Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-01-30 21:13:35 እውነተኛ ክርስትና፣ ክርስቶስን ወደ መምሰል ማደግ ነው። ወደ ሕይወት ራስ ወደ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እንደግ!
145 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 14:35:43 ከዘር ፖለቲካ ባልተናነሰ፣ የሃይማኖት ፖለቲካም ኢትዮጵያን ሌላ ዋጋ ያስከፍላታል። ኢትዮጵያ ደም የሚፈስባት ቤተ መንግሥታዊም፤ ሃይማኖታዊም ምክንያት አለመጥፋቱ ልብ ያደማል።
272 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 22:37:15
ይህ አባባል፣ የዘርዐ ያዕቆብን ነፍሰ ገዳይነት ያጎላል። እስጢፋኖሳውያን ሹመትና መንበር አልፈለጉም፤ ከወንጌል ምስክርነትና ከጸሎት፣ በሥራ ከመትጋት በቀር ተአምረ ማርያም አንቀበልም ነበር ያሉት። ምነው ሹመኞቹ መች ተአምሯን ካዱና! ምነው መዘባረቅ በዶክተሮቹ ባሰሳ?!
307 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 09:28:46 የአዳዲሶቹ ጳጳሳት ሹመት ስጋት፣ ተስፋዬና ትዝብቴ


ጌታ እግዚአብሔር በሉዓላዊ አምላክነቱ፣ ክፉውን ነገር ኹሉ ለክብሩ ሊጠቀምበት፣ ወደ በጎ እንደሚያመጣው እናምናለን፤ ኀጢአት እንኳ ከእግዚአብሔር የሉዓላዊነት ወሰን አልፎ አያውቅም፤ እናም በምድራችን ላይ የምንሰማውን መለያየትና ጥቅመኝነትን ጌታ እግዚአብሔር አጥፍቶ፣ ለሕዝባችን መታነጽና ለክብሩ ታላቅነት እንዲሠራ ከኹሉ በፊት አስቀድመን እንማልዳለን።

አዎን! እግዚአብሔር የፈርዖንን ልበ ደንዳናነት፣ ለሕዝቡ ጥበቃና ትድግና እንደ ተጠቀመበት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው ስንል፣ በመላለሙ ላይ መጋቢና ሠራዒ፤ አስተዳዳሪና ጌታ ነው እያልን ነው፤ ስለዚህ የምድራችን ነገር የሚገደውና የሚያስብልን ተንከባካቢና ጻድቅ ጌታ አለን ማለታችንም ነው!





የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ፣ በዚህ ሳምንት “ሕገ ወጥ ናቸው” ባሉት የጳጳሳት ሹመት ላይ ውግዘት አስተላልፈዋል። አዲሶቹ የተሾሙት ጳጳሳት ደግሞ፣ በዚህ መንገድ የሄዱበትን አካሄድ ምክንያቱን ሲናገሩ፣ “በቋንቋዎቻቸው ሕዝቦች ወንጌል ሊሰሙ ይገባል” የሚል ማጠንጠኛ አለው።

በቋንቋቸው ሕዝቦች መገልገል አለባቸው መባሉ እውነት ቢኾንም፣ ይህን ግን በስህተት መንገድ በመጠየቅ የሚፈጸም አይደለም፤ ስህተት በስህተት መንገድ አይስተካከልምና። ወንጌልን መስማት በገዛ ቋንቋ መኾኑን ማንም የማይክደው እውነት ነው፤ ይህን ለማድረግ ግን በሰው ሥርዓትና የፖለቲካን በትር መጠቀም፣ የዓመጽን መንገድ መምረጥ፣ ሰዎችን ለጥፋትና ለደም ማፋሰስ መጋበዝ፣ ኅብረትን በሚንቅና በሚንድ መንገድ መሄድ … አግባብ ነው ብዬ አላምንም።

