Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-11 08:16:18
#የማለዳ_ቃል

“እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው።”
-ዘጸአት 14፥14

መልካም ቀን


#ለእኔ_ሕይወት_ክርስቶስ_ነው

@CHRIST_TUBE
@CHRIST_TUBE
1.5K viewsAna, edited  05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 22:01:35 Live stream finished (54 minutes)
19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:11:15 https://t.me/Christ_Tube?livestream=973972c137007650e1
672 viewsAna, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:10:28 https://t.me/Christ_Tube?livestream=973972c137007650e1
670 viewsAna, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:10:28 የፀሎት ፕሮግራም ለመካፈል
643 viewsAna, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:06:38 Live stream started
18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:06:23 Live stream የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሯል
CHRIST_TUBE
➥@CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ
647 viewsAna, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 21:00:33 ቀን ሶስት (3)
የፀሎት መርሃ ግብር

1, ስለጠፉ በጎች ልመናና ምልጃ

“ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።”
— ዮሐንስ 21፥15



2,ሰለ ምድራችን

“እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ።”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1-2

3, መልካም መሪዎችና እረኞች እንዲነሱ መፀለይ

1ኛ ጢሞ 2÷1-2

ማታ 3:00 pm መንፈሳችሁን ለፀሎት አዘጋጁ

@CHRIST_TUBE
➥@CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ
622 viewsAna, edited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-10 20:00:05 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=አንድ
ክፍል=43
ሳባ ካሳሁን

