Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-01-22 14:18:44 “ጳጳሳቱ”ም እንደ “ጐበዝ አለቃ”
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ለቍጥር በሚታክቱ የጐበዝ አለቆች ሥር ወድቃ ታውቃለች፤ እኒህ የጐበዝ አለቆች “ለሕዝባቸው” ዘለላ ርኅራኄ የላቸውም፤ ሕዝባቸውን ቆራርሰው ከማስጨነቅ፤ የራሳቸውን ልድልድና ምቹ የዙፋን ሠረገላ ከማመቻቸት የዘለለ፣ ሕዝቡን ሲፈይዱ አልታዩም። እንዲያውም “የሰኞ ገዳይ”፣ “የማክሰኞ መጋቢ” ተባብለው በሳምንቱ ቀናት ላይ ተሿሹመው አስጨናቂ አስገባሪዎች እንደ ነበሩ ዛሬም ድረስ የምናስተውለው እውነታ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም እንዳለመታደል ከዚህ ዕጣ ፈንታ አላመለጠችም። ለዘመናት ቤተ ክርስቲያኒቱ “በአንድ ቋንቋ ብቻ ከማስተማር ተቆጥባና የአስተምኅሮ ዝንፈቷን አስተካክላ” ለምድራችንና ለአኅጉራችን ብሎም ለመላለሙ “የፍሬ በረከት ትኾን ዘንድ” የተለያዩና በየዘመናቱ ያላቋረጡ የተሐድሶ ጥሪዎች ሲደረጉላት ነበር። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያቱ ለዘመናት ከመስማትና እንከኖቿን ከማስተካከል ይልቅ በግብዝነት የእልኸኝነት መንገዷን ገፍታበት ቆይታለች።
ነገር ግን “አዲሱና ሥልጣን በእጁ ከጨበጠው መንግሥት ጋር ያበረውና የተባበረው ትውልድ” ጉዞዋን ከእባብ ወደ ዘንዶ አፋጥነው አሳደጉላት እንጂ በሚሻል ነገር አልፈየዱላትም። ከሰሞኑ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው “የኦሮሞ ጳጳሳት ሹመት” ጉዳይ፣ በአደባባይ በ”ጳጳስ” ሳዊሮስ “ፓትያርክነት” አዳዲስ ጳጳሳት ሹሞ ብቅ ብሎአል። ይህ ተግባር እንደ አገርም፤ እንደ ቤተ ክርስቲያንም ታላቅ ውርደት ነው።
እንደ አገር ሳስበው፣ ካልተዘነጋ በቀር ቤተ ክርስቲኒቱ ከጥቂት ዓመታት በፊት በአገር ውስጥና በውጭ ሲኖዶስ በሚል ለኹለት ተከፍላ የነበረችበትን ታሪኳን “በዕርቅ ቋጭታ” አንድ ኾና ነበር፤ ነገር ግን የጠብና የመከፋፈሉን ዘመን ያህል እንኳ ሳይቆይ፣ በአጭር ተቋጭቶ ቤተ ክርስቲያኒቱ ዳግም “ለኹለት ተከፈለች፤” ለእኔ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ማለት ያለ ሲኖዶሱ ፈቃድ የሚደረገው፣ የጳጳሳት ሹመት የመከፈል ያህል ይሰማኛል። የወሊሶው ጳጳስ ይህን ያህል ድፍረትን ያገኘው ከመንግሥት ጋር ባለው ሽርክና ነው የሚል ጽኑ ጥርጣሬ አለኝ! ይህ ለፖለቲካውም መጠንዛት ዓይነተኛ ማሳያ አይኾንም ግን?!
እንደ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ይህ ከውርደት ያለፈ መርገምም ነው፤ ቤተ ክርስቲያን በማናቸውም መንገድ ከመንግሥት ጋር መሻረኳ ፍጹም ይጎዳት እንደ ኾን እንጂ፣ ዘለላ ታህል የሚፈይዳት አንዳችም ነገር የላትም። የኦርቶዶክስ አዲሱ ተገንጣይ “ባለ ጳጳሳት ቡድን” ይህን እውነት፣ የመከፋፈልን መዘዝ “በአጭር ዕድሜ እየተነካከሰ” ካለው ከወንጌላውያን(ከፕሮቴስታንት) “ኅብረት” ሊማር በቻለ ነበር። ነገር ግን ያልታደለው “የሳዊሮስ ቡድን” በመከፋፈል መንገድ ነጎደ!
ልዩነትን መፍጠርና የራስን ምኞት መከተል የተገለጠ ኀጢአት ነው፤ ክፉ ምሳሌነትም ነው። ይልቅ በዚህ ጊዜ በርን ገርበብ አድርጎ ለውይይት መቀመጥ፣ የሕዝባችንን ሰቆቃ መመልከት፣ በልዩነት ቋፍ ላይ ያሉትን “ትግራይንና ኢትዮጵያን” በሰላም ቃል ማሸማገል፣ ወንጌል ላልደረሰውና በተለያዩ የፍጡራን አምልኮ ለተዋጠው ማኅበረ ሰብ መራራትና ወንጌል ማድረስ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለውን የፍጡራንና የገድላትን ገናናነት ማስወገድ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሰዎችና ከቤተ ክርስቲያን ቃል በላይ እንዲከበር መሥራት፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን መፍራትና ሌሎች እጅግ አያሌ የቤት ሥራዎች እያሉ የጎበዝ አለቆችን መንግሥትን ታምኖ ማሠማራት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ብሎም ለአገር እጅግ ክፉ መንገድ ነው፤ እስራኤልን ለኹለት የከፈለው ኢዮርብዓም፣ በእስራኤል ላይ ያደረገው መቼም መልካም አልነበረም! እናም ሳዊሮስን እግዚአብሔርን ይገስጽህ ከማለት በቀር ምን እንላለን?
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ግን አኹንም ቀኑ አልባጀባትም፤ ፍትሐ ነገሥታዊ አንቀጾችን ጠቅሶ ከመወጋገዝና ከመገፋፋት፤ ለወንጌል እውነት በመሸነፍ ሕዝቡ የሚሻውን ወንጌል ለመናገር መድፈርና ቤተ ክርስቲያኒቱ መልሳ ራስዋን ለማየት ጊዜው አኹን ነው ብለን እናምናለን! ወንጌልን መግፋት፣ ኢየሱስን መተው ኦርቶዶክስን ከዚህ በላይ ዋጋ እንዳያስከፍላት እፈራለሁ፤ የዚህ ኹሉ መፍትሔው ኢየሱስን ማክበር፣ የተገፋው መስቀሉንና የመስቀሉን ሥራ በቦታው መመለስ፣ ዕድፈትና ኀጢአተኝነትን መጠየፍ ይገባታል!
ጌታና እውነተኛ እረኛው ኢየሱስ ለሕዝባችን ይራራ! አሜን። my blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/01/blog-post_22.html
923 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 14:23:24 በቃና ዘገለላ (በገሊላ አውራጃ በገሊላ ከተማ)