ለዚህ ውጤት ማሳያ፣ በምዕራብ ወለጋ ከምትገኘው ጊምቢና ሌሎችም አንዳንድ ከተሞች ላይ የሚደረገው እንቅስቃሴና ቅስቀሳ አሉታዊ ነገሩ ያመዝናል። በተለይም የወለጋ መስመር በብዙ መልኩ በብዙ ደም የተነከረ፣ በሰቆቃ የተዋጠ፣ አያሌ ውድመት የደረሰበት … መስመር ነው። እናም “አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ጳጳሳት” በገዛ ቋንቋው እናስተምረዋለን ያሉት ሕዝብ፣ ደሙ እንዳይፈስ፣ በሞት እንዳይቀጠፍ፤ ምድራዊና ሰማያዊ ኑሮው እንዳይጐሳቆል ሊጠነቀቁለት ይገባል። ሰዎች ኹሉ ወንጌልን እንዲሰሙ መትጋት እንጂ፣ የዘረኝነት ፖለቲካ በደቆሳትና ድህነት ባደቀቃት ምድር ላይ ሌላ ሃይማኖታዊ ጥላቻን መዝራት አይገባም፤ እንኳን ሃይማኖታዊ ግጭት ተጨምሮበት፣ የዘረኝነቱን ጦስ ገና አልተላቀቅነውምና፤ ይህ ጽኑ ስጋቴ ነው።

ሌላው ተስፋዬ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ይህን እንደ መልካም ዕድል ከተጠቀመችበት የሚፈነጥቅ አንድ ተስፋ እንዳለ አስተውላለሁ። በርግጥ አዳዲሶቹ ተሿሚ ጳጳሳት “ለቅዱስ ወንጌል ትምህርትና ሕይወት ሩቅ” መኾናቸውን አውቃለሁ፤ እንዲሁም ከጥቂቶቹ በቀር፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ውስጥም ያሉት ጳጳሳት እንዲሁ። ዳሩ ግን እውነተኛ የወንጌል እሳት በምድሪቱ ላይ እንዲቀጣጠል ይህ ምክንያት ይኾንን? የሚል ተስፋ አጭሮብኛል፤ ይህ እንዲጭርብኝ ያስገደደኝ፣

1. የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሲኖዶስ ባስተላለፉት ውግዘት ውስጥ፣ ሌሎች መንፈሳዊ ኅብረቶችን ወይም የእምነት ተቋማትን አዎንታዊና አጋራዊ በኾነ መንገድ የመቀበል ትክክለኛ አዝማሚያ አሳይተዋል። እንደ እኔ ግምት ይህን በኦርቶዶክስ ውስጥ የታየ አዲስ ፍንጣቂ ተስፋ ነው።

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ በአብዛኛው የምትታወቀው ሌሎችን በማግለልና ራስዋን ብቸኛ የመዳን መንገድ አድርጋ በማቅረብ ነበር፤ አኹን ግን ከዚህ ፈቀቅ ብላ ሌሎችን እንደ አጋር መቁጠርዋ ይበል የሚያሰኝ እውነት ነው። የተሐድሶ አንዱ እርምጃ ልበ ሰፊነትና እውነትን በትክክል መፈተን ነውና!

2. በቋንቋዎች ማገልገል የሚለው ዐሳብ፣ ቀለል ብሎ ቀርቦአል፤ ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ከግዕዝ ቋንቋ የበላይነት ይልቅ (በግሌ ግዕዝ ጠል አለመኾኔ ይታወቅልኝ) ወንጌል ለኹሉ ደግሞም በሚሰሙት ቋንቋ እንዲሰበክ በር ይከፍታል የሚል ጽኑ ተስፋ አለኝ። ከዚህ ባለፈ ደግሞ ምናልባት ለአስተዳደራዊ ተሐድሶ ምክንያት ይኾንን?

ከዚህ ባሻገር በውስጤ የተፈጠረ ትዝብትም አለ፤ ሲኖዶሱ፣ ለአዲሶቹ ጳጳሳት ምላሽ የተፋጠነውን ያህል፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መሪዎች ባለፉት ኹለትና ሦስት ዓመታት በተደጋጋሚ ላደረጉት የእርስ በርስ ጦርነት አፋጣኝ ምላሽ አለመስጠታቸውን ሳስብ እጅግ እንድታዘብ አድርጎኛል። ኹለቱም አካላት ከሥልጣናቸው ይልቅ የሕዝቡ እንደ ቅጠል መርገፍ ምነው አላሳሰባቸው?

