Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-22 11:02:55
በኢየሱስ ማረፍና መርካት ተስኖህ ስትዝ*ረከረክ፣ እንዲህ የሐሰት መም#ህራን መጫ#ወቻ አሻን#ጉሊት ትኾ*ናለህ!
243 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:01:50 ኀጢአትን ይቅር የማለት ጉዳይ! (ዮሐ. 20፥23)


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጣቸው ሥልጣን መካከል አንዱ፣ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” (ዮሐ. 20፥23) የሚል ነው፤ ብዙዎች የዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ዓውዳዊ ትርጕም ለሌላ ነገር ሲጠቀሙበት ብንመለከትም፣ በቀጥታ ሲተረጐም የሚሰጠን ትርጕም ግን፣ “እናንተ ኀጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ኀጢአታቸው ይቅር ተብሎአል፤ ያላላችኋቸው ግን ይቅር አልተባለም” የሚል ነው።



ይህ የሚያመለክተው ቅዱሳን ሐዋርያት በቀጥታ ይቅር የማለትና ያለማለት ሥልጣን እንዳላቸው የሚያመለክት አይደለም፤ ነገር ግን ሥልጣኑ ከእነርሱ የሚመነጭ ሳይኾን ወይም ደግሞ እግዚአብሔር የሐዋርያትን ወይም የአማኞችን ይቅር ማለት ተከትሎ ይቅር ይላል፣ ይቅር ሳይሉ ሲቀሩ ይቅርታ ይነፍጋል ማለት ሳይኾን፣ ወንጌልን በእውነትና በጽድቅ የሚመሰክሩ ኹሉ፣ ኀጢአትን ይቅር የማለትና ያለማለት ሥልጣን እንዳላቸው የሚያመለክት ነው።

ይኸውም፣ ሰዎች አንድ ሐዋርያ ወይም አማኝ የሚነግራቸውን ቅዱስ ወንጌል ሰምተው ቢያምኑና መታዘዝ ቢጀምሩ ኀጢአታቸው ይቅር ይባላል፤ ነገር ግን የሰሙትን ወንጌል ባያምኑና ባይታዘዙ ኀጢአታቸው ፈጽሞ ይቅር አይባልላቸውም ማለት ነው። ምክንያቱም፣ “በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ያላመነ አሁን ተፈርዶበታልና።” (ዮሐ. 3፥18)። ይህም የኀጢአት ይቅርታና ፍርድ የሚያገኘን፣ ክርስቶስን በማመንና ባለማመን የሚመጣ እንጂ ክርስቶስ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር እንዲሉ ወይም እንዳይሉ ፍጹም ሥልጣን እንደ ሰጣቸው አያመለክትም።

ሐዋርያት ወንጌልን ለመላው ፍጥረት ሲያውጁ፣ የይቅርታና የፍርድ አዋጅን ነው የሚያውጁት። ይህን የማወጅ ሥልጣንን የሰጣቸው ጌታችን ኢየሱስ ነው። ይህን የወንጌል አዋጅ ለሚሰማና ለሚታዘዝ ኹሉ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚሰጥ ይቅርታ አለ፤ በማያምን ኹሉ ላይ ግን ኀጢአቱ በእርሱ ላይ አለ፤ በእግዚአብሔር ልጅ አለማመን ሕይወትን አለማየት ነውና (ዮሐ. 3፥36) የደቀ መዛሙርት ትልቁ ሥልጣን፣ ይቅርታው የሚገኝበትን የመዳን ወንጌል ለሰዎች ኹሉ ማወጅ ነው፤ የኀጢአትን ይቅርታ የሚሰጠው ደግሞ አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ (ማር. 2፥7)።

እንግዲህ እንዲህ ማለት እንችላለን፤ ሰዎች በክርስቶስ ካላመኑ፥ ይቅርታን እንዳላገኙ ለማወጅ ሥልጣን አለን፤ ከዚህ ውጭ ግን በጌታችን ኢየሱስ በማመን ለኀጢአቱ ሥርየት ይኾን ዘንድ፣ የመዳን ንስሐ ያልገባውን ሰው ትድናለህ፣ በጌታችን ኢየሱስ አምኖ ንስሐ የገባውን ሰው አትድንም እንል ዘንድ አንችልም። “ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኃጢአት ሊያስተሰርይ የሚችል ሌላ የለም” ስንልም፣ እኛ በመዳን ወንጌል ላይ ቆመን፣ ሰዎች በክርስቶስ እንዲያምኑ የመዳንን ወንጌል ማወጅና በደስታ ሲቀበሉ እንደሚድኑ የተስፋውን ቃል መናገር፣ ብሎም ደግሞ አልቀበልም ሲሉና ሲክዱ ወይም ሲገፉ ግን ይቅርታን እንደማያገኙና ሕይወትን እንደማያዩ ልናስጠነቀቅ ተጠርተናል።

በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት አለ፤ የኀጢአት ይቅርታም ይገኛል፤ በማያምኑና ኢየሱስንና የመስቀል የማዳን መንገዱን በሚገፉ ላይ ግን ኀጢአታቸው ተይዞባቸዋል፤ የኀጢአት ይቅርታም አያገኙም። ከዚህ በዘለለ የኀጢአት ይቅርታ በማናቸውም ሌላ መንገድ አይገኝም! የለምም!

