Get Mystery Box with random crypto!

DA-SUPPORT

የቴሌግራም ቻናል አርማ dasupport01 — DA-SUPPORT D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dasupport01 — DA-SUPPORT
የሰርጥ አድራሻ: @dasupport01
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.82K
የሰርጥ መግለጫ

Educational Channel

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 19:14:46 24/12/2014ዓም

ለተከበራችሁ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች

ዳይመንድ አካዳሚ የወላጆች ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን፥
አጀንዳዎቹም

የትምህርት ቤት ዓመታዊ እቅድ
የወላጆች ኃላፊነት ስልጠና
የትምህርት ቤት ድርሻ
አዲሱ ስርዓተ ትምህርት
የክፍል ወተመህ ተወካይ ምርጫ እና
የልጆቻቸውን የትምህርት ግብ መጣል ሲሆኑ

ወላጆች በልጅዎ ክፍል መሰረት ከታች በተቀመጠው የውይይት መርሀ ግብር መሰረት እንድትሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

1) የአንደኛና ሁለተኛ ክፍል ወላጆች በ25/12/2014 ከ 3፡00 – 5፡00

2) የሶስተኛና አራተኛ ክፍል ወላጆች በ25/12/2014 ከ7፡00 – 9፡00

3)የአምስተኛና ስድስተኛ ክፍል ወላጆች በ26/12/2014 ከ 3፡00 – 5፡00

4)የሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል ወላጆች በ26/12/2014 ከ7፡00 – 9፡00

5)የዘጠንኛና አስረኛ ክፍል ክፍል ወላጆች በ27/12/2014 ከ 3፡00 – 5፡00

6)የአስራ አንደኛና አስራ ሁለተኛ ክፍል በ27/12/2014 ከ7፡00 – 9፡00

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
898 views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:48:20 24/12/2014ዓም
ለተከበራችሁ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች

የ7ኛ ክፍል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና የሚከናወነው ሐሙስ፣ ነሃሴ 26 እና አርብ፣ ነሃሴ 27፣ 2014 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በቤት እንዲያጠኑ ለምታደርጉት እገዛ በእጅጉ አክብሮታችንን እንገልፃለን፡፡

ዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
985 viewsedited  08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 15:44:46 22/12/2014 ዓም

ለመጀመሪያ ዙር የSAT ሰልጣኞች
እንኳን ደስ አላችሁ!!!

በዳይመንድ አካዳሚ ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የSAT ስልጠና አርብ እለት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ በት/ቤቱ ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
በቀጣይ ዋናውን ፈተና ለሚወስዱ ሰልጣኞቻችን እና ተማሪዎቻችን መልካም ምኞታችንን እየገለፅን ይህንን ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ለሚያመጡ ሰልጣኞቻችን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ሽልማት ቃል የተገባላቸው ሲሆን፤ ይህ ሽልማት በቀጣይም ስልጠናውን ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ከት/ቤታችንና ከሌሎች ት/ቤቶች መጥታችሁ ስልጠናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች በፕሮግራሙ ላይ ለሰጣችሁን ቀና አስተያየት እናመሰግናለን።

ሰልጣኝ ተማሪዎች የሰጡትን አስተያየት ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
https://t.me/sat_diam

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
1.2K viewsedited  12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:40:42 ቀን 19/12/2014ዓም

ለተከበራችሁ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች

የSAT የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች፤ነገ፥ ነሃሴ 20 የፈተናችሁን ውጤት የምትቀበሉበትና የእውቅና ፕሮግራም የሚካሄድ በመሆኑ ጠዋት3፡00 ሰዓት ላይ ዳይመንድ አካዳሚ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
936 views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:02:37 ቀን 19/12/2014ዓም

ለተከበራቹ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች

የሁለተኛው ዙር የSAT ስልጠና ምዝገባ መጀመራችን ይታወቃል በመሆኑም ስልጠናው ሰኞ፣ ነሃሴ 23፣ 2014ዓም የሚጀምር ሲሆን ከነሃሴ እስከ መስከረም ፤ በሳምንት ለ4 ቀናት ከ1ኛው ዙር ጋር በተመሳሳይ ለ54 ሰዓታት የሚሰጥ ይሆናል።
ሁለተኛውን ዙር ስልጠና ለየት የሚያደርገው ከSAT ስልጠና በተጨማሪ ተማሪዎች የ"College Counseling" የሚያገኙበትና በቀጣይ የውጭ ትምህርት እድል ለማግኘት ከአሁኑ ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች ምክር የሚያገኙበትና የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች የሚያደርጉበት በመሆኑ ለተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ ስልጠና ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ +251 91 182 3371
                         +251 93 032 9537