“ኢየሱስ... የታምራዊ ምልክቶቹ መጀመሪያ... አደረገ[ውኃውን ወደ ወይን ለወጠ]፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።” (ዮሐ. 2፥11)
480 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 20:36:22 በውኃ ጥምቀት የልጅነት ጸጋ ይገኛል የሚሉ፣ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ጨርሰው አያስተውሉም፤ ሰው በመንፈስ ቅዱስ ካልተጠመቀ በቀር፣ የእግዚአብሔር ልጅ አይኾንምና።
571 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:09:31 የመንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ መውረድ


በጥምቀት ወራት ከሚነሡት ዐሳቦች መካከል አንዱ፣ “ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤” (ማቴ. 3፥16) የሚለው ቃል ይታወሳል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በጌታችን ላይ ወረደ።



ጌታችን ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ነው፤ ደግሞም ፍጹም ሰው ነው፤ በአምላክነቱ መታዘዝ የሌለበት ጌታ በፍጹም ሰውነቱ ለመንፈስ ቅዱስ ታዘዘ፤ ደግሞም ተገዛ። መሲሑ በመስቀል ሞት በመታዘዝ ተሰቅሎ ያድነንና በጽድቅ መንገድም በመታዘዝ የሕግ ፍጻሜ እንዲኾን ለመቀባቱ ምልክት ይኾን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ ወረደ።

በነቢይ መጽሐፍ፣ ስለ መሲሑ እንዲህ ተብሎ ተነግሮለታል፤ “የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።” (ኢሳ. 11፥2) መሲሑ በመንፈስ ቅዱስ መቀባቱ፣ በሰውነቱ ፍጹም ለእግዚአብሔር መታዘዙን የሚያመለክት ነው። የእግዚአብሔር ወልድ ትህትና እጅግ አስደናቂ ነው።

