Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-07-07 20:20:38 ፖለቲከኞች ሺዎች ቢሞቱ ሰበብ አላቸው፤ ኢየሱስ ብቻ ግን አንድ በግ(ሰው) ቢጠፋበት አንዱን ፍለጋ የምድር የታችኛውን ዝቅታ ይወርዳል። ምድር ሆይ፤ ወደ አዛኝሽ ኢየሱስ መመለስ ይበጅሻል!
554 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 16:57:26 reverend(አባ አባት) ብዬ የምጠራው ያህዌ ኤሎሂምን ብቻ ነው፤ በዚህ ስም ሊጠራ የሚወድድ ፍጡር ቢኖር እርሱ ትዕ*ቢተኛና እቡ*ይ፤ ያህዌን ልኹን ባይ ነው!
300 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 23:02:30 ከኀጢአት በቀር የሰላም፣ የዕርቅ፣ የበጎ ነገር ኹሉ ምንጭ፤ መገኛ፤ ሰበብ፤ ምክንያት፤ መሠረት... ክርስቶስ ኢየሱስ ነው! ምድር ሆይ፤ ወደ መሠረትሽ ተመለሺ!
374 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 20:42:04 እነዚያ የኾነ "church" ፈረሰ ብለው የተንጋጉትና የሰው መታረድ የማያንገበግባቸው ፓስተሮች እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ናቸው አ ? (ሰው የማይገዳቸው ኾነው እናገለግላለን ሲሉ ይሰቅቃሉ )
395 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:15:22 ነገር ግን ትርክቱ እጅግ እርስ በራሱ የተሳከረ ነው፤ በድርሳነ ዑራኤል የቴዎድሮስን መንገሥ የሰማው የኤርምያስ ረድእ የነበረው ባሮክ ከኾነ፣ በዚያው ክፍል ውስጥ ደግሞ መልሶ ከማርያም ጋር መያያዙ ግራ ያጋባል። ገድለ ፊቅጦር ደግሞ በኢትዮጵያ ፍጹም ሰላምና ጥጋብ እንደሚኾን ሲናገር፣ ይህ ከመኾኑ በፊት ግን በምድሪቱ ላይ ለብዙ ዓመታት ዓመድ እንደሚዘንብ ይናገራል። የኹሉም ትርክት ሲጠቀለል፤ በንጉሡ ዘመን ሰላምና ጥጋብ የሚኾነው በ“ቴ” ወይም በ“ቶ” ምልክትነት ነግሦ ከመጣ በኋላ ነው።

3. የኢየሩሳሌም ዩንቨርሲቲ አጥኚዎች፣ ይህ የ“ቶ” ምልክት በብሉይ ኪዳን ውስጥ በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን በተሠራ ሸክላ ላይ ታትሞ መገኘቱን ይናገራሉ። [2] ስለዚህም ምልክቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ የታወቀ ምልክት ሊኾን ይችላል። ይህም ከአማልክት አምልኮ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል መገመት ይቻላል።

እንግዳ አማልክቶችን ከመከተል ተጠበቁ

እንግዲህ በዚህች አጭር ዕይታ፣ የ“ቶ” መስቀል ክርስቲያናዊ አንዳችም ምልከታ የለውም፤ በግልጽ አማልክት ወዳድና ከክርስትና ውጭ ያሉ ሰዎች ይገለገሉበት የነበረ መኾኑን ማስተዋል ይቻላል። ነገር ግን ዛሬ ላይ ክርስትናን እንከተላለን የሚሉ ይህን ምልክት ያለበትን በአንገታቸው አስረው ሲሄዱ እንመለከታለን። በርግጥ እኒህ ሰዎች የአማልክትን መንገድ ይከተላሉ ብንል ማን ሊወቅሰን ይችላል?






