Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-12-27 07:19:11 ጌታችን ኢየሱስ የሕይወት ምንጭ ነው፤ ቅዱሳን ኹሉ የእርሱን ሕይወትነት ይራባሉ፤ ይጠማሉ፤ ይናፍቃሉ። አሜን።
172 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 18:33:07
መቼም ልረዳው የማልችለው መራራ እውነት!
እንዲህ "በወንድማማችነት" መተያየታችንና አብረን መቀመጣችን ላይቀር፣ ያ ኹሉ ሰቆቃና ዋይታ በምድሪቱ ለምን እንዲኾን ተፈቀደ?! ያ ኹሉ ደም ለምን ነበር?!... ጌታ ሆይ፤ አንተ ብቻ ጻድቅ ነህ!
246 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 17:34:45 ከማናቸውም የኀጢአት ቁስልና ጠባሳ የሚፈውሰው፣ ቁስለኛው የናዝሬቱ ኢየሱስ፤ የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ ነው!
248 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 16:13:56 [2] Taddesse Tamrat. “Hagiographies and the Reconstraction of Medieval Ethiopian History.” Confrence on Current Research Trends in Ethiopian History. Addis Abeba: A.A,U., I.E.S., 1970

[3] ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ ሐመረ ተዋሕዶ(የሐመር መጽሔት ልዩ መጽሔት)፤ ሚያዝያ 1999 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ አሳታሚ ማኅበረ ቅዱሳን።


my blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2022/12/blog-post_25.html
297 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 16:13:56 ሄኖክ ኃይሌ(ዲያቆን) ስለ አዋልድ መጻሕፍት ያሳየው ደካማና ጠንካራ ሙግቱ!


ሄኖክ ኃይሌ፣ ስለ ተአምረ ማርያም በጻፈው ኹለተኛ ክፍል ላይ እስካኹን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ አዋልድ መጻሕፍትን (ማለትም ትርጓሜያትን፣ ገድላትን፣ ድርሳናትን፣ መልክዐ መልክዕን፣ ተአምራትን፣ ነገራትን፣ ፍካሬያትን) ለማስተካከልና ለማደስ የተቸገረችበትን ምክንያት ሲጠቅስ እንዲህ ይላል፤

“ … ላለፉት ሠላሳ ዓመታት ያሳተሟቸውና በነጻ ያደሏቸው መጻሕፍት … ክርስቶስን ‘ጨርሶ አታውቂም’ የሚሏትን ከሳሾችዋን በማስታገሥ ሥራ ላይ ተጠምዳ እንድትቆይ ግድ ኾኖባት ቆይቶአል።”


በገድላት ላይ እንዲህ ያለ ችግር የመጣበትንም ምክንያት ሲናገር፣

1. ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ሲገለበጡ የዐሳብ መጥፋት፣

2. ጸሐፊያኑ በራሳቸው የሥነ ጽሑፍ ስልት ታሪኮቹን ሲተርኩ የሚጨምሯቸው አንዳንድ አንቀጾች፣

3. የመንደር ማተሚያ ቤቶች መኖር፣

4. የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር ማቃለል የሚፈልጉ ወገኖች በሚሠሩት የተንኮል ሤራ እንደ ኾነ ይናገራል።

ሄኖክ ላለፉት 30 ዓመታት ብቻ ሳይኾን፣ ተአምረ ማርያምን ፊት ለፊት ከተቃወሙት ከእስጢፋኖሳውያን ዘመን ጀምሮ፣ አዋልድ መጻሕፍት እንዲስተካከሉ አያሌ ዋጋዎች ተከፍለዋል። ከዚህም ባለፈ በተለያየ መንገድ እጅግ አስተማሪ የኾኑ ጥናቶች ሲቀርቡ ኖረዋል፣ (ለምሳሌ፦ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ የጌታቸው ኃይሌን (1968 ዓ.እ.)፣ የታደሰ ታምራትን (1970 ዓ.እ.)፣ የሰላማዊት መካን (2006 ዓ.እ.) መጥቀስ ሲቻል፣ በአማርኛ ደግሞ የሰባሄ ካሳውን 1981 ዓ.ም)፣ የሰርፀ ገብረ መድኅንን (1982 ዓ.ም)፣ የኤልያስ መንግሥቱንና (1997 ዓ.ም) እንዲሁም እነ ዲያቆን አግዛቸው ተፈራ፣ ሊቀ ጉባኤ አበራ በቀለ፣ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፣ አባ ገሪማ የሠሩአቸውን ሥራዎች) መጥቀስ ይቻላል።

