Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-27 10:51:08
ዓለም ዓቀፍ መድረክ ላይ እንዲህ በሰላም እየተወያየንና እየተነጋገርን፣ በአገራችን መድረኮች ላለማውራትና ላለመተያየት መገፋፋታችን ያሳዝናል። እናም ኢትዮጵያ የምትባለው አገር፣ ወደ ሌላ ዓለም ስትሄድ የምታሳየውን ትህትናና ዝቅታ በልጆችዋ መካከል አስቀድማ ብታሳይ ምኞቴ ነው፤ በሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው መገፋፋትና መናናቅ፤ መንግሥታዊ የፖለቲካም ሴራ ቀርቶ ለሃይማኖተኞች ብቻ ሃይማኖቱን መተዉን በምድሪቱ ላይ ባይ ደስ ይለኛል!

የዐሳብ ልዕልና በመካከላችን ቢነግሥና ቢከበር፣ ቍሳዊው ብልጥግና በራሱ ጊዜ ይመጣ ነበር! እግዚአብሔር ምድራችንን ይጐብኝ!
278 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 07:18:18 "እግዚአብሔር ሆይ! ተስፋችንን በአንተ እንዳደረግን ዘላቂ ፍቅርህ በእኛ ላይ ይሁን።" (መዝ. 33:22)
16 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 19:16:32
ነገ 8:30 ላይ ሐዳስያን ያልኾናችሁም በፍቅር ተጋበዙ
131 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 07:18:49
ሙሾ!

መበልጸጉ ይቅር ምንድነው መትረፍረፍ
አንድ ያለኝን ሰንጋ ጠብቄ ሳላተርፍ?

ይበዛል አትበሉኝ የሕልም እልም ተስፋ
አንዱን አድኑልኝ ባፍ ጢም ሳልደፋ!

ሰንጋ ማለት ለእኔ አባትና ልጅ ነው
የምድር አቀበቴን በጫንቃው ምቀዝፈው
እናም እባካችሁ ይህንን በሬዬን ማን ለኔ ይመልሰው?
201 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-24 04:45:21
“ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።” (መዝ. 147፥9) የተባለልህ እውነተኛ መጋቢው እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትን እባክህ አስብ፤ ለመሪዎችም የልብ መደንገጥንና መራራትን ስጥ፤ አሜን።
16 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 01:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 08:07:51 ኀጢአተኞች ኹሉ ምሕረት ያገኘንበት አዲሱ ኪዳናችን፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ የምሕረት ኪዳኑም ላይሻር በቅዱስ ደሙ ታትሞአል! አሜን።
159 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 21:04:35 በሕመምና በጤና፣ በስብራትና በጽናት፣ በማጣትና በማግኘት፣ በማናቸውም የሕይወት ጉዞዬ እግዚአብሔር ጻድቅና ትክክል ነው።
219 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 21:12:10 ኑ እንቀደስ!

ለቅበላ ሥጋ ማጣጣም ወግ ኾነ
ሰውን ያህል ክቡር እየመነመነ፤

በግ በሬ ወተቱ እየተወደደ
ለቅበላ ሽሚያ ሰውነት ወረደ፤

ነፍስን ታህል ክቡር እያረካከሱ
ቅበላን በሥጋ በቅቤ አስወደዱ፤

ተዉ እናንተ ሰዎች ተዉ ተቀበሉ
ኢየሱስ ነው ቤዛ ለፍጥረተ ዓለሙ፤

ወጭት እያጠሩ ንስሐ ሳይገቡ
ጾም በሌለ ወራት ጌታን ሳያከብሩ
አኹን ምን ያደርጋሉ ’ንጹም መባባሉ?!

ጆሮ ያለው ይስማ በመንፈስ ቅዱስ
ኀጢአት ዕድሜው አጥሮ ኑ እንቀደስ!

My Twitter link - https://twitter.com/Diyakon.../status/1626836348475940864

My Blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/02/blog-post_19.html
193 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 13:31:19
ስለ ሌብነት በጳጳሳቱ አንደበት!

