒህና በሌሎች መንገዶች የሚንጸባረቁ ራስ ወዳድነቶች እጅግ አደገኛና መራዥ ናቸው።

መጥምቁ ዮሐንስ ለኢየሱስ ዘመድና የቅርብ ወዳጅ ነው፤ በአገልግሎትም ኾነ በዕድሜ ጌታችን ኢየሱስን ይቀድመዋል፤ በአይሁድ ማኅበረ ሰብና በሮማውያን ባለሥልጣናት ዘንድም ከፍተኛ ተደማጭነት ነበረው።

በተደጋጋሚ ሰዎች ከኢየሱስ ይልቅ ክብሩን በእነርሱ ፊት እንዲገልጥ ዮሐንስን ጐትጉተውታል፤ እንዲያውም ከመጥምቁ ዮሐንስ ይልቅ፣ ኢየሱስ ሊልቅ፣ ዮሐንስ ደግሞ ዝቅ ዝቅ ሊልና ሊያንስ እንደሚገባ ተናገረ እንጂ በመቅናት የኢየሱስን አገልግሎት ሊያደናቅፍ ፈጽሞ አልፈለገም።

አገልጋዮች በሰዎች ልብ ሲገንኑና ሲተልቁ፣ ኢየሱስ በአገልግሎታቸው ይደበዝዛል፤ መሪዎችና አገልጋዮች ዝቅ ዝቅ ሲሉና ኢየሱስን እጅግ ሲያተልቁ ከክርስቶስ የተነሣ በሰዎች ልብ እግዚአብሔር ይከብራል፤ መንግሥቱም ትሰፋለች። መጥምቁ ዮሐንስ ይህን በሚገባ ያስተዋለ የጌታ አገልጋይ ነው።

ፍሬያማ አገልጋይ ለመኾን ዮሐንስ፣ ኢየሱስን ባገለገለበት መንገድ ልናገለግል ይገባናል፤ እንዴት?

1. ኢየሱስ ከሰማይ ነውና ዘወትር ሊገንና ሊከብር ይገባል፤ እኛ ኹላችን ከምድር ወይም ፍጡራን ነን፤ እርሱ ግን ታላቅና ገናና ከሰማይ የኾነ አምላክ ነው።

2. “እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።” (ዮሐ. 3፥30) የተባለለት ኢየሱስ ብቻ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ሲናገር እንከን የማይገኝለት፣ የታመነና የታተመ ምስክርነት ያለው ኢየሱስ ነው።

ከዚህም የተነሣ እውነትን በትክክል መናገር የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው፤ ምከንያቱም እግዚአብሔርን ያየም ሆነ የመንግሥተ ሰማይን እውነቶች ኹሉ የሚያውቅ እርሱ ክርስቶስ ብቻ ነው። የኢየሱስ ቃል የእግዚአብሔር ቃል በመኾኑ ልንታዘዘው ይገባል። እግዚአብሔር ለማንም የሰው ልጅ ያልሰጠውን መንፈስ ቅዱስን በምልአት ለክርስቶስ ሰጥቶታል። እግዚአብሔር ክርስቶስን ስለሚወደው በምድር ላይ ሥልጣንን ሰጥቶታል። እናም ዘወትር ሊልቅና ሊገንን የሚገባው፣ ትኵረት ሊሰጥም የሚገባው ለክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ነው!

3. ኢየሱስ ኹሌም ትኵረት የሚገባው ሙሽራ ሲኾን፣ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ ሚዜ ነው። የዮሐንስ ደስታ የኢየሱስ ፈቃድና ዐሳብ በትክክል ሲፈጸም ነው። ዮሐንስ ከዚህ በቀር ሌላ ደስታ የለውም። በኢየሱስ አገልግሎት ብዙ ተከታይ ሲገኝ፣ የዮሐንስ ተከታዮች ደግሞ እየቀነሱ መኾኑን ቢያውቅም ዮሐንስ ግን በዚህ እጅግ ደስተኛ ነበር። ለዚህም ነው “እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባኛልና” በማለት የተናገረው።