ማጠቃለያ

የክርስትና ዋና ስብከት፣ የተሰቀለው ክርስቶስ ስብከት ነው። ከዚህ ስብከት ውጭ ሌላ ስብከት፤ ሌላ ዓርማም ሊኖር አይገባም። በሥጋችን ተሸክመን የምንዞረውና ለዓለሙ ኹሉ የምሥራች ብለን የምንሰብከው፣ የክርስቶስን ኢየሱስን መስቀል[መሥዋዕታዊ ሞት] ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው የክርስቶስን መስቀል የሚጋርድና የሚያኮስስ ነው። ወደ እውነተኛው መስቀልና ሕይወት መመለስ ይኹንልን፤ አሜን።


[1] Rivka Ulmer; The Egyptian Gods in Midrashic Texts, The Harvard Theological Review፤ Vol. 103, No. 2; 2010; p. 185 እና Umberto Cassuto. Perush ‘al sefer shemot; 1965; Jerusalem: Magnes; pp. 72-73

[2] The Hebrew University of Jerusalem Website, Impression of King Hezekiah’s Royal Seal, Retrieved on October 2017.


My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/2021/09/blog-post_25.html
434 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:15:22 በላይ በቀለ ወያ በመፈታቱ (እንደ ሰው) ደስ ብሎናል፤ ይኹንና የ“ቶ” መስቀልን በስፋት ከሚጠቀሙ አንዱ ነው፤ እንደዚያውም ደግሞ “ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን” ነኝ ሲል እንመለከተዋለን፤ ነገር ግን “ክርስቲያናዊ ምልክት” አለመኾኑን ከዚህ በታች አቋሜ አመለክታለሁ! ...

“ቶ”


ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በአንገታቸው የመስቀል ምልክትን የሚያስሩ ብዙዎች፣ “ቶ” ምልክት ያለውን በአንገታቸው ማሰርን በአደባባይ እየተመለከትን ነው። “ቶ” ምልክት ያለው ብቻ ሳይኾን፣ ሌሎችም እንግዳ ድርጊቶች ሲከሰት፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶና በሌሎችም አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት ሲከናወን ዝም ማለት አልያም አንዳችም ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ፤ ነገሩ ከእንቁላል ወደ ጫጩት እስኪያድግና ብሎም እስኪጐለምስ ችላ ማለት እንግዳ ተግባርም አይደለም።




የመጽሐፍ ቅዱሱ ክርስትና፣ መስቀል ሲል ዋናውን ትርጕም በመከተል፣ የክርስቶስን የማዳን ኹለንተናዊ ተግባርን በመወከል ይሰብካል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀሉ፣ የክርስትና ዋና ማዕከልና የመዳናችን ቱንቢ ነው። እግዚአብሔር ለወደቀው ዓለም ርኅራኄውን የገለጠው አንድያ ልጁን በመስቀል ላይ አሳልፎ በመስጠት ነው። አንድያ ልጁም “ስለ እኛ ነፍሱን የሰጠው” (ዮሐ. 10፥11፤ ቲቶ 2፥14) እጅግ ኃጢአተኞች፣ ደካሞች፣ ጠላቶች፣ በበደላችንና በኃጢአታችን ሙታን፣ ዐመጸኞችም ሳለን ነው፤ (ሮሜ 5፥6፡ 8፡ 10፤ ኤፌ. 2፥1፤ 1ጴጥ. 3፥18)።


ለዚህ ነው አራቱም ወንጌላውያን በአንድነት ተባብረው ስቅለቱንና ሞቱን በታላቅ ርዕስነት የሚያነሡት። አዎን፤ የመሲሑን ልደት፣ የልጅነቱን ሕይወት ኹሉም ወንጌላውያን አልተረኩትም፤ መስቀሉን ግን ተባብረው በአንድ ቃል አጽንዖት ሰጥተው ተርከውታል። ምክንያቱም መስቀሉ[መሥዋዕታዊ ሞቱ] የክርስትና ዋና ጭብጥና ትምህርት፤ ፍጥረተ ዓለሙ የተዋጀበት እንከንና ነቅ አልባ ቤዛና ዋጆ ስለ ኾነ። የክርስቶስ መስቀል የሌለበት ክርስትና፣ እርሱ ክርስቶስ ያስተማረንና ተሰቅሎ ያሳየን ክርስትና አይደለም። መጽሐፍ በግልጥ ቃል ልዩ ወንጌልና ልዩ ኢየሱስ እንዳለ ሲነግረን፣ “ … የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥” (2ቆሮ. 11፥4) በማለት ያሳስበናል፤ ልዩ ኢየሱስና ልዩ መንፈስ ካለ፣ ልዩ መስቀልም ሊኖር እንደሚችልም መዘንጋት አይገባም።

