Get Mystery Box with random crypto!

“... እናንተ የምትንቁ፥ እዩ ተደነቁም ጥፉም... ” (ሐ. ሥ.13፥40-41) ከቅርብ ጊዜ ወዲ | የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ

“... እናንተ የምትንቁ፥ እዩ ተደነቁም ጥፉም... ” (ሐ. ሥ.13፥40-41)

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰባክያን "በፖለቲካና በዓለማዊ መድረኮች" ላይ ቀርበው፣ ዲስኩር መደስኮርን ተያይዘውታል። አሳዛኙ ነገር ደግሞ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ ግን የመጽሐፉን ቃል ሳይተረጉም የልባቸውን ዲስኩር ብቻ ደስኩረው ይወርዳሉ። አለመታደል!

ከሰሞኑ የአድዋ በአል መታሰቢያ ላይ፣ በአንድ ወቅት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርብ የነበረው ዶክተር ዮናስ ከላይ የጠቀስኩትን ጥቅስ ጠቅሶ ደሰኮረ።

ቃሉ የተነገረው በትንቢተ ዕንባቆም ምዕ. 1፥5 እና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ነው። ዕንባቆም ይህን ቃል የተናገረው፣ እግዚአብሔር ኀይል የተሞላበትን ሥራ ለመግለጥ በሚውል አገላለጥ ነው። ይሁዳ ስለ በደሏ ትቀጣለች፤ ለመቅጣት ደግሞ ጨካኝ ባቢሎናውያንን ያመጣል፤ ይህ ለዕንባቆም የማይታመን ቢኾንም፣ እግዚአብሔር ግን ቢነገራቸው ለማይሰሙ የማይቀረውን ፍርድ ይናገራል።

በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ደግሞ የተጠቀሰው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ለመሲሑ እንደ ተጠቀሰ በማውሳት ነው። ስለዚህም የኢየሩሳሌም ሰዎች በዕንባቆም የተነገረው ትንቢት፣ በእነርሱ እንዳይፈጸም ቅዱስ ጳውሎስ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ የተናገረው የመደምደሚያ ቃል ነው። የመሲሑን እውነት ቢንቁና ባይቀበሉ፣ ከይሁዳ በከፋ ኹኔታ የሚገጥማቸው አደገኛ ጠንቅ ነው።

ቃሉ እንዲህ ሊነገር ሲገባው፣ ዶክተሩ ግን ይህ ችላ ማለቱ ያሳዝናል። እናም ዲስኩርነትና የቃለ እግዚአብሔር ቃል ጠቀሳ ቢቀር ምናለ?! "ሰባኪዎች" ዲስኩር ባይደሰኩሩስ? የደጋፊ ጩኸትና ፉጨት ጥማት ካለብን ከቃሉ ሳንጠቅስ ሌላ "መድረኩን የሚመጥን ተራ ዲስኩር" ማቅረብ አይቻልም?

በቃለ እግዚአብሔር አትዘብቱ፤ ያውም ለመሲሑ በተነገረው ቃል ላይ አትቀማጠሉ!

ይልቁን፤ በመሲሑ ቃል ላይ፣ እንደ ቧልት የምትደሰኩሩ፣ እዩ ተደነቁ ጥፉ!