የአደባባይ ጉባኤያትን የሚያደርጉ መሪዎችና አገልጋዮችን ከምንመዝንበት መመዘኛ ውስጥ አንዱ፣ “በአገልግሎታቸው ይበልጥ አነጋጋሪና ታዋቂ እየኾነ ያለው ማን ነው? ትኵረት እየሳበስ ያለው ማን ነው? … “ የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ጥያቄዎች ናቸው።

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24) https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/03/330.html
194 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:56:13 ወንጌል፣ የኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ጅማሬውም፤ ፍጻሜውም የኾነ ብቻ ነው!
125 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 12:10:56 ኦርቶዶክስን ስት*ነቅፍ መንጋ ተከታይ አለህ፤ "ወንጌላውያን አልያ ሐዳስያን" ሳይኾኑ ነን ከሚ*ሉ የአንዱን ኑፋ*ቄ ወይም የታወቀ ነው*ር ከተቃወምህ፣ ደጋ#ፊዎቻቸው ሊቃወሙህ አያማትሩም! የደጋፊ አባዜ!
220 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 20:30:09 "እኔ ስብከት ሰምቼ ወይም ሰውም ነግሮኝ ከኦርቶዶክስ አልወጣሁም ራሱ ጌታ አስተምሮኝ ወጣሁ እንጂ" ሲልህ፣ "አሜን" ካልህ፣ ዕውርን ዕውር መራው ማለት ይህ ነው!
278 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 13:52:34
መስኪ ይቅርታ! ... ሌላ ኢየሱስ ከሚሰብኩ ግን ተጠንቀቁ!

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል እንዲህ ይላል፣

“... አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ የሰበክነውን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም እናንተ የተቀበላችሁትን መንፈስ ሳይሆን ሌላ መንፈስ ብትቀበሉ፥ ወይም የተቀበላችሁትን ወንጌል ሳይሆን ሌላ ወንጌል ብትቀበሉ፥ ዝም ብላችሁ ተሸነፋችሁ ማለት ነው።” (2ቆሮ. 11፥3-4)።

ቅዱስ ጳውሎስ፣ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ ታማኝ ኾና ላትቆይ እንደምትችል ስጋቱንና፣ የስጋቱን ምክንያት ሲያቀርብ፣ ሐሰተኛ መምህራን፣ ቅንነትንና ታማኝነትን የሚያበላሽ ባሕርይ እንዳላቸው አስረግጦ በመናገር ነው። እባብ ወደ ገነት ሰርጎ እንደ ገባው፣ የሐሰት መምህራንም አገባባቸው ሾልኮ ከበር ውጭ በኾነ በጓሮ “በር” ነው። እንዲህ ሲነገር የሚከፋቸው “ክርስቲያኖች” አሉ፤ ጥላቻ፣ ቅንአት፣ መበላለጥ የሚመስላቸው ተላላና ዳተኞች አሉ።

ለዚህም ነው፣ ከሰሞኑ “የብልጽግና ወንጌል አቀንቃኙ”ና የጃፒ ደቀ መዝሙር የኾነው በጋሻው ደሳለኝ፣ ያለ ፈቃድዋ የእህት ዘማሪ መስከረምን የራሱ ጉባኤ ማስታወቂያ ፖስተር ለጥፎ፣ ዘማሪዋ ግን ሌላ ጉባኤ ላይ በመገኘት “የብልጽግና ወንጌሉን ጉባኤ” በመቅረት እንቢታዋን አሳይታለች፤ በእርግጥ ወንድም ስንታየኹ በቀለ “መስከረም አታደርገውም!” ብሎኝ ነበር፤ በትክክልም እርሱ እንደ ተናገረው አድርጋዋለችና፣ ዘማሪት መስከረምን ይቅርታ በመጠየቅ አቋሟን በመደገፍ ይህን ጽፌአለሁ።

ዛሬም ግን ደፍረን እንናገራለን፤ በኢየሱስ እንዳላረፈ ሰው “አዲስ ትምህርት ለመስማት የምንቸኩል” ቆሮንቶሳውያን አይደለንም፤ አዎን፤ አንድ ክርስቶሰ፣ አንድ መንፈስና አንድ ወንጌል ብቻ እንዳለ እናምናለን፤

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)
314 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