ስለ እግዚአብሔር ባሕርያት በተደጋጋሚ ስናጠና፣ ስለ ትህትናው እምብዛም ተነግሮን አናውቅም፤ ዳሩ ግን ስለ መዳናችን ዘወትር ስናወሳ ትዝ የሚለን እውነት፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍጹም ትሁትነትና የእኛን ሥጋ ከመልበሱ ጀምሮ እስከ ውርደት ሞት የታዘዘው መታዘዝ ፍጹም ትህትናን ማዕከል ያደረገ መኾኑ ነው።

ይህን እውነት ማዕከል አድርገን፣ ስለ ርግብ ስንናገር፣ ርግብ በአይሁድ ማኅበረ ሰብ ዘንድ የገርነትና የሰላም ምልክት ናት። መንፈስ ቅዱስ ወደ መሲሑ ሲመጣ፣ እንደ ርግብ በመውረድ ነበር ስንል፣ መጥምቁ ዮሐንስን ጨምሮ ኢየሱስ ይመጣል ብለው ጠብቀው የነበረው፣ ታላላቅ መንግሥታትን ድል በመንሣት፣ ከሮም ቅኝ ግዛት አይሁድን ነጻ በማውጣት፣ መሲሐዊ ድል ነሺ መንግሥትን በመመሥረት … በኃይል እንደሚመጣ ጓጉተው ነበር።

ነገር ግን መሲሑ የተገለጠው፣ “ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ።” (ሉቃ. 3፥21) እንዲል፣ እንደ ማንኛውም ኀጢአተኛ ኢየሱስ ተሰልፎ፣ ከታላቅ ትህትናው የተነሣ ሰው ኹሉ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስ በመጨረሻ ተጠምቆ ነው። ፍጹም ትሁቱ ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲታይ፣ ከኀጢአተኞች እንደ አንዱ ተቆጥሮ፣ እኛ ኀጢአተኞችን ከትዕቢት ከፍታ አውርዶ በትህትና ወደ እግዚአብሔር እግር ሥር ይወስደን ነው።

ቤተ ዘመዶቹ ሳይቀር እንኳ፣ ኢየሱስ በኃይልና በሥልጣን፣ በአስፈሪ ግርማ እንዲገለጥ ደጅ ቢጠኑትም እርሱ ግን በፍጹም ትህትና ተገለጠ። በድጋሚ፣ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደ ስንል፣ ትሁቱንናን በትህትናውም እጅግ አስደናቂ የኾነውን ጌታ በማስተዋል እንድንከተለው መንፈስ ቅዱስ እያስተማረን ነው። እንዲህ አለ መሲሑ፣ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤” (ማቴ. 11፥28-29) አለ፤ ሸክማችንን የሚሸከምልን ጌታ በትህትናው እጅግ፤ እጅግ ትሁት የኾነው ጌታ ነው፤ ስሙ ይባረክ፤ አሜን!


My blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/01/blog-post_18.html
710 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 13:29:15 "ማንኛውንም ነገር እንደ እርሱ ፈቃድ ብንለምን እንደሚሰማን እንተማመናለን።" (1ዮሐ. 5፥14)
167 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 10:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 14:52:46 አእመረ አሸብር፣ "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አንልም፤ ማርያም አርጋለች የሚል ሌላ መጽሐፍ ካለ እንቀበላለን" ብሎ "ከነዮኒ ማኛ" ሲያወራ ሰማኹ ልበል? ቅዱስ ቃሉን የመናቅ ጥግ!
310 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-15 04:04:00 ጌታችን ኢየሱስ ከቅድስት ድንግል ሥጋ በመንሣቱ መካከለኛችን እንደ ኾነ በትክክል ሳይረዳ፣ ወንጌል እያገለገልኹ ነው እንደሚል ሰው ያለ ምስኪን በምድር ላይ ያለ አይመስለኝም።
332 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 01:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-14 14:01:18 በክርስቶስ ኢየሱስ የሚገኝ የኅጢአት ይቅርታ፣ ከፈውስና ሙት ከማስነሣት የበለጠ መንፈሳዊ ደስታ አለው!
368 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-13 16:17:48
ነውራችን በአደባባይ!
ይህ የምትመለከቱት “ነቢይ ነኝ ባይ አገልጋይ” በኦሮሚያ ክልል በኢሉአባቦር ዞን፣ በሁሩሙ ወረዳ፣ “የተቀደሰች የእግዚአብሔር ተራራ ዓለም ዓቀፍ ቤተ ክርስቲያን” የተባለውን መሥራችና ባለራዕይ ነው! በዚህ ሰው ላይ የሁሩሙ ወረዳ ፍርድ ቤት የ8 ዓመት እና የ5 ወር ጽኑ እስራትና የብር 4000 ሺህ ቅጣት አስተላልፎአል፡፡
ይህ “አገልጋይ ነኝ” ባይ፣ “አገልጋይ መኾኑን በመጠቀም” አራት የተለያዩ የራሱን ቤት (ቤተክርስቲያን ማለት ስለሚቸግረኝ) ሴቶችን አስረግዞ ሚሶፕራዛል የተባለ የውርጃ መድኃኒት በማስዋጥ፣ ፖሊስ ጣቢያም ከገባ በኋላ በድብቅ ባስገባውና በእጁ በተያዘው የእጅ ስልክ፣ የተለያዩ ወሲብ ቀስቃሽ ዕርቃን ምስሎችን፣ የዝሙት ቪዲዮዎችን፣ ራሱም ከሌሎች ሴቶችና ወንዶች ጋር ከተፈጥሮ ውጭ በኾነ መንገድ ዝሙትና ሰዶማዊ ተግባር ሲፈጽም በመገኘቱና ይህም በማስረጃ በመረጋገጡ በ2/5/2015 በዋለው ችሎት “ነውረኛው አገልጋይ” ተቀጥቶአል፡፡
በተደጋጋሚ የስህተት ትምህርቶችን የምንቃወመው፣ ሰዎች የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፣ ለአጋንንታዊ ልምምድ ተላልፈው እንዳይሰጡና የማንም ወፈፌ መጫወቻ እንዳይኾኑ ለማድረግ ነው! ደግመን እንላለን፤ የሐሰት መምህራን በተከታዮቻቸው ብዛት እውነተኛ መኾናቸው አይለካም፤ የእውነት መለኪያው የኢየሱስ ሕይወትና ትምህርት ብቻ ነው! ጌታ ለሕዝባችን ይራራልን፤ አሜን!
1.2K views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-12 06:44:59
ታምራት CJ በዓለማችን ከታወቁ "የቃል እምነት እንቅስቃሴ መምህራን" ጋር የዳበረ ግንኙነት እንዳለው፣ በአገራችን "በእምነት ቃል እንቅስቃሴ" አስተማሪነቱ የሚታወቀው ኃይሉ ዮሐንስ ይመሰክራል። በአገራችን "የእምነት እንቅስቃሴ መምህራን" ቁጥራቸው ትንሽ አይደለም፤ ከትምህርታቸው አንዱ፣

"ባለጠግነት ያልለፋህበትንና አንተ ላብህን ጠብ ያላደረግህበትን የሌላውን ሃብት ለራስህ መሰብሰብ ነው" ይላሉ። እንዲህ ብለው ከሚያስተምሩት መካከል ዮናታን አክሊሉ፣ ታምራት CJ፣ ደረሰ "catman" (ማለቴ ድመት "ፈዋሹ ሰው) እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፣

“በአካሄዱ ነውር የሌለበት ድኻ፣ መንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይሻላል።” (ምሳ. 28፥6)

“ሊሠራ የማይወድ አይብላ" (2ተሰ. 3፥10)

“... እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤” (2ጴጥ. 1፥8)


"ስለ ስሙ የወጡት ከአሕዛብ ምንም ሳይቀበሉ ነውና። እንግዲህ አብረን ለእውነት እንድንሠራ እንዲህ ያሉትን ሰዎች ልናስተና ግድ ይገባናል።" (3ዮሐ. 7-8)

እናም፣ ደጋግመን እንደምንለው እርስ በእርስ እየተሞጋገሱ በማማለል ከሚያስቱ አሳቾች ተጠንቀቁ። የሥራ ባህል ደካማ በኾነባት በኢትዮጵያ ምድር ላይ፣ የሌላውን ሀብት እንድንመለከት ከሚያደርጉ ነውረኛ አሳቾች ተጠበቁ!
521 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