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
1.0K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 21:34:58 ቀን 17/12/2014ዓም

ለተከበራቹ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች

በትምህርት ቤታችን ሲሰጥ የነበረው የSAT ስልጠና በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ፥ ረቡዕ ነሃሴ 18፥ 2014ዓም ማጠቃለያ ፈተና እንደሚሰጥ እያስታወስን ልጆችዎ በቤት ለሚያስፈልጋቸው እገዛ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ እንጠይቃለን።

ማስታወሻ፡
ተፈታኝ ተማሪዎች ነገ ለፈተና ስትመጡ ካልኩሌተር፥ እርሳስና ላጲስ ይዛችሁ መምጣት እንዳትረሱ።

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
1.2K viewsedited  18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 16:37:56 11 /12/2014
ለተከበራቹ የዳይመንድ አካዳሚ ወላጆች/አሳዳጊዎች

ሁለተኛው ዙር የSAT Tutorial Program ምዝገባ ተጀምሯል!
ስልጠናው የሚሠጥበት ጊዜ ከ August 29 - September 15, 2022 ይሆናል፡፡ ይህ ፕሮግራም በተለይ October እና December ለሚፈተኑ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ ልክ እንደ አንደኛው ዙር ሁሉ አሁንም ውስን ተማሪዎችን ብቻ ተቀብለን የምናሰለጥን በመሆኑ ቀድመው ልጅዎን ያስመዝግቡ፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ +251 91 182 3371
+251 93 032 9537

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
2.3K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 21:53:25 ለዳይመንድ አካዳሚ የ2015 የ8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች

ጉዳዩ: የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ማዘጋጃ የክረምት ትምህርትን ይመለከታል

እንደሚታወቀው ትምህርት ቤታችን የ2015 የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች የላቀ የትምህርት ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከነሃሴ 02/2014ዓ.ም ጀምሮ የማዘጋጃ ትምህርቱን በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ ወላጆች የሚሰጠው ትምህርት ለሁሉም ተማሪዎች መሆን/ አለመሆኑን ለመጠየቅ ቢሮ እየደወላችሁ በመሆኑ ፤ የማዘጋጃ ፕሮግራሙ ለሁሉም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ መሆኑን እንየገለፅን ማስመዝገብ ፈልጋችሁ የነበራችሁ ወላጆች፤ ፕሮግራሙ ለተማሪዎቹ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ብዙ ሳያመልጣቸው በጊዜ እንድታስመዘግቧቸው እናስታውቃለን።

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
2.9K views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:41:00 ቀን 03/12/2014 ዓም

ለክረምት የ8ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች

የክረምት የ8ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ትምህርት ሰኞ፣ ነሃሴ 2፣ 2014 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል፤ ስለሆነም ተማሪዎች በየቀኑ ቤታቸው ሆነው የሚሰሯቸው የተለያዩ መልመጃዎች የሚሰጣቸው በመሆኑ ወላጆች ልጆቻችሁ እነዚህን መልመጃዎች በቤት በቂ የሆነ ጊዜ ሰጥተው እነዲሰሯቸው የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በትህትና እናሳስባለን፡፡

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
2.6K viewsedited  17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 12:50:54 ቀን 28/11/2014 ዓም

ለ 8ኛ ክፍል የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ለመማር የተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ሰኞ፣ ነሐሴ ፣2014 ዓም የሚጀምር መሆኑ ይታወቃል፤ በመሆኑም ተማሪዎች ዘወትር ጠዋት 2፡00 ሰዓት ላይ ት/ቤት መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ትምህርቱ በግማሽ ቀን መርሐግብር የሚሰጥ ስለሚሆን ልጆዎን 7፡00 ሰዓት ላይ መጥተው መውሰድ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ በ2014 የትምህርት ዘመን ሲማሩባቸው የነበሩትን ደብተሮችና መፃህፍት፤ በተጨማሪም አሁን ለሚማሩት ት/ት ማስታወሻ መያዣ ደብተር ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል።
ተማሪዎች ተገቢ የሆነ አለባበስን ተከትለው መልበስ ይኖርባቸዋል።
የክፍያ የባንክ ስሊፕ ያልላካችሁልን ወላጆች፤ ሰኞ በልጅዎ በኩል ይላኩላን።

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር
2.9K views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