Get Mystery Box with random crypto!

ከአገልግሎት ፊት ይቅርታ አይቀድምም ወይ? በጋሻው ደሳለኝና ባልንጀሮቹ “የእምነት እንቅስቃሴ” ወ | የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

ከአገልግሎት ፊት ይቅርታ አይቀድምም ወይ?

በጋሻው ደሳለኝና ባልንጀሮቹ “የእምነት እንቅስቃሴ” ወይም “ቃል እምነቴ” የኾነውን ትምህርት ሲያራምዱ አስቀድመው ከሰሙት መካከል አንዱ ነኝ። ትምህርቱን አምኖበት ስለ ማስተማሩና ስላለማስተማሩ ስጠይቀውም፣ “ቆፍጠን ብሎ አላዋቂ መኾኔን ጭምር ጠቅሶ፣ የእምነት እንቅስቃሴ አማኝነቱን በግልጥ ነግሮኝ” ነበር። ከዚያም በኋላ ይህን ስሑት ትምህርት ባስተማረባቸው ስፍራዎችና ያስተማራቸውን ትምህርቶች ለመስማማት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተጉዤ አጣርቻለሁ (ለምሳሌ፦ አዋሳ፣ መቂ፣ ዲላ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባና ሌሎችም ቦታዎች)።

በዚያ ትምህርቱ ብዙዎች ስተዋል፤ ትዳራቸውን አፍርሰዋል፤ ወደ ዓለማዊነት ፊታቸውንም የመለሱም ነበሩ። ለብዙዎችም የኬኔት ሔገንንና የኬኔት ኮፕላንድን መጽሐፎችን ከማንበብ ባለፈ ለሌሎችም ያሰራጭ ነበር፤ ከጃፒ (“ሐዋርያው” ብዙአየሁ ከሚባለው) ጋር በሽርክና በአንድነት ይሠራ ነበር።

እንግዲህ በጋሻው ደሳለኝ “ተመልሻለሁ” ካለ፣ ለእነዚህ ተግባሮቹ ኹሉ አስቀድሞ ይቅርታ መጠየቅና ለሳተበት ስህተቱና ላሳተበት መንገዱ ትክክል አለመኾኑን በግልጽ ሊናገር ይገባዋል። አልያ ግን “ታዋቂ አገልጋዮችን በማሰለፍ ብቻ” ስህተቱንና አሳችነቱን በበግ ለምድ አጊጦ ቢገለጥ፣ ለጊዜው እንጂ ከእውነተኛ አማኞች ዓይን ይሰወራል ተብሎ አይታመንም!

እናም ከአገልግሎተ በፊት ሊቀድም የሚገባው ላጠፉትና ለሠሩት ስህተት ንስሐና የበደሉትን በትክክል መካስ መኾኑን የሚጠይቅ መኾኑን ማስታወስ እንወዳለን! ይህ ባልኾነበት መንገድ ግን አገልግሎት ምንም ቢደምቅና ቢዋብ፣ በሰው እይታ “wow!” ቢያስብልም ከንቱ የከንቱ ከንቱ መኾኑን አስረግጠን እንናገራለን!