"... እኛ ቤት ሌብነት አለ። እንደው እርሶ(ዶክተር አቢይ) ገብተው ቢፈትሹ። ዝም አይበሉ... "
(አቡነ ሳዊሮስ)

"... እውን እኛ ቤት ሌብነት አለ። እንደውም እንደ ሚኒስትሮች የግል ሐብታችንንም ጭምር ማስመርመር እስከ መድረስ ብንፈታተሽ እላለው።" (አቡነ ናትናኤል)

እንግዲህ ይህን የአደባባይ እውነት ተሐድሶ አያሻውም ትላላችሁ? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተሐድሶ ማለት ቃሉ እንደሚለው ብቻ እንኑር፤ እንመላለስ ማለት ነው። እናም እንዲህ ያለውን ሌብነት መጠየፍ፣ መጥላት እርሱ የእውነተኛ ሐዳሲ ጠባይ ነው።

እንዲህ ያለ ሌብነት በመንግሥት አይጠፋም፤ ቤተክርስቲያን ግን በቅድስናና በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ካሸበረቀች በእውነት ያለ ነቀፋ መኾንና ያለ ነውር በእግዚአብሔር ፊት መመላለስ ይቻላታል። ጌታ ለቤተክርስቲያን ጉብኝት ያድርግ። አሜን።
227 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 18:23:58 የብሔር ተስፋው ምንድር ነው?
እግዚአብሔር አምላክን የምንከተለው ዛሬ የሚታመንና ነገ የሚፈጸም ተስፋ አለው ብለን ስለምናምን ነው። እግዚአብሔርን ብንታመነው የሰጠንን ተስፋ ፈጽሞ ያሳርፈናል፤ “ባናምነው ደግሞ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።” (2ጢሞ. 2፥13)፤ እኛ ብንሰናከልና እግዚአብሔርን ብንክድ፣ እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና ታማኝ ኾኖ ይኖራል።



ከክህደታችን ንስሐ ገብተን ብንመለስ፣ ይቅር የሚለንና ተስፋውን የሚፈጽምልን አምላክ አለን፤ ብንክደው ግን ይክደናል፤ ጌታ እግዚአብሔር የማይቀበሉትን ሊቀበል አይችልምና። ተስፋውን የሰጠውና የሚፈጽመው፣ ታምነው ለሚከተሉትና ራሳቸውን አሳልፈው ለሰጡለት ብቻ ነው። ሰማዕታትና ቅዱሳን እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተስፋ ስላመኑ ፍጹም ተከተሉት። አላመነቱም፤ አልተጠራጠሩም፤ አልተግደረደሩም ወደው ተከተሉት!

እግዚአብሔር ለነገ ተስፋ ሲሰጥ፣ ዛሬ ላይ ተስፋውን ሳያስጨብጥ በከንቱ አይደለም፤ ተስፋን የሰጠ የታመነ ነው፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም ተስፋን ሰጥቶናል፤ ስለዚህም ራሳችንን በእርሱ ላይ ዥው አድርገን በመጣል እናምነዋለን፤ እንታመነዋለን። እግዚአብሔር ብናጣው የምናጣው ሕይወትና የዘላለም ተስፋን ነው፤ ብናምነው ደግሞ የምናገኘው የሚፈጸም ተስፋና የዘላለም ሕይወትን ወይም ራሱን እግዚአብሔርን እንወርሰዋለን። ስለዚህም እግዚአብሔርን ፍጹም እናምነዋለን።

አብርሃም፣ እግዚአብሔርን አመነ፤ ስለዚህም “ከአገርህና ከዘመዶችህም ወጥተህ ወደማሳይህ ወደ ማንኛውም ምድር ና” (የሐ. ሥ. 7፥3) ሲለው፣ ከቶ አልጠራጠረም፤ ምክንያቱም “መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።” (ዕብ. 11፥10)፤ ስለዚህም ተስፋውን አምኖ፣ እግዚአብሔርን ተከተለ። አብርሃም እግዚአብሔርን በመከተሉ እልፍ፤ ትእልፊት ትርፍ እንጂ አንዳችም ኪሳራ አልገጠመውም።

