Get Mystery Box with random crypto!

የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ebenezertek — የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ
የሰርጥ አድራሻ: @ebenezertek
ምድቦች: ኢሶቴሪክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.26K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-27 06:53:34 እውነተኛ አገልጋይ ዘወትር ይህን አይረሳም፣ “እርሱ[ኢየሱስ] ሊልቅ፣ እኔ ግን ላንስ ይገባል።” (ዮሐ. 3፥30)
ራሳቸውን ግን ከሚያተልቁ "ጌቶች" ተጠበቁ!
196 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 20:58:00 ጋሻውን ይዞ "በጋሻችን" ራሱን "ከእምነት እንቅስቃሴ አማኞች" ማለትም፣ ከነጃፒ ጎን ራሱን አሰልፎአል! መጥኔ! ለምልክት ናፋቂ አመንዝራ ትውልድ! መቼም ከዳንሳማ ይሻላል የሚል ነሁላላ መች ይጠፋና?
272 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 12:33:16 ከአገልግሎት ፊት ይቅርታ አይቀድምም ወይ?

በጋሻው ደሳለኝና ባልንጀሮቹ “የእምነት እንቅስቃሴ” ወይም “ቃል እምነቴ” የኾነውን ትምህርት ሲያራምዱ አስቀድመው ከሰሙት መካከል አንዱ ነኝ። ትምህርቱን አምኖበት ስለ ማስተማሩና ስላለማስተማሩ ስጠይቀውም፣ “ቆፍጠን ብሎ አላዋቂ መኾኔን ጭምር ጠቅሶ፣ የእምነት እንቅስቃሴ አማኝነቱን በግልጥ ነግሮኝ” ነበር። ከዚያም በኋላ ይህን ስሑት ትምህርት ባስተማረባቸው ስፍራዎችና ያስተማራቸውን ትምህርቶች ለመስማማት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጉዤ አጣርቻለሁ (ለምሳሌ፦ አዋሳ፣ መቂ፣ ዲላ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባና ሌሎችም ቦታዎች)።

በዚያ ትምህርቱ ብዙዎች ስተዋል፤ ትዳራቸውን አፍርሰዋል፤ ወደ ዓለማዊነት ፊታቸውንም የመለሱም ነበሩ። ለብዙዎችም የኬኔት ሔገንንና የኬኔት ኮፕላንድን መጽሐፎችን ከማንበብ ባለፈ ለሌሎችም ያሰራጭ ነበር፤ ከጃፒ (“ሐዋርያው” ብዙአየሁ ከሚባለው) ጋር በሽርክና በአንድነት ይሠራ ነበር።

እንግዲህ በጋሻው ደሳለኝ “ተመልሻለሁ” ካለ፣ ለእነዚህ ተግባሮቹ ኹሉ አስቀድሞ ይቅርታ መጠየቅና ለሳተበት ስህተቱና ላሳተበት መንገዱ ትክክል አለመኾኑን በግልጽ ሊናገር ይገባዋል። አልያ ግን “ታዋቂ አገልጋዮችን በማሰለፍ ብቻ” ስህተቱንና አሳችነቱን በበግ ለምድ አጊጦ ቢገለጥ፣ ለጊዜው እንጂ ከእውነተኛ አማኞች ዓይን ይሰወራል ተብሎ አይታመንም!

እናም ከአገልግሎተ በፊት ሊቀድም የሚገባው ላጠፉትና ለሠሩት ስህተት ንስሐና የበደሉትን በትክክል መካስ መኾኑን የሚጠይቅ መኾኑን ማስታወስ እንወዳለን! ይህ ባልኾነበት መንገድ ግን አገልግሎት ምንም ቢደምቅና ቢዋብ፣ በሰው እይታ “wow!” ቢያስብልም ከንቱ የከንቱ ከንቱ መኾኑን አስረግጠን እንናገራለን!
576 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, edited  09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 18:17:50 በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገው የመሪዎች ሥልጠና የሰማኹት ውብ ዜና፣ በቤተክርስቲያን ጉዞ ከሐሰተኞች ይልቅ እውነተኞችም ቁጥራቸው ትንሽ እንዳይደለ ነው! ጌታ ሆይ በስውር ስለምትሠራው እጅህ ግነን፤ ከፍ በል!
212 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 11:06:05 ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ትመሰክራለህን?


“ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10፥9)

ይህን ቃል የተናገረው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ነው፤ የተናገረውም ለሮሜ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ነው። ሐዋርያው ይህን ምስክርነት የሚመሰክረው የመዳንን ታላቅና ብቸኛ መንገድ እያመለከተ ባለበት ክፍል ነው። በሮም ምድር የቄሳር ጌትነት ገንኖ ይነገር ነበር፣ አማኞች ግን የኢየሱስን ጌትነት በመመስከር ሰማዕታት ኾኑ፤ ምክንያቱም የኢየሱስ ጌትነትን መቀበልና አለመቀበል፣ ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነውና።



አንዳንዶች የሙሴን ሕግ በመጠበቅ መዳን ይቻላል ይላሉ፤ በርግጥ የሙሴን ሕግ በመጠበቅ መዳን እንደሚቻል ሕጉ፣ “የሚሠራቸው ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” (ዘሌ. 18፥5፤ ሮሜ 10፥5) ተብሎአል። ነገር ግን ሕጉን በመጠበቅ መዳን የሚቻለው፣ ሕጉን ያለ ነቀፋና ያለ አንዳች እንከን መፈጸም ለሚቻለው ሰው ብቻ ነው፤ ነገር ግን የሕግ ፍጻሜ ከኾነው ከኢየሱስ በቀር፣ ሥጋ ለባሽ ኹሉ ሕጉን ያለ ነቀፋ መፈጸም አልተቻለውም፤ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ፣ “አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና፤” እንዲል (ሮሜ 3፥9)።

ሌሎች ደግሞ ለመዳን “ወደ ሲዖል መውረድ ይገባናል” ይላሉ (ሮሜ 10፥7)፤ ስለዚህም ቅዱስ ጳውሎስ የመዳንን መንገድ ያመለክታል፤ እርሱም የክርስቶስን ጌትነት በማመን የሚገኝ የእምነት ቃል ነው ይለናል፤ ይህን የመዳን መንገድ ለማግኘት ወደ ሰማይ መውጣትም አያስፈልግም (ሮሜ 10፥6)፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ሰዎች ኹሉ እርሱን በማመን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ክርስቶስ ኾኖ ተገልጦአል። ወደ ሲዖል መውረድም አያስፈልግም፤ እርሱ ከሙታን መካከል ተነሥቶአል፤ ወደ ሰማይም መውጣት አያስፈልግም እርሱ ወደ ምድር ወርዶ ታላቅ ጽድቅን ሠርቶልናልና፤ አሜን።

ጌታችን ይህን ሥራ የሠራው በጌትነቱ ነው፤ ወደ ሲዖል፣ “ሄዶ በወኅኒ የነበሩ ነፍሳትን ሰብኮአል፤” (1ጴጥ. 3፥19) ደግሞም፣ “በሞት ላይ ኃይል ያለውን ዲያብሎስን በሥጋ ሞቱ ደምስሶታል” (ዕብ. 2፥14-15)፤ በሰማያትም ቢኾን ቅዱስ አባቱ አብ፣ “ከግዛትና ከሥልጣን፣ ከኃይልና ከጌትነት” (ኤፌ. 1፥21) በላይ “በግርማው ቀኝ” (ዕብ. 1፥3) አስቀምጦታል፤ እናም እግዚአብሔር በሰማይም በምድርም፣ “ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት” (ኤፌ. 1፥22) ለዚህም ነው፣ በሰማያት ለታረደው በግ፣ አራቱ ሕያዋን ፍጡራንና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በፊቱ ተደፍተው(ራእ. 4፥8)፣ “ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ የነበሩ መላእክት … በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ” (ራእ. 5፥11፡ 13) በታላቅ ዝማሬ ሲሰግዱለት የምንመለከተው፤ እርሱ ጌታችን ኢየሱስ አዎን በሰማይም በምድር ጌታ ነው! ጉልበት ኹሉ የሚንበረከክለት አንድ ጌታ አለ፤ ኢየሱስ (ፊል. 2፥9-11)።