ክብር ይግባውና፣ የተሰቀለው ጌታችን ኢየሱስ ለእኛ ሕይወታችን ነው፤ በእርሱ በስቁሉ ተወዳጅ መሲሕ መሰቀልም ተነግሮ፤ ተሰፍሮ የማያልቁ በረከቶችና ጸጋዎችን ማግኘታችንን መዘንጋት የለብንም፤ ጥቂቱን ብንጠቅስ፦

· በደላችንና ኃጢአታችን በእርሱ መሰቀል ተሰረየ፤

“ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።” (ማቴ. 26፥28)

“እርሱንም [ክርስቶስ ኢየሱስንም] እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው” (ሮሜ 3፥25)

“መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ …” (1ቆሮ. 15፥3)

“በውድ ልጁም እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን በደሙ የተረገ ቤዛነታችንን አገኘን፤ እርሱም የበደላችን ስርየት” (ኤፌ. 1፥7)

“ክርስቶስ ደግሞ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሠዋ በኋላ …” (ዕብ. 9፥28)

“ለወደደን ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን …” (ራእ. 1፥6)

· ተቃዋሚያችን ከመንገድ ተወግዶበታል፤

“በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤” (ቈላ. 2፥14)

· ዱካውን እንድንከተል በመሰቀሉ አሳይቶናል፤

ጌታችን ኢየሱስ ሲያስተምር በግልጥ ቃል እንዲህ አለ፤ “መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።” (ማቴ. 10፥38)። ልክ እርሱ እስከ ሞት ባለፈበት መንገድ አማኞችም ሕይወታቸውን እስከ ሞት ድረስ ጭምር ስለ ኢየሱስ በመስጠት ሊያልፉበት እንዳላቸው ተናገረ። ቅዱስ ጳውሎስም እንደ መሰከረው፤

“የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስለ አለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብ. 12፥2)

እኒህና ሌሎችንም አያሌ በረከቶችን የሰጠን የመሲሑ መስቀል(መሲሐዊ የሥጋ ሞት)፣ ተዘንግቶና ተረስቶ ዛሬ ላይ “እንጨቱን መስቀል” ማለትም፣ የተሰቀለበት እንጨት ዋና ትኵረት አጊኝቶ ስናይ እጅግ እናዝናለን። ክርስቶስ መሰቀሉና የዘመናትን ቀንበር ማንከባለሉና ፍጹም ነጻነትን በመሥዋዕታዊ ሞቱ መስጠቱ፣ እንደ ዋዛ ቀልሎና ታልፎ፣ እንጨቱን አልቀው ሰዎች ማየታቸው እጅግ ያስደንቃል። በርግጥ መስቀሉን ምልክት ማድረግ፣ አሉታዊ በኾነ መንገድ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ቢታወቅም፣ በተለይም ከመስቀሉ ጦረኞች ጋር በተያያዘ አብያተ ክርስቲያናት አርማውን መጠቀማቸው የተለመደ ነው። ነገር ግን የውርደትንና የመከራውን ዓርማ መጠቀም ዋናውን ጥሎና ዘንግቶ መኾን አልነበረበትም።

የ“ተ” ምልክት መስቀሉ፣ የክርስቶስን መሥዋዕታዊ ሞት ቦታን ተክቶ መውረሱ ሲደንቀን፣ ከዚህ የከፋውና እንግዳው ነገር ደግሞ፣ የ“ቶ” ምልክት እንግዳ የአንገት ጌጥ መምጣቱ ነው።