አራጌ ይመር በወለተ ጴጥሮስና በፍቅርተ ክርስቶስ ላይ በተሠራ አንድ የገድላት ጥናት ላይ እንዲህ ቀርቦአል፤

“ … ተራኪዎቹ የሴቶቹን ታሪክ ሲያቀርቡ ግራ የመጋባት፣ የማወላወልና የመጠራጠር ነገር ይታይባቸዋል። “የሚስተካከላት የለም” ባሉበት አንደበታቸው፣ መልሰው ‘ተከለከለች’ ይሉናል። ‘የምድር ነገሥታት ለእርስዋ ይሰግዳሉ’ ባሉበት አንደበት፣ እንደገና ‘ሸሸች፣ ተደበቀች፣ አለቀሰች’ ይሉናል። … ይህን የሚያደርገው የገድሎቹ ተራኪዎች አድሎአዊ ስለኾኑ ወይም የገድሉ ባሕርይ ኾኖ ሳይኾን የሃይማኖቱ አባዊ ተፈጥሮ ነው። …”[1]

ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በተጨማሪ እንዲህ ይላሉ፣

“ብዙዎቹ ገድሎች የሚጻፉት ተጋዳልያኑ ከሞቱ ከብዙ ዘመን በኋላ በመኾኑ፣ የገድሎቹ ጸሐፊዎች ስለ ግለሰቦቹ የሚነገሩ አባባሎችን፣ ተረኮችን፣ ታሪኮችን፣ ትውፊቶችን መሰብሰብና በጽሑፍ መልክ ማዘጋጀት ግድ ይላቸዋል። ጥቂቶቹ ገድሎች ደግሞ ቅዱሳኑ እንደ ሞቱ ወዲያው ስለሚጻፉ ጸሐፊዎቹ (ምናባዊ ፈጠራ በብዛት ሳይጨምሩ) በገሃድ የሚያውቁትንና የሚያስታውሱትን ይጽፋሉ። በዚህ ዓይነት መንገድ በሚጻፉ ገድሎች ውስጥ የሚቀርቡ ተጋድሎዎች ‘ተራ’ እና ‘የዘወትር’ መምሰላቸው አይቀርም።”[2]

እንግዲህ የገድላት ተሐድሶ ጥያቄ የረጅም ዓመታት ጥያቄና ውትወታ መኾኑንና ጥያቄውም ዳጎስ ያለና ሊስተባበል የማይችል ነበር መላት እንችላለን።

በሌላ በኩል ሄኖክ፣ ስለ አዋልድ መጻሕፍት፣ አንድ አስደናቂ ንግግር ተናግሮአል፤

“ገድላት፣ ድርሳናትና ተአምራት ሲነሡ ‘ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሌላ መጽሐፍ አንፈልግም’ ብለው የሚተቹ አካላት መጽሐፍ መሸጫ መደብሮቻቸው ጎራ ብትሉ ‘ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አይሸጥም’ አይሏችሁም። መጽሐፍ ቅዱስን የሚያብራሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች፣ የሚሲዮናውያን ታሪኮች፣ ‘ሲኦል ደርሶ የመጣው ሰው ምስክርነት’፣ የወንጌላዊው እገሌ የአገልግሎት ግለ ታሪክ ወዘተ የሚሉ መጻሕፍት መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው? አዋልድ መጻሕፍት ማለት ይሄ ነው።”

ይህ እጅግ አስደናቂ ምስክርነት ነው፤ እንዲያውም፣ ሄኖክ፣ “አሜሪካ የተስፋ ምድር ናት” የሚሉ አዋልድ መጻሕፍት ጭምር አሉ እስከ ማለት ከደፈረ፣ “ለመታደስ” የሚደረገው ጉዞ ይበል የሚያሰኝ ነው ማለት እንችላለን። ከዚህ በፊት አዋልድ መጻሕፍትን በተመለከተ ያለው ምስክርነት ግን በተቃራኒው ነበር፤ ዳንኤል ክብረት(ዲያቆን) እንዲህ ብሎ ነበር፤

“የሰው ዘር አባትና እናት አዳምና ሔዋን ናቸው፤ ልጆቻቸው ግን በዝተዋል፤ ሞልተዋል፤ ይበዛሉም፤ ይሞላሉም፤ አዋልድ መጻሕፍትም አባት እናታቸው አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ቢኾንም ልጆቻቸው ግን በዝተዋል፤ ሞልተዋል፤ ይበዛሉም፤ ይሞላሉም”[3]

ሄኖክ ግን፣ አዋልድ መጻሕፍትን በዚህ ልክ እንዲታዩ መጻፉ ይበል የሚያሰኝ ነው። በነገራችን ላይ ሄኖክ ወደ ወንጌላውያን የመጻሕፍት መደብር ጎራ ብሎ ያስተዋለውን ትዝብት እኔም እጋራዋለሁ፤ የምጋራው ግን ክርስቶስ ሰምራ ወደ ሲዖል ወርዳ የመመለሷን ነገር፣ የወንጌላውያን መንደር አለ የተባለውን ‘ሲኦል ደርሶ የመጣው ሰው ምስክርነት’ በማመሳሰል ነው!

