Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-22 07:32:51 የክርስቶስን ክንድ ተደግፎ የወደቀ፣ በታሪክ ማንንም አላውቅም!
168 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 21:15:14
ይህ ጦርነት ከዚህ የከፋውን ዕልቂትና ፍጅት እንዳያደርስ እጅግ በጣም ጥቂቶች ተቃውመው ነበር። ነገር ግን ተረገሙ፤ ተኮነኑ እንጂ የተረዳቸው አልነበረም፤ ምሳሌ ለመጥቀስ ከታች ምስሉ ያለው ዘፋኝ ይጠቀሳል። የሃይማኖት መሪዎች የዚህን ልጅ ድፍረት ማጣታቸውና ለሰላም አለመጨከናቸውን ሳስብ አዝናለሁ፤ እደነቃለሁም። የበለጠ የማዝነውም፣ ኢትዮጵያ የምትባል አገር፣ በተደጋጋሚ ከወደቀችበት ከጥልቅ ውድቀቷ የማትማር ተላላ አገር መኾንዋን ሳስብ ነው።

ሠላምን "ሠላም ሠላም" ስላልን አናገኛትም፤ ይልቁን መልካም በማድረግ እንፈልጋት፤ እንከተላትም። ኢትዮጵያ ሆይ፤ ሰላም ላንቺና ለመሪዎችሽ ይኹን።

"ከክፉ ነገር ሽሹ፤ መልካም ነገርንም አድርጉ፤ ሰላምን ፈልጉአት፤ ተከተሉአትም።" (መዝ. 34፥14)
219 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:37:48
የገንዘብ መጠኑስ ተተምኖ ይኾናል፤ ያለቀውና የረገፈው የሰው ሕይወትስ? የአንድ ሰው ዋጋው ስንት ይኾናል? በተደረገው ጦርነት ያለቁትና የረገፉት ሰዎች ብዛት ያስደነግጠናል? ያሳቅቀናል?  ከወደመው ብርና ብረት ይልቅ ሰው ያንገበግበናል? ሰው ጠፋ ብለንስ መፈለግ ያምረናል? ጌታ ኢየሱስ ዓይነ ልቡናችንን ያብራ፤ አሜን።
378 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 14:09:37 "ሰዎች ኾን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።"
(መክ. 8፥11)
294 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 07:11:16 "ኢየሱስ ያድናል" ማለትን ከለመድንና በትክክል ኀጢአትን ከተጠየፍን፣ "ኢየሱስ በኀጢአተኛው ዓለም ላይ ይፈርዳል" ስንባልም ደስ ይበለን። ኢየሱስ ያድናል፤ ይፈርዳልም፤ አሜን።
485 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 21:24:03 ክርስትና ጨክነው ለሚቆሙ ብቻ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ አኹን ድረስ መንግሥተ ሰማይ በብዙ ትገፋለች፤ የሚያገኟትም ብርቱዎች ናቸው፤” (ማቴ. 11፥12) እንዲል፣ በኢየሱስ ጉዳይ በርቱ እንጂ አትልፈስፈሱ!
563 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 22:39:00
657 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 14:28:41
ምናልባት ዓለማዊነትን እርግፍ አድርገው ሲተዉ፣ እንደዚህች ውብ እናት ጽምፅን አጥፍቶ ማገልገል ትልቅ ብጽዕና ይመስለኛል። ብዙዎች የተዉትን ዓለማዊነት በቅጡ መተዋቸውን መንፈሳዊ የንስሐ ፍሬ በሚገባ ሳያሳዩ፣ ዘለው ወደ አገልግሎት ይገባሉ።

በዓለማዊው ዝና መንፈሳዊ አገልግሎት ለማገልገል መቸኮል አለመታደል ይመስለኛል። ሂሩቴ፣ ለዚህ ምርጥ ማሳያ ናት። ምድራዊውን ንቆ ለሰማይ ድምጽ አጥፍቶ ማገልገል ትልቅ ዕድለኝነት ነው።
935 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 21:29:36 ግንቦት ልደታና ቦረንቲቻ አይዛመድ ይኾን?