በዘመናችን ግን ክርስትናን ከተጣባውና አልላቀቅ ካሉ ተውሳኮች አንዱ ዘረኝነትና ጣጣው ነው። እርግጥ ነው ሰዎች ባህል፣ ልዩ ልዩ ቋንቋ፣ እሴት፣ የተከለለ አገር፣ ድንበርና ብዙ ልማዶች አላቸው። ይህ ተፈጥሮአዊና በዓለም ኹሉ የታወቀ ነው። እኒህ ኹሉ ግን በዚህ ምድር ሳለን ብቻ የምንግባባቸውና እንደ ዕድገታችንና ዕውቀታችን የምንጠቀምባቸው ናቸው፤ ነገር ግን ለነገ የሚሰጡን አንዳችም ተስፋ የላቸውም! እኒህ ኹሉ እንደ ለበስናቸው ልብሶች ያረጃሉ፣ ይኮስሳሉ፣ ይጠፋሉ ብሎም ይረሳሉ።

ሰዎች እንደ ወደዱ እንደሚለብሱት እንዲሁ፣ የወደዱትንና ያደጉበትን ባህልና ቋንቋ ይከተላሉ፤ ይናገራሉ፤ ይህን በማድረጋቸውም ከልካይ የለባቸውም፤ ደግሜ እላለሁ፤ ነገር ግን ለነገ አንዳችም ተስፋ አይሰጡም። ታድያ አንድ ነገር ነገ ላይ የሚሰጠን ተስፋ ከሌለው፣ ለምን እንከተለዋለን? ለነገ ተስፋ የማይሰጥ ከኾነስ፣ ዛሬ ላይ እንዴት እንታመነዋለን? አንድ ሰው ኦሮሞ ወይም አማራ፣ አልያም ከንባታ ወይም ሲዳማ ነኝ ብሎ ቢያምን ወደፊት ምን ይደረግለታል? ባለመኾኑስ ምን ይጐድለበታል? በእግዚአብሔር ፊት አንድ ኦሮሞና አማራ ወይም መንጃና ሂንዱ መካከል ምን ልዩነት አልያ አብላጫ አለ? በመኾናቸው የተሰጠ ተስፋስ አለ? አንዱን ኾነን ሌላውን ባንኾን ምን ይጐድልብናል? ምንስ ይጨምርልናል? እንኪያስ የሚያመጣውም ኾነ የሚያስገኘው ነገር ከሌለው በምን አመክንዮና መንገድ ሰው ይጋደልለታል?

ከሰሞኑ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተነሣው “ብሔር ተኰር መገፋፋት”፣ አቡነ ኤርምያስ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ በተሰበሰበው ስብሰባ ላይ ሲናገሩ፣ እገሌ የተባለው ጳጳስ ከእገሌ ብሔር ነው እያሉ ያብራራሉ፤ እንዲህ መናገር አለባቸው? ብዬ ራሴን ጠይቄአለሁ፤ አይገባም። እንዲህ እንዲሉ ያደረጋቸው ግን ለአገልግሎት የእግዚአብሔር ቃልና እውነት ተሽሮ፣ ብሔርተኝነት አካል ነሥቶ በመቅደስ ስለ ተንጎማለለ ነው፤ ነገር ግን በድፍረት እንዲህ እላለሁ፤ ወደፊት ተስፋ ለማይሰጥ ነገር መቆምና መጋደል፤ መታገልና መድከምን ያህል ምስኪንነትና ሞኝነት የለም።

አማኞች ሆይ፤ በእምነት የአብርሃም ልጆች አልያም አብርሃምን የምትከተሉ ከኾናችሁ፣ እግዚአብሔርን በማመንና በተገባላችሁ ተስፋ ጽኑና እግራችሁን አንሥታችሁ ወደ ተሰቀለው ክርስቶስ በጽናት ተራመዱ! “ይህን መመሪያ ለሚከተሉ ኹሉና የእግዚአብሔር ወገኖች ለኾኑት እስራኤላውያን ሰላምና ምሕረት ይሁን።” (አት) አሜን።



My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/02/blog-post_18.html My Twitter link - https://twitter.com/DiyakonTeklu/status/1626836348475940864?t=ELu39xY3-UQyw0T1HcK59A&s=19
260 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