ሌላው፣ የተአምረ ማርያም መጽሐፍ የተጻፈበትን ጊዜም ማስቀመጡ አስደናቂ ምስክርነት ነው፤ የተጻፈበትን ዘመን 13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ብሎታል፤ ይህም ጊዜ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የነገሠበት ጊዜ መኾኑን አንስተውም። ዘርዓ ያዕቆብ ደግሞ፣ ደቂቀ እስጢፋኖስን በመግደልና በእነርሱ ላይ አሰቃቂ መከራ በማድረስ የታወቀ ሰው እንደ ነበር በታሪክ ሊዘነጋ የማይቻል እውነት ነው፤ ሄኖክ ግን ‘በዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ብቻ አልተጻፈም’ ለማለት መልሶ ይክድና፣ ሌሎቹም (ማለትም ዐፄ በካፋ፣ ዳዊትና ቴዎድሮስ) ግን የየራሳቸውን አስተዋጽኦ ማድረጋቸውንና በዘመናቸው የነበረውን ተአምር ማስፈራቸውንም ይናገራል።

በክፍል ኹለት ጽሑፉ ሄኖክ ኃይሌ፣ ሌላ (በርግጥ የተለመደ ነው) አደገኛ ስህተት ይስታል፤ እንዲህ በማለት፣

“ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳንስ አዋልድ መጻሕፍትን ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትንም መጻሕፍት ከብዙ መጻሕፍት መካከል መርጣ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ብላ ወስናለች… ‘ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ሠጠችን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን አልሰጠንም’ እንደሚባለው ቤተ ክርስቲን መጽሐፍ ቅዱስን እንኳን በዕድሜ ትቀድመዋለች።”

በዚህ ጽሑፉ ሄኖክ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን ሕያው ቃል በግልጥ ይክዳል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው ብሎ የሚያምን ሰው፣ ከእስትንፋሰ እግዚአብሔር በፊት ቤተ ክርስቲያን አለች ብሎ ደፍሮ አይናገርም። “በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥” (ማቴ. 16፥18) እንዲል፣ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችው በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ላይ በማመን በጸኑ ቅዱሳን ነው። ይህን ዐሳብ በተመለከተ፣ “የመድሎተ ጽድቅ” ጸሐፊ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ሥልጣን በመጋፋት ለጻፈው ክፍል የመለስኩትን በስፋት መመልከት ይቻላል።

በመጨረሻም፣ ሄኖክ ከዚህ ጋር አያይዞ፣ የአትናቴዎስን ቀኖና መቀበሉን ካመነ ከ27ቱ የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውጭ ሌሎቹን (ግጽው ሲኖዶስ፣ አብጥሊስ፣ ሥርዓተ ጽዮንንና ሌሎችንም) ከወዴት አምጥተው ይኾን የተቀበሉት? ማለት እንወዳለን።

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ኹሉ ጸጋ ይኹን፤ አሜን” (ኤፌ. 6፥24)።


[1] አራጌ ይመር፤ የሴትነት ጽንሰ ዐሳብ በድለ ፍቅርተ ክርስቶስና በገድለ ወለተ ጴጥሮስ፤ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር የሥነ ጽሑፍ መጽሔት (ብሌን) ቅጽ 8፤ ቍ. 1(ታኅሳስ 2007፤ ገጽ 65
414 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-24 15:00:26
ሄኖክ ኃይሌ(ዲያቆን) መጽሐፍ ቅዱስን በገድል ሊያስቀና?

ሄኖክ ኃይሌ፣ ገድላት ውስጥ የማይታመኑ ታሪኮችን መቀበል ካዳገተን፣ የመጽሐፍ ቅዱስም ታሪኮች ለመቀበል ያዳግቱናል የሚል ሙግት ለማቅረብ እንዲህ ይላል፣

"መጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡... አህያ ጌታዋን ስትመክር፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር፣... ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ? አንድ አባት ‘ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?’..." ይላል።

ሄኖክ ያላስተዋላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እውነቶች፣

- የታሪኮቹ የመጨረሻው ግብ እግዚአብሔርን ብቻ ማክበር ነው።
- የታሪኮቹ የመጨረሻ ግብ ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ለሰዎች መዳን መዳረሻ የኾነ ነው።
- ለብዙዎችም የመታነጽ ምክንያት ነው።