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/04/2023.html
160 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 04:36:42 በኦርቶዶክስ ውስጥ ኢየሱስን የሚሰብኩ ተሰድደው፣ የዶሮ ብልትና ጉልቻ የሚመስሉ "ነሁ ላላ ሰባክያን ተከብረው" መኖራ ቸውን ሳስብ እደነቃለሁ! ዘበነ ለማን ጌታ ይገስ ጸው!
529 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 01:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 06:27:33 “ኢየሱስ ሊቀ ካህናት የኾነው[የኾነልን] በማይጠፋ የሕይወት ኀይል መሠረት እንጂ፣ እንደ ትውልዱ በሕግ ሥርዐት አይደለም፤” (ዕብ. 7፥16) የሕይወት ኃይል ያለው ጌታ ተነሥቶአል! አሜን፤ ሃሌ ሉያ!
143 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 03:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 14:29:31 የጴጥሮስ ጌታ ዛሬም ይራራል! (ማር. 14፥66-72)


ቅዱስ ማርቆስ፣ ወንጌሉን ሲጽፍ በቅዱስ ጴጥሮስ ላይ ያተኵራል፤ ነገር ግን ከኢየሱስ በላይ አያልቀውም ወይም ከፍ ከፍ አያደርገውም። ኢየሱስ በተያዘበት ሌሊት ስለ ነበረው ኹኔታ ሲናገር፣ “ጴጥሮስንም፦ ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?” (ማር. 14፥37) ሲል፣ ሌሎቹ ወንጌላት ግን ኢየሱስ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለኹሉም ደቀ መዛሙርት እንደ ነበር ይናገራሉ (ማቴ. 26፥40፤ ሉቃ. 22፥46)።




በተመሳሳይ መንገድ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱን በገሊላ እንዲጠብቃቸው መልእክት ሲናገር፣ ማርቆስ አኹንም በተመሳሳይ መንገድ ከሌሎቹ ወንጌላውያን በተለየ ኹኔታ፣ “ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።” (ማር. 16፥7) በማለት ትኵረት ሲያደርግ እንመለከተዋለን።

ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ ሲገረፍ አይቶታል፤ እንዲሁም የኢየሱስ ተከታይ መኾኑ በብዙዎች ዘንድ ታውቆአል፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ስምዖን ጴጥሮስ፣ እንደሚክደው ጌታችን ኢየሱስ በተደጋጋሚ ትንቢት ተናግሮ ነበር። ጴጥሮስ ምንም እንኳ ኢየሱስን እስከ መጨረሻው ግቢ “የተከተለውም ቢኾን እንኳ”፣ ነገር ግን መንገዶቹ ኹሉ በቅጥፈት፣ በውሸትና ስለ ኢየሱስ “ይህን የምትሉትን ሰው አላውቀውም በማለት በመራገምና በመማል” (ማር. 14፥71) በክህደት የተሞላ ነበር።

ስምዖን ጴጥሮስ፣ እንደ ጌታችን ኢየሱስ ትንቢት በአደባባይ በሴቶችና በተወሰኑ ሰዎች ፊት ክዶአል፤ ልክ እንደ ካደ ግን፣ ኢየሱስ “ትክደኛለህ ያለው ቃል ትዝ ሲለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።” (14፥72)። ይህ እጅግ አስደናቂ ተግባር ነው፤ የሠራውን ኀጢአት ሊናዘዝበትና አልቅሶ ሊመለስ መውደዱ ለእኛ የሚያስተምር ብርቱ መልእክት አለው።

ብዙዎቻችን ኀጢአት ሠርተን ከመናዘዝና ለመተው ከመጨከን ይልቅ ለመደበቅ እንሞክራለን። ምናልባት ብዙዎቻችን እንደ ጴጥሮስ፣ በጌታ ዘመን ኖረን ልክ ጴጥሮስ ኢየሱስ ሲገረፍ እንዳየው እኛም ተመልክተን ቢኾን፣ ኢየሱስን ደጋግመን ልንክደው እንችላለን። ነገር ግን ማርቆስ እንደሚነግረን ኢየሱስ ጴጥሮስን በልዩ ፍቅር ወደደው፤ ይቅርም አለው፤ ራራለትና ወዶ ተቀበለው።

ይልቁን የክርስቶስን ወንጌልና ክርስቶስ ስለ እኛ የከፈለውን ታላቅ የመስቀል ሥራ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ገበታ፣ በታክሲ ስፍራ፣ በቤተሰብ መካከል፣ በባልንጀሮቻችን ፊት ለመመስከር ብዙ ጊዜ የምናፍርና የምንክድ ነን። የምንፈራውና የምንክድበት ምክንያታችንም ብዙ ነው፣ አንዳንዶቻችን አፍረን፣ ሌሎቻችን ፈርተን፣ ሌሎቻችን ደግሞ ሰዎች እንዳይሳለቁብንና እንዳያሸማቅቁን ብለን የትንሣኤውን ወንጌል ከመመስከር ቸል ያልንባቸው ጊዜያት ብዙ ናቸው።