ቦረንቲቻ፣ በዋቄፈና አስተምህሮ መሠረት፣ በዓመት ኹለት ጊዜ ዋቃን ለማመስገንና ምልጃ ለመጠየቅ (መስከረምና ግንቦት አከባቢ) በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የሚከናወን ባህላዊና አምልኮታዊ ሥርዓት[1] ወይም የሚከበር በዓል ነው። በአርሲ ኦሮሞዎች ዘንድም በቤተሰብ፣ በከብቶቻቸው ላይ የሚመጣቸውን ማናቸውንም ክፉ ነገር ለማስወገድ ከሚከበሩ በአላት አንዱ ቦረንቲቻ ነው።[2] ቦረንቲቻ ክብረ ብኵርና ነው፤ የኦሮሞ ኹለቱ የትውልድ ሥርወ ግንዶች ቦረናና በሬንቱ ናቸው። ቦረና ታላቅ እንደ መኾኑ፣ በኦሮሞ ዘንድ ብኵርና ታላቅ ክብር ስላለው፣ ለቦረና ልዩ ክብር “ቦረንቲቻ” የሚባል በአል ይከበርለታል።[3]



በበአሉ ዕለት የዋቃ ምሳሌ በኾነው፣ ጥቁር ጥለት የተጌጡ ልብሶችን በተለይም ወንዶቹ ቡልኮ፣ ሴቶቹ ደግሞ ቆሎሰበታን ለብሰው ይታያሉ። በተለይም በአሉ ከክረምት ዝናም ጋር በመያያዙ፣ የክረምት ዝናም ደግሞ ከጥቁር ደመና ጋር በመምጣቱ፤ ታላቅ ክብር ነው። ስለዚህም ጥቁር ኮርማ በማረድ አቀባበል ይደረግለታል፤ ይህም ማለት፣ ለክረምት ዝናም የሚደረገው አቀባበል “ቦረንቲቻ” ይባላል።[4] Ayyaanni Afraasaa-Gannaa kun Ayyaana Boorantichaa jedhama.[5]

ይህ በአል የሚከበርበትም ምክንያት፣ የሰላም ዝናም ዝነምልን፣ ውሽንፍር፣ ነፋስ፣ በረድ፣ መባርቅት፣ ጎርፍና አደጋው አያግኘን! በማለት ጥቁር ኮርማ በማረድ፣ “ዋቃ ሆይ፤ እባክህን ሊመጣ ካለው መጸው አድርሰን” በማለት ይለማመናሉ። በክረምት ወቅት ወደ ወንዝ ወርዶ ኢሬቻ አይደረግም፤ ምክንያቱም የክረምት መልካ ድፍርስና ሕያዋንና ሙታንን ተሸክሞ ስለሚሄድ። ሙት ደግሞ አያና የለውም፤ ዋቄፈታ ደግሞ ሙት ወደ ኾነው ወይም ሙት ባለበት ኢሬቻውን አያደርግም።[6] በሰላሌ አከባቢ በቦረንቲቻ በአል አከባበር ማለትም በጥቅምትና በግንቦት ወቅት ላይ መጠጥ ይደፋል፤ እህል ይበተናል።

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶለሳ እንዲህ ይላል፣

“የቦረንቲቻ አምልኮ ክርስቲን በኾኑም ባልኾኑም ኦሮሞዎች እንዲሁም በአማሮች እና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን በግንቦት ወር የቅድስት ማርያም ልደት (ልደታ) ተብሎ በሚታመንበት ዕለት ይከበራል። ይህን በአል ለማክበር ሰዎች “አድባር” በሚሉት እንደ ቅዱስ በሚታሰብ ዛፍ ስር ይሰበሰቡና ምግብ (ንፍሮ) ይቀቅላሉ፤ የያዙትን ስጦታም ከቅድስት ማርያም ጋር ለሚያምታቱት ለቦረንቲቻም ይሰጣሉ።”[7]