ከዚህ የተነሣ የመጽሐፍ ቅዱስ ተአምራትና ሥራዎች ለመታመን አዳጋች ነገር የለባቸውም፤ ደግሞም የተፈጸሙና እውነት ናቸው። በዚህ ረገድ ተአምራትና ገድላት ከላይ ለተዘረዘሩት ዐላማዎችና ግቦች ከዋለ አንዳች ተቃውሞ የለንም።
ነገር ግን

- በተክለሃይማኖት ገድል ያለውን የክርስቶስን ደም የሚያክፋፋውን ትርክት፣

- በድርሳነ ዑራዔል ያለውን የተመሳሳይ ጾታ መሳሳምን ጸያፍ ትርክት፣

- ኪዳነ ምሕረት የተባለችበትን የማርያምና የበላዔ ሰብዕ ትርክት፣

- የመርቆርዮስ አሃዜ ዓለማትነት ትርክት፣

- በአርጋኖን ያለውን ማርያምን የሰገራ መውጫ መደፈንዋን የሚናገረውንና በሌሎችም ገድላትና ተአምራት እንዲሁም ድርሳናት ያሉትን ትርክቶች የወንጌል ተቃራኒ፣ ክብረ እግዚአብሔርን ጋራጅ፣ ፍጡር አግናኝና ርኩሰትን ደጋፊ ናቸውና እንቃወማለን ነው ያልነው።

መጽሐፍቅዱሳዊ ተሐድሶ ያሸንፋል።
310 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-23 06:26:03 ከሰሞኑ ግርግር ያስተዋልኩት!

1. ፖለቲከኞች ከደገሱልን የሰሜን ጦርነትና አኹንም በየቦታው ከምንሰማው ጥላቻ፣ ግድያ፣ ዕልቂት፣ አፈና፣ መፈናቀል... ገና አላገገምንም፤ በዋዛም አናገግምም! ከብሔርና ከዘረኝነት ተኮር መቦጫጨቅ ያልወጣን ኋላ ቀር ሕዝብ ኾነን፣ እንኳን ተሐድሶአውያን ይቅርና "አንዳንድ የኦርቶዶክስ "መምህራን ጭምር" እንዲታደስ ሲጠይቁ በነበሩ የገድል፣ የድርሳን፣ የመልክዕ፣ የፍካሬ... ጸያፍ ጽሑፎች ታክከው ሌላ "የጦርነትና የመከፋፈል" አጀንዳ የሚሰጡን አሉ።
"ጭር ሲል አልወድሞች!"

2. እንደ ዮናታን "መንጋውን" የሸወደና ስሙን ያስከበረ የለም፤ "የቃል እምነት እንቃስቃሴ" ነሁላላ ትምህርቱን፣ በተክለሃይማኖት "እንትን" አጥቦ፤ አጥኖ ዐረፈው! (dirty church politics!) "ጥሩ ምግብ" በዕድፋም መመገቢያ አይቀርብም!

3. የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የነገሥታት ድጋፍ በነበራት ዘመን የሠራችውን ግልጽ ስህተቶች፣ "ወንጌላውያን"ም "ወግ ደረሰን" ብለው "በካውንስሉ" አሳይተው የጀመሩትን የቁልቁለት መንገድ እንዳይቀጥሉበትና "ወንጌላዊው ክርስትና" አስቀያሚ ቅርቃር ውስጥ እንዳይገባ እፈራለሁ። በእርግጥ ወንጌላዊው ክርስትና መከራ "ወጉም ጫጉላውም" ነው!

እግዚአብሔር ግን ኹሌም በሉዐላዊ መግቦቱ አለ! አሜን።
125 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 16:44:40 የቤተክርስቲያን ተልእኮዋ ለመላለሙ ነው፤ የምትጀምረው ግን ከአንድ ሰው ነው፤ ትልቁን እዪና ከትንሹ ግን በእምነት ጀምሪ! የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ሰናፍጭ ቅንጣት ናትና!
222 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 06:40:03 መራራ ቁጭት!
ኦርቶዶክስ፣ ተአምራትና ገድላትን "ላለማስነካት" ያደረገችውን ርብርብ፣ ከሌሎች ጋር በመኾን አሰቃቂዎቹ ያለፉት ጦርነቶችን "ተዉ" ብላ ቢኾን፣ ሚሊዮናት ከሰቆቃ በዳኑ ነበር!
121 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  03:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-21 17:24:05 የኢየሱስ ትምህርት እና ሕይወት ለብዙ "ክርስቲያኖች" መራራና ሊዋጥ የማይችል ነው፤ ጥቂቶች ብቻ ግን በስብከት ሞኝነት ይታዘዙታል።
294 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