የ“ቶ” ምልክት “መስቀል” ምንነት

የ“ቶ” ምልክት ምንነት አያሌ ትርክቶች አሉት፤ ጥቂቶቹን ብናነሳ ከዚህ በታች እንዲህ ማስቀመጥ እንችላለን።

1. በጥንት ግብጽ ውስጥ “ራ” የፀሐይ አምላክ ነው፤[1] ይህን አምላክ ስሙን ጠርቶ ለሚለምነው፣ በእጆቹ በ“ቶ” ምልክት ከያዘው “መስቀል” በጨረር ፍንጣቂ፣ ሕይወት፣ ጥበብና ኃይልን ለአማኞቹ ኹሉ ያድላል፤ ይሰጣል ተብሎ ይታመናል። የዚህ ፀሐይ አምላክ አገልጋይ ካህናት የ“ቶ” ምልክትን በእጆቻቸው ይዘው ጣዖቱን ለማገልገል ይገደዳሉ። “ራ” በአምላካዊ ማንነቱ በፀሐይ ውስጥ ኾኖ “ቶ”ን ይይዛል። “ቶ” ደግሞ ዘወትር ሃይልን፣ ዕውቀትንና ጥበብ የተመላ ነው። ስለዚህም የ“ቶ” ምልክት በቀጥታ ከአማልክቱ አምልኮ ጋር የሚገናኝ መኾኑ አያሌ ማስረጃዎች አሉ።







እንግዲህ ይህን ምልክት እንደ መስቀል በአንገታቸው የሚያስሩ ራሳቸውን እንዲመረምሩ ብንልስ?


2. የጥቅምቱ ድርሳነ ዑራኤል፣ ፍካሬ ኢየሱስ፣ ገድለ ሲኖዳ፣ መጽሐፈ ምስጢርና ገድለ ፊቅጦር የሚተርኩት እጅግ እንግዳ ትርክት ደግሞ አለ። በተለይም ከ“ኢትዮጵያ ትንሣኤ” ጋር በማያያዝ። በገድለ ፊቅጦር ስለሚፈርሰው መቅደስና በኢትዮጵያ ስለሚነግሠው ቴዎድሮስ ስለሚባለው ንጉሥ የተገለጠ ራእይ እንዳለ ይናገራል። በድርሳነ ዑራኤል ደግሞ የቴዎድሮስን መንገሥ የሰማው የኤርምያስ ረድእ የነበረው ባሮክ ነው ይላል። እርሱም 40 ቀንና ሌሊት ጾሞ እንደ ተነገረውም ጭምር ይናገራል።

ይህ በ“ቶ” ምልክት የሚነግሠውና የስሙ መጀመሪያ በ“ቴ” ስም የሚጀምረው ንጉሥ በመንገሡ፣ ኢትዮጵያና ግብጽ ያልፍላቸዋል፤ እርሱም የአሕዛብን ነገሥታት ኹሉ ይደመስሳል። የመከራውን ዘመን ኹሉ ያሳልፋል ይላል እጅግ ሰፊው የመጻሕፍቱ ትርክት። ይህ ንጉሥ በሚነግሥበት ዘመን እንኳን ሰውና፣ ጠማማ እንጨት እንኳ አይኖርም በማለት ጭምር የንጉሡን ዘመን ፍጹም ያደርጉታል።
397 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:44:23 ይህ ኹሉ ግድያ ሲፈጸም፣ መንግሥት ይቅር፤ የሃይማኖት አባቶች የሉም ወይ? መግደል የሚጠየፍ "ሃይማኖተኛ" ሕዝብስ የለም ወይ?!... እውን ኢትዮጵያ ናት "የሃይማኖት" አገር?!
357 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 06:55:13
አንችልም!

ሰው ኹሉ ተደፍቶ ፍግም ብሎ ቢሰግድ፣
እኛ ግን አንችልም ለኢየሱስ እንጂ ለፍጡር መንበርከክ!
428 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 19:01:16 በአሜሪካ ለ50 ዓመታት የቆየው የውርጃ ሕግ መሻሩ!