በቁጣ ድምፅ "ቢኒያም ሰለሞን ነኝ የት ናችሁ?" አለው ቢኒ በጣም ከመደንገጡ የተነሳ ዐይኖቹና የፊቱ ቅላት ከምንጊዜውም ተለይቶ ደም መሰለ እጆቹ ከኪሱ ወጥተው እርስበርሳቸው ተፋተጉ ሁኔታውን ያስተዋለችው ሊዱ ግራ በመጋባት ድምፅ ሳታወጣ "ቢኒ ምንድነው? ማነው?" ብላ ይዞ የቀረውን ስልክ አዙራ ለማየት ሞከረች ልክ እንዳየነው የደወለው አባዬ መሆኑን ስናውቅ ድመት እንዳየች አይጥ የምንገባበት ጠፋን ከቢኒ በባሰ ሁኔታ ተርበደበድን። ተዐምርን መስራት የለመዱት ሊያና ኬብሮን ነገሩን ሲያውቁ በሙሉ መረጋጋት ተጠግተውን ኬብሮን ለቢኒ በጆሮው "እኛ ቤት ነን በላቸው" አለው ነገር ግን ቢኒ መዋሸትን አልቀበል አለ ያለን ምርጫ ግን ይሄ ብቻ ነበር ራሱን የቻለ ሌላ ትግል ውስጥ ገባን
ሁለት ምርጫ
እውነት የማትወጣ ይመስል ውሸትና ማታለልን ማንገስ ወይም
ያለንበትን ቦታ በመረዳት አዕምሯችንን አንቅተን በማስተዋል ተረጋግተን እውነቱን በግልፅ አስረድቶ ቤተሰቦቻችንንና ከሁሉ በላይ ጌታችንን ማስቀደም። በሰዐቱ ምርጫችን ወዲያው ወደ አንዱ ተጣደፈ ይኸውም ውሸቱ ነበር ልክ የለመድነው ይመስል ቢኒን አረጋግተን ስልኩን መልሶ ምንም እንዳልተሰማው "ሄሎ. .ሄሎ አይሰማም??" ብሎ የቅንብር ቃላትን ማውጣት ጀመረ አባዬም በሀያል ድምፅ "ይሰማል ቢኒያም የት ናችሁ?" አለው ምርጫውን የመረጠው ቢኒ ምንም ሳይጠፋበት "አሁን ከቸርች ወጥተን እኛ ቤት ሆነን ነውኮ ይቅርታ አባ ቆየን አይደል?" አለው በመሀል የሶሲና የእማ ጫጫታ በቴሌቭዥኑ የተከፈተ ልብ አረስራሽ መዝሙር አልፎ ይሰማል አባዬም ከልቡ አምኖን ከቁጣ ወጥቶ በፈገግታ ድምፅ "ምነው ልጄ ምን ነካችሁ? ዛሬ ሶሲ ፈተና እንደምትጨርስ እያወቃችሁ? በሉ ቶሎ ኑ በቃ ግን ቅጣት ይጠብቃችኋል" አለው ሁላችንም ለዚህ መሆኑን ስናውቅ የመገላገልና ተረፍን አመለጥን ዋው!! አባዬንም ሳናስፎግር በጥሩ መልክ አታለልነው ብለን በረጅሙ ተነፈስን ራሳችንን እንደ አንደኛና ብቃት እንዳለን ጀግና አየነው።
በዙሪያችን የከበቡን የሰሞኑ ውሏችን የሆኑት ልጆች እንደተሳካልን ሲያዩ በደስታ ተሞሉ እኛም ወደነበርንበት ፈገግታ ተመለስን ወዲያው ግን ሁሉም በአንድ ድምፅ በተመሳሳይ ሁኔታ ልብ በሚነካ አስተያየት እያዩን ከጆሮ በማይጠፋ ስስ ድምፅ "በቃ ጓደኞች ሂዱ እንዳናስቆጣችሁ ይቅርታ በእኛ ምክንያት ነው የተጨናነቃችሁት" ብለው አንገታቸውን አቀረቀሩ እንዲህ ሲሉን ልባችን ተንሰፈሰፈ ፍቅራቸውና ትህትናቸው አፋችንን እስክንይዝ አስደነቀን ቃላት አጥሮን እንደቆምን ሊዱ ዬ አጠገባቸው በርከክ ብላ "ህይወታችን ላይ እናንተን የመሰሉ ጓደኞች ስላሉን እድለኛ ነን በጣም እንወዳችኋለን" ብላ እጇን ዘረጋችላቸው ሁሉም እየተነሱ አቀፏት እኛም በፈገግታ እያየናቸው ቢኒ "በቃ ጓደኞች እንገናኛለን" ብሏቸው ከኬብሮንና ከሊያ ጋር ለመውጣት ተነሳን በቤቱ የነበሩት ሁሉም ልጆች ልክ ስንገባ እንዳደረጉት ከፍራሻቸው ተነስተው በፉጨትና በፍቅር ቃላት አጅበው ሸኙን እኛም ልባችንን "ሂድ ከዚህ!!" ብለን አዕምሯችን በፈጠረልን ፍፁም ደስታ ከልባችን እየተሳሳቅን ጉዟችንን ወደ ቤት አደረግን እነ ሊያን ቀን በቀን አብረናቸው በዋልን ቁጥር ሁለነገራቸው ሳበን አንዳንዴ ቆም ብዬ ሳስበው የመጀመሪያ ቀን ምን ነክቶኝ ነው የደበሩኝ ኸረ ምንስ ሆኜ ነው እንደዛ የተኮሳተርኩባቸው ብዬ እገረማለሁ በመንገዳችን ላይ እንደተለመደው በግልፅ እያወሩን ስንሳሳቅ ሳይታወቀን ቤት ደረስን ሊያ በስሱ የሊዱን እጅ እያሻሸቻት "በቃ ግቡ እንዳናስመሻችሁ" አለችን እኛም ተስማምተን ከልባችን አቅፈናቸው ማታ እንደሚደውሉልን ነግረውን በፍቅር ተለያየን። ቤት ስንገባ ገና ከውጪ ድምፃቸው ይሰማል ሁሉም እየተሳሳቁ ነው ከመዝሙሩ ድምፅ ጋር አብረው እየዘመሩ ገርበብ ብሎ በተከፈተው የፊት በር ከወዲያ ወዲያ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ ሊዱና ናሆሜ እየሮጡ ገቡ እኔና ቢኒም ብቻችንን ስንቀር ደንግጠን እየተሽቀዳደምን ገባን ስንገባ ቤቱ ሞቅ ብሎ ድግስ ያለበት ቤት መስሏል አባዬ እማን እያገዛት በእጆቹ ሳህን እሷ ደግም ጀበና የሚቀመጥበትን ማውረጃ ይዘው መጡ ሁለቱም ልክ እንዳዩን እንዳላስተዋሉን ነገር "ሰሌ አስቀምጠው" "እሺ አዜቤ" እየተባባሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ያወራሉ እኛም ተያይተን ሳቃችን መጣ ቅታችን እንደሆነ አምነን ሁላችንም ለመለመን ቆርጠን ተነሳን ቢኒ ሮጦ እማ ጋር ሄደ ቁመት በልጧት አቀፍ አደረጋትና "እማ አይለመደንም እኮ ሁለተኛ እ" እያለ ልቧን ስለሚያውቅ ሳማት ናሆሜም አባን በጣም ስለሚቀርበው ዝም ይለኛል ብሎ ሊያረሳሳው እየሮጠ ሲሄድ አባዬ