Get Mystery Box with random crypto!

22/12/2014 ዓም ለመጀመሪያ ዙር የSAT ሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ!!! በዳይመንድ አ | DA-SUPPORT

22/12/2014 ዓም

ለመጀመሪያ ዙር የSAT ሰልጣኞች
እንኳን ደስ አላችሁ!!!

በዳይመንድ አካዳሚ ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የSAT ስልጠና አርብ እለት በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ በት/ቤቱ ተፈትነው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።
በቀጣይ ዋናውን ፈተና ለሚወስዱ ሰልጣኞቻችን እና ተማሪዎቻችን መልካም ምኞታችንን እየገለፅን ይህንን ፈተና ወስደው ከፍተኛ ውጤት ለሚያመጡ ሰልጣኞቻችን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ሽልማት ቃል የተገባላቸው ሲሆን፤ ይህ ሽልማት በቀጣይም ስልጠናውን ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የሚሰጥ ይሆናል።

ከት/ቤታችንና ከሌሎች ት/ቤቶች መጥታችሁ ስልጠናውን የወሰዳችሁ ተማሪዎች በፕሮግራሙ ላይ ለሰጣችሁን ቀና አስተያየት እናመሰግናለን።

ሰልጣኝ ተማሪዎች የሰጡትን አስተያየት ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
https://t.me/sat_diam

የዳይመንድ አካዳሚ አስተዳደር