Get Mystery Box with random crypto!

ለአባ የትናንቱ ____________ ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው ፣ ማን ነበር ትውልዱ | መንግስተሰማይ ቀርባለች እና ንሰሀ ግቡ🙏 ተዋህዶ ሀይማኖቴ

ለአባ የትናንቱ
____________

ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው ፣
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው ።
አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ ፣
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ ።
በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው ፣
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው ።
የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ ፣
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ ።
የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ ፣
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ ።
በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ ፣
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ ፣
ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ› ፣
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ ፣
የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ ፣
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ ፣
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ ፣
በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ ።


ዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ

#ሼር
__
@Tewahido_Haymanote_1
@Tewahido_Haymanote_1
Join