እግዚአብሔር በማናቸውም መንገድ የሰው ልጅ እንዲገደል አይፈልግም። ከታላላቆቹ ሕጎች መካከል አንዱ፣ “አትግደል” የሚለው ሕግ ነው። የሰው ልጆች ደግሞ በተቃራኒው፣ የሰውን ልጅ ለተለያዩ የገቢ ምንጭነትና የዓመጽ ሥራ በብርቱ ጭካኔ ከሚገድሉበት መንገድ አንዱና ዋነኛው፣ ውርጃ ከፊቶቹ ተርታ ይመደባል። ውርጃ በግልጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ቢከለከልም፣ ተፈጥሮን የሚቃረን ቢኾንም እጅግ በሚዘገንን መልኩ አያሌ የውርጃ ተግባራት እንዲተገበሩ ብዙ ብሮች ይፈሱበታል፤ ሰዎች ተግባሩን እንዲፈጽሙ በሕግ ጭምር ከለላ ይደረግላቸዋል። ይህን በማድረግ ከሚታወቁት መካከል ግንባር ቀደሟ አሜሪካ አንዷ ናት። እናም ለ50 ዓመታት በሕግ ከለላ ሰጥታ ትፈጽም የነበረውን የውርጃ ሕግ፣ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ሽረውታል።


ይህ ውሳኔ የሴታዊነት (Feminism) አስተሳሰብ የሚደግፉትን ብዙዎችን ከማስቈጣቱም ባሻገር፣ ግብረ ሰዶማውያንን ውሳኔው እጅግ አበሳጭቶአቸዋል። ለዚህ ውሳኔ መወሰን ምክንያቱ ደግሞ፣ በፍርድ ቤቱ ውስጥ የተሾሙት ዳኞች ክርስቲያኖችና የውርጃ ተቃዋሚዎች መኾናቸውን ብዙ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች አስተጋብተው ዘግበውታል።

እንግዲህ፣ የአሜሪካው ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ አሜሪካ ለሃምሳ ዓመታት ያህል ትገለገል የነበረበትን የውርጃ ሕግ መሻሩ፣ ጠንካራ አማኞችና በመልካም ሞራል የዳበረ ሥነ ምግባር ያላቸው ዳኞችና ሕግ አውጪዎች ሥፍራውን የመያዝ ዕድል ቢኖራቸው ወይም በተመሳሳይ መንገድ እንዲህ ያለውን ተግባር የሚጸየፉ ሰዎችን “እንዲፈጠሩ” ብናበረታታና በብዙ ብንጥር፣ እንደ ገብረ ሰዶማዊነትና ውርጃ ያሉ ሕጎችንና መብቶችንም ጭምር የሚሽሩ “የሰላም ሰዎች” ይነሳሉ ብለን እናምናለን። ደግሞም እግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌታ እንደ መኾኑ፣ ከወሰኑ ሳያልፍ ዓመጽን እንዴት እንደሚቆጣጠር ከምናስተውልባቸው መንገዶች አንዱም ጭምር ነውና በዚህ ጌታን እጅግ አድርገን እናከብራለን።




በተለይም ደግሞ እንደ ባላደራ፣ ምድራችንን የደም ምድር ከሚያደርጋት ክፉ ዓመጽ ከውርጃ ራሳችንን ጠብቀን፤ ሌሎችም እንዲርቁ የሚጠበቅብንን ኹሉ ማድረግ ይገባናል። እንዲህ ያሉ መልካም ውሳኔዎችን ስንሰማም፣ ዓመጽ ምንም ያገነገነና የበረታ ቢመስልም፣ በፍጻሜው ግን ሊረታና ሊሸነፍ እንደሚችል ጥቂት ማሳያ እንደኾነ ማስተዋል እንችላለን። እግዚአብሔር ምድራችንን መልካም በኾኑ ዜናዎች እንዲያበስርልን ዘወትር እየማለድን በጸሎት ከመትጋት ልንታክት አይገባንም። ጌታ ኢየሱስ በምድራችን ከፍ ያለውን ዓመጽ ይገስጽልን፤ በጎውንና መልካሙን ዜና ያሰማን፤ አሜን።


My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/2022/07/50.html
895 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 06:08:06 የክርስትና መሠረቱ የክርስቶስ ትምህርትና ሕይወት ብቻ ነው፤ ክርስትና ከዚህ መሠረት "ስንዝር ታህል" ፈቀቅ ካለ፣ "ኀይል አልባ ተ*ራ ሃይማኖት" ነው!
470 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9), 03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