Get Mystery Box with random crypto!

መንግስተሰማይ ቀርባለች እና ንሰሀ ግቡ🙏 ተዋህዶ ሀይማኖቴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido_haymanote_1 — መንግስተሰማይ ቀርባለች እና ንሰሀ ግቡ🙏 ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahido_haymanote_1 — መንግስተሰማይ ቀርባለች እና ንሰሀ ግቡ🙏 ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የሰርጥ አድራሻ: @tewahido_haymanote_1
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.15K
የሰርጥ መግለጫ

እሴብህ ጸጋኪ ኦ እግዝትነ ማሪያም🙏
ፅዮን ሆይ ስምሽን ለልጅ ልጅ እናሳስባለን 🙏
"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሏቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ.."
[ዕብ 13፡7-9
#ተዋህዶ #ሀይማኖቴ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2021-11-16 10:56:00 የ 26ቱ ፊደላት ትርጓሜ

ሀ - ብሂል ሀለዎቱ ለአብ እምቅድመ አለም።
ለ - ብልሂ ለብሰ ስጋ እም ድንግል።
ሐ - ብልሂ ሀመ ወሞተ።
መ - ብልሂ መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር።
ሠ - ብልሂ ሠረቀ በስጋ።
ረ - ብልሂ ረግአት ምድር በቃሉ።
ሰ - ብልሂ ሰብአ ኮነ እግዚእነ።
ቀ - ብልሂ ቀዳሚሁ ቃል።
በ - ብልሂ በትህትና ወረደ።
ተ - ብልሂ ተሰብአ ወተሰገወ።
ኀ - ብልሂ ኀይለ እግዚአብሔርን።
ነ - ብልሂ ነሥአ ደዌነ ወጾረ ህማመነ።
አ - ብልሂ አእኩቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር።
ከ - ብልሂ ከላሂ ለእግዚአብሄር።
ወ - ብልሂ ወረደ እምሰማይ።
ዐ - ብልሂ ዐረገ ሰማያተ።
ዘ - ብልሂ ዘኮሎ ይእኀዝ እግዚአብሔር።
የ - ብልሂ የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ።
ደ - ብልሂ ደመረ ስጋነ ምስለ መለኮቱ።
ገ - ብልሂ ገብረ ሰማያት በጥበቡ።
ጠ - ብልሂ ጠዐሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር።
ጰ - ብልሂ ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ፅድቅ።
ጸ - ብልሂ ጸጋ ወክብር ተዉህበ ለነ።
ፀ - ብልሂ ፀወነ ኮንከነ።
ፈ - ፈጠረ ሰማየ ወምድር።
ፐ - ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ።


ፀሀፊ - ዲ/ን ዳዊት
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
Join
3.1K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:51:24 #ተዋህዶ #ሀይማኖቴ
መንፈሳዊ ትምህርቶችን በዚህ ቻናል ላይ ማስተማር የምትፈልጉ @YESILASE_LIJ_7 አውሩኝ admin እሰጣቹሀለው
1.9K viewsedited  07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:46:06 ✥ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ✥



የቅዱስ ኤፍሬም ሀገረ ውላዱ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች መካከል ነው፡፡ አባቱም ክርስትናን የሚጠላ ካህነ ጣዖት ነበር፡፡ አንዳንድ ምንጮች ከቅዱስ ኤፍሬም ሕይወት በመነሳት ወላጆቹ ክርስቲያኖች እንደነበሩ ዘግበዋል የሐምሌ አስራ አምስት ስንክሳር ግን የአባቱን ካህነ ጣዖትነት ያረጋግጣል ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው  በ306 ዓ.ም ገደማ “በሜሶፖታሚያ” ውስጥ በምትገኝ “ንጽቢን” እንደሆነ ይታመናል። (ንጽቢን   በደቡባዊ ቱርክ እና በምዕራባዊ ሶርያ መካከል የምትገኝ ቦታ ናት፡፡) ይህቺም ቦታ ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ የነበረው የቅዱስ ያዕቆብ ሀገረ ሰብከቱ የነበረች ናት፡፡