በዚህ ረገድ ኹላችንም በካድንባቸው፣ በበደልንባቸው፣ በክርስቶስ ባፈርንባቸው፣ ችላ ባልንባቸው ጊዜያት ኹሉ ኢየሱስ የማይለወጥ ታማኝ ወዳጅና አባት ነው፤ እስክንመለስ የሚጠብቅ እረኛም ነው፤ መካዳችንን ረስቶ በፍቅር ሊቀበለንና ሊምረን የታመነ ሊቀ ካህናት ነው። ስለዚህም እንደ ጴጥሮስ በኀጢአታችን ልንናዘዝና ይቅርታ ልንለምን ይገባናል እንጂ መሸፋፈንና መደበቅ አይገባንም። ጴጥሮስን ይቅር ያለው ጌታ ዛሬም መሐሪ ነው!

ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ፣ በሙሉ ድፍረት በሕዝብ ኹሉ ፊት መሰከረለት። እናንተም፣ ያላፈረባችሁን አትፈሩበት፤ በአደባባይ ለክብራችሁ የተዋረደውን እርሱን በሰዎች ኹሉ ፊት ስሙን በመመስከር ፍቅራችሁን ግለጡለት።

“በማያቋርጥ ፍቅር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለሚወዱ ሁሉ ጸጋ ይሁንላቸው።” (ኤፌ. 6፥24)

My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/04/1466-72.html
218 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 14:42:40 እናንተ ባሮች ሆይ...!

 ንጉሥ በባዶነት ዝቅ አለ ወረደ
አሮጌውን አዳም በአዲስ አስወገደ
ደግሞ...!
ንጉሡ ዝቅ ብሎ መታዘዝ "ተማረ"
ሕማም የማያውቀው፣ ሰውን ስለ ማዳን ሕማምን ታመመ!

ንጉሡ ውድ ነው ተወዳጅ ትምህርቱ
ንድፍ ብቻ ሳይኾን ይገዛል ሕይወቱ
ኩራት አስወግዱ ተዉ አትታበዩ
ጌታ የኾነውን ይህን ባሪያ እዩ!
ንጉሥና ባሪያ ባንድ ባይስማሙም
በኢየሱስ አይተናል አካል ነሥተው ፍጹም!

እንኪያስ
በየሜዳው መጮኽ ይቅር አትለፍፉ
እናንተ ባሮች ሆይ...!
ጌታን አክብሩና እናንተ እለፉ፣
አስከብሩትና እናንተ ተረሱ
ይህ ነው ዋና ትምህርት የኢየሱስ ንጉሡ!

My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/?m=1
158 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  11:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 08:27:55 ትክክለኛው ትህትና ትንሹ ለትልቁ የሚያደርገው ብቻ አይደለም፣ ይልቁን ትልቁ ለትንሹ በጽድቅ የሚታዘዘው ነው፤ ልክ እንደ ኢየሱስ!
229 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 11:52:42 ወንጌል፣ የእግዚአብሔር ልጅ ሕይወት እና ትምህርት የሚመሰከርበት ነው እንጂ፣ እኔ ለሌሎች፤ ሌሎች ለእኔ ጥብቅና የሚቆሙበት "ጽድቅ መሳይ ግብዛዊ" መንገድ አይደለም!
255 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 05:02:59 የክርስቶስ በሥጋ መሞት ፍጹም ሰው መኾኑን ያመለክታል፤ ትንሣኤ ደግሞ ፍጹም አምላክነቱን። እንዲህ እናምናለን፤ እንታመናለን!
338 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 02:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 13:11:18 አትተወኝ!
 

የሰቆቃ አድማስ ተንዶ ሲፈጨኝ
ዋይታና እሪታ ምግብ መጠጥ ሲኾነኝ
እንደ ዘጠኝ ወር ምጥ
በየቀኑ ሳምጥ
ሰቀቀን ወዳጄ ሐዘን ባልንጀራ
ደስታና ፈገግታ ከእኔ ተቀያይመው ኾነው ባላጋራ
ሲያድሙ ከልቅሶ ከእንባዬ ጋራ
ባክህ ደስታዬ ሆይ ና ወደኔ ግባ!

ና ግባ ከቤቴ ኹሌ በየቀኑ
ስብራት ይወገድ ይነቀል ችንካሩ!
ይብገን ቅጥል ይበል የልቅሶ ሸለቆ
ሳቅህ በየቀኑ በቤቴ ላይ ደምቆ
የክብር ንጉሥ ሆይ! ወደ ቤቴ ግባ
ተመላለስበት ብቻህን አባባ
ብበድልህ እንኳ ገብተህ ባክህ አትውጣ
እንደገና ሠርተህ ክበርብኝ ጌታ!

My blog link - http://abenezerteklu.blogspot.com/2023/04/blog-post_9.html?m=1
446 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