እንዲሁም የትግራይ አብያተ ክርስቲያናትም ጉዳይ ተያይዞ ቢታይና መፍትሔ፤ እልባት ቢያገኝ ምናለበት? አልያ ግን የአንድ ወገን ብቻ ሳይኾን፣ መንታ በኾነ መንገድ በኹለት ቡሃቃ የተቀመጠ፣ የኃጢአት እርሾ እንዳይኖር ፍርሃቴ ነው! ጌታ ለምድሪቱ ምሕረት ያድርግ፤ አሜን።

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ኹሉ ጸጋ ይኹን፤ አሜን” (ኤፌ. 6፥24)።


My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/01/blog-post_27.html
372 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 07:03:57 ኢየሱስ!
ለእኔ የተቸነከርከውን ችንካር አልረሳውም!
ለእኔ ነው!
351 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 20:53:53
እንበድል ይኾናል፤ ይቅርታ የጠንካሮችና የተነሣሂያን መገለጫ ነው።

Balleessu dandeenya. Dhiifama gaafachuun garuu mallattoo amoota ciccimoo fi sheenaa beekani dha.
490 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 12:05:58
ዳንኤል ክብረት ብልጥና ልጥጥ ዐሳብ ተከታይ ነው። የተደረገውን የጳጳሳት ሹመት መጀመሪያ ተቃወመና "ለቤተክርስቲያን ውርደትና ተግባሩም ሕገወጥ ነው" ብሎ ጻፈ። ከዚያ ቤተ መንግሥት ያለው አለቃው ፊት ሲነሣው፣ (ምናልባት አለቃው ከሰዎቹ ጋር ንግግር ይኖረው ይኾን? እንጃ) "ከሕገ ወጦቹ ጋር መነጋገር ይሻላል" የሚል የለዘበ ዐሳብ አንጸባረቀ። ሎሌነት ያስ ጠላል፤ የራስ አቋምን ለሰውና ላላመኑበት ነገር መጣል ይሰቃል። ሕገወጦችንና መልካም ምሳሌ የሌላቸውን ምግባረ ብልሹ ግለሰቦችን ለመቃወም፣ የሰውን ፊት እያዩ መናገር የለየለት አለማ ዊነት ነው።
590 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 09:18:05 ኦርቶዶክስ፣ ፍጡራንን በማግነን የክርስቶስን የመስቀል ሥራ እንዳክፋፋች በተደጋጋሚ ከጻፉት መካከል ነኝ። ለዚህ ብድራቷ "በከፋ ምግባረ ብልሹነት በተዘፈቁ ሰዎች" እጅ "ትውደቅ" ብዬ ግን አልፈነድቅም!
810 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 21:10:12 ዮናታን/ይነበብ አክሊሉ ምርጥ "የሰባኪ" ተዋናይ ነው፤ መንግሥታዊም፤ "ቸርቻዊም" ተልዕኮ ይሰጠዋል፣ ተልዕኮውንም በትክክል ይፈጽማል። እግዚአብሔር ግን በዙፋኑ አለ!
596 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 16:30:12 ዛሬም!
እግዚአብሔር ዛሬም ሉዓላዊ ነው!
ክርስቶስ ዛሬም ቤዛ ነው!
መንፈስ ቅዱስ ዛሬም አጽናኝ ነው!
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ታስፈልገናለች!
ሰይጣን ዛሬም አሳችነቱን አልተወም!
ወንጌል ዛሬም የመዳን ምሥራች ነው!
የጌታ ክብር ዛሬም ምድርን እያሸፈነ ይሄዳል!
የጌታችን ቃል ዛሬም እያሸነፈና ምድርን እየከደነ ይሄዳል!
613 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