ይህንን ታላቅ አባታችንን የእግዚአብሔር መንፈስ አመላክቶት ወደ ቅዱስ ያዕቆብ ሄዶ ትምህርተ ክርስትናን ተምሮ የተጠመቀ ሲሆን ከወላጆቹ ጋር የኖረው እስከ አሥር ዓመቱ ብቻ ነው፡፡ በትምህርተ ክርስትና አምኖ ከተጠመቀ በኋላ ግን በቅዱስ ያዕቆብ ዘንድ በብሕትውና ተወስኖ በመማርና በማስተማር በንጽቢን ለሚገኘው መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ሓላፊ እስክመሆን ደርሶ ነበር፡፡
በ393 ዓ.ም የንጽቢን ከተማ  በወራሪዎች እጅ ስትወድቅ ቅዱስ ኤፍሬም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመሆን የሮም ግዛት ወደነበረችው ኤዴሳ (ታናሽ እስያ፣ዑር) ተሰደደ፡፡ ይህቸ ቦታ ቅዱስ ኤፍሬም ከመናፍቃን ጋር የተጋደለባት፣ በቤተክርስቲያን ትምህርት ላይ ያላቸውን አብዛኞቹን የክህደት ትምህርቶች የሞገተባትና  መጻሕፍቱን ያዘጋጀባት ናት፡፡አብዛኛዎቹን ትምህርቶቹንና መጻሕፍቱን ያዘጋጀው በዚች በኤዴሳ በሚገኘው ትምህርት ቤት ነው፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከቅዱስ ያዕቆብ ጋር በመሆን በአርዮስ ምክንያት በተካሄደው  የኒቅያው ጉባኤ ( 325 ዓ.ም ) ላይ ተገኝቷል፡፡ በዚህም የአርዮስን ክህደትና ምክንያተ ውግዘት ተገንዝቧል፡፡ ከኒቅያ ጉባኤ መልስ መንፈሰ እግዚአብሔር በራዕይ በገለፀለት መሠረት ቅዱስ ኤፍሬም ከቅዱስ ባስልዮስ (ቁጥሩ ከ318ቱ ሊቃውንት ወገን ነው) ዘንድ ለመገናኘት ወደ ቂሣርያ ሄዷል፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም የዲቁና ክህነት ሠጥቶ ከሀገረ ስብከቱ ከፍሎ እንዲያስተምር ወስኖ በእርሱ ዘንድ አኑሮታል፡፤ በዚያም ቦታ ብዙ ተአምራትን አድርጓል መጻሕፍትንም ጽፏል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በትውፊት እንደሚታወቀው ምንኩስናን በገቢር ገለጣት እንጂ ሥርዓተ ምንኩስናን መፈጸሙን በግልጽ የሚመለክት ማስረጃ አልተገኘም፡፡

እንዲያውም በሶርያውያን ክርስቲያኖች የሚዘወተረውን ራስን በአንድ ስፍራ ወስኖ በብሕትውናና በመምህርነት ቤተክርስቲያንን የማገልገል (Proto monasticism) ሕይወት ይኖር እንደነበር ይታመናል፡፡ በትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመጎብኘት ወደ ቀጰዶቅያ እንዲሁም አባ ቢሾይን ለመጎብኘት ወደ ግብጽ እንደተጓዘ የሚነገረውም ከዚህ ጋር በተያያዘ ነው ፍጹም በሆነ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቱ ምሳሌ በሚሆነው ትምህርቱና የምናንኔ ሕይወቱ የሚታወቀው ቅዱስ ኤፍሬም ሐምሌ አስራ አምስት ቀን በ 370 ዓ.ም አርፏል፡፡በዚህ ሁሉ ትጋቱም ሶርያውያን ክርስቲያኖች ‹ጥዑመ ልሳን›፣ ‹መምህረ ዓለም›፣ ‹ዓምደ ቤተ ክርስቲያን› በማለት ይጠሩታል፣ያወድሱታል፣ያመሰግኑታል የቅዱስ አባታችን ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን!


__



@Tewahido_Haymanote_1
@TewahidooHaymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
Join
1.9K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:44:36 አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤ ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው። በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

መልካም ቀን
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
1.8K views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:27:48 ለአባ የትናንቱ
____________

ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው ፣
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው ።
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ ፣
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ ።
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው ፣
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው ።
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ ፣
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ ።
የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ ፣
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ ።
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ ፣
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ ፣
ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ› ፣
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ ፣
የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ ፣
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ ፣
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ ፣
በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ ።


ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ

#ሼር
__
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
Join
1.7K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:26:52 የ ቅ/ጊዮርጊስ ተአምር
1.6K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:26:27 Channel name was changed to «መንግስተሰማይ ቀርባለች እና ንሰሀ ግቡ ተዋህዶ ሀይማኖቴ»
07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-16 10:19:28 Channel photo removed
07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