እናም በግንቦት ልደታ ወቅት በአብዛኛው ኦርቶዶክሳውያን ዘንድ፣

- ማርያም በሊባኖስ ተራራማ አገር ከቤት ውጭ ተወልዳለችና፣ እርሱን ለማሰብ ተብሎ የግንቦት ልደታ በአል ከቤት ውጭ (በወንዝ አከባቢ፣ በዛፍ ሥር፣ በመንገድ ላይ … ይከበራል፤

- በአሉ ሲከበር የበሰለ እህል የመበተን ወይም ቆርሶ የመጣል ልማድ በብዙ አከባቢዎች ዘንድ አለ፣

- ታቦቱ በሚነግሥበት አከባቢ፣ ከብት ታርዶ ታቦቱ እንዲራመደውና አንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ደሙን ረግጦ የመግባት ልማድ አለ፤ እንዲሁም ታቦቱ አከባቢ ወንዝ ካለ ወደ ወንዝ ወርዶ በዚያ አከባቢ የመመገብ ልማድና ሌሎችም ልማዶች አሉ።

እንግዲህ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተሐድሶ ወይም መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ስላደረገ እውነተኛ ተሐድሶ ስናወራ፣ እኒህ ኹሉ ነገሮች በእግዚአብሔር ቃል እንዲታረሙና እንዲስተካከሉ ከሚፈልግ እውነተኛ ጥማት የተነሣ ነው።

ይህ ጽሑፍ “ስለ ኢሬቻና አምልኮአዊ ልምምዱ” ከጻፍኹት መጽሐፌ ገጽ 76-78 የተወሰደ ነው።


[1] ዓለማየሁ ኃይሌ፤ 2007 ዓ.ም፤ ዝክረ በዓላት፤ ገጽ 71

[2] ሰሎሞን ተሾመ። 2002 ዓ.ም፤ የግድያ ግጭት ባህላዊ አፈታት በስሬ ኦሮሞዎችና አማራዎች- ንጽጽራዊ ጥናት። ያልታተመ የኹለተኛ ድግሪ ማሟያ ጥናት፤ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሁፍና ትምህርት ክፍል፤ አዲስ አበባ። ገጽ 15

[3] ተሊላ ቡልቡላ እና መርሰን ቦባሳ፤ “DUUDHAA”፤ 2001 ዓ.ም፤ በኦሮሚኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀ ልዩ የኢሬቻ እትም። ገጽ 9

[4] Dirribii Damusee Bokkuu; Ilaalcha Oromoo; ገጽ 79

[5] Dirribii Damusee Bokkuu; Ilaalcha Oromoo; ገጽ 64

[6] Dirribii Damusee Bokkuu; Ilaalcha Oromoo; ገጽ 79

[7] ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶለሳ፤ የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ፤ 2008 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ገጽ 24

My telegram link - https://t.me/ebenezertek
My blog Link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/05/blog-post.html
910 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 19:10:58
በአገረ ኬንያ አንዱ ነሁ*ላላ የስህ*ተት መምህር፣ "ዕድሜ ልክ ወይም እስከ ዕለተ ሞታችሁ ብትጾሙ ፈጣሪንና መንግሥቱን ታገኛላችሁ፤ ለጾማችሁ ትክክለኛነትም ደግሞ በር ሊቆለፍባችሁ ይገባል" ብሎ ከ70 በላይ ለኾኑ ሰዎች የሞት ምክንያት በመኾኑ፣ "የቤተክርስቲያኒቱን ቄስ" ፖውል ማክሄዚን የኬንያው ፕሬዘዳንት "ማደሪያውና መዋያው ወኅኒ መኾን አለበት" ብለዋል። International Good News Churchም ላይ ምርመራ እንዲደረግ አዝዘዋል።

ኹሌም እንደምንለው በአገራችንም ያሉት የስ*ህተት መም*ህራን፣ የሥጋም የነፍስም ጠ*ንቅ ናቸው። እረኞች ስላይደሉ ለመንጋው አይራ*ሩም። ጌታ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርት እንደ ተናገሩት ጨካኞችና ረብ ብቻ ፈላጊዎች ናቸውና እንዲህ ካሉት ተጠን*ቀቁ፤ ተጠ*በቁ ማለትን አንተውም።
244 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