በዘመናት መካከል የኢየሱስ ጌትነት ርዕስ ያልኾነበት ጊዜ የለም። ርዕስነቱ ደግሞ በኹለት ጐራ ተከፍሎ ነው፤ አንደኛው የሚያምኑትና በነፍሳቸው ተወራርደው ወይም ነፍሳቸውን ሰጥተው ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ ሲመሰክሩ (የሐ.ሥ. 15፥25-26፤ ፊል. 2፥30)፣ ሌሎቹ ደግሞ ለኢየሱስ ልክ በሌለው ጥላቻ ተሞልተው ጌትነቱን በመቃወም የሚቆሙ ናቸው፤ በኢየሱስ ጌትነት ዙሪያ ከእነዚህ ከኹለቱ ጐራዎች በቀር ሌላ ሦስተኛ ወይም ገለልተኛ የሚባል ጐራ የለም፤ የኢየሱስን ጌትነት ካመንን ወደን እንከተለዋለን፤ በእርሱም ድነን እንቀራለን፤ ጌትነቱን ከናቅነው ግን እንክደዋለን፤ የራሳችንንም ጽድቅ አቁመን ወይ በሲዖል ወይ “በሰማያት” በከንቱ እንንከራተታለን።

እናም ትድኑ ዘንድ በኢየሱስ ጌትነት እመኑ፤ ለመዳንና የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የኢየሱስን ጌትነት በአፋችሁ መስክሩ፣ ደግሞም በልባችሁም እመኑ። በልባችን ሳናምን በአፋችን ብንመሰክር ሐሰተኞች ነን፤ በልባችን ያመንነውን በአፋችን ስንመሰክር ደግሞም ጌትነቱ በሕይወታችን ይታይ፤ ስሙ የቅድስናችንና የመዳናችን አዋጅ ምንጭ ይኹን፤ በኢየሱስ ጌትነት በኩል ማንም ምስጢራዊ አማኝ ወይም ክርስቲያን የለም! በአዋጅ እንናገራለን፤ ኢየሱስ ጌታ ነው! አሜን! My Blog link - https://abenezerteklu.blogspot.com/2023/03/blog-post_18.html
395 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 19:23:20 መዳናችን በክርስቶስ እንዲያው የተፈጸመ ቢኾንም፣ ፈጽሞ ግን ኀጢአት ለመሥራት አርነት አይሰጠንም።
280 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-17 06:42:39 "አቤቱ የዕውቀት ዓይኖችን ስጠን፤ ዘወትር አንተን ያዩ ዘንድ ጆሮዐችንም ያንተን ቃል ብቻ ይሰሙ ዘንድ።"

(ቅዳሴ እግዚዕ - የጌታ ቅዳሴ)
314 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 20:28:30
ካውንስሉ የተቋቋመበት አንዱ ዓላማ፣ እንዲህ ያሉ "ተግዳሮቶችን" ለመቅረፍ አልነበረ እንዴ?! የተሰቀለው ክርስቶስ ያስተማረን ክርስትና፣ አደገኛ የተግዳሮት ቅርቃር ውስጥ ለመግባቱ ምልክቶች ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ እያየሉ እየመጡ ይመስላል።

በመከራ እያለፉ ላሉ፣ የመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ይክበባቸው፤ አሜን።
438 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 07:04:05 የ200 ሚሊየን መኖሪያ ቤት፣ የ20 ሚሊየን መኪና፣ የ150 ሺህ ብር ሱፍ፣ የ50 ሺህ ጫማ፣ የግል ጀት... ለ"ጌታ አገልጋይ" ይገባዋል አ?!... ለእኔ ግን እንደዚህ ዐይነት ድኃ "አገልጋይ" የለም! ኢየሱስ የተቆረሰ ሕይወት ሰጪ እንጂ የኮተት ሰብሳቢ አልነበረም!
609 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 15:11:41 ከሚያበራ የንጋት ኮከብ ይልቅ፣ የኢየሱስ የተስፋ ቃል በየትኛውም ጨለማ ላይ ያበራል።
514 views"ውሰድና ብላት" (ራእ. 10፥9) በምሕረቱ የኾነውን የኾነ!, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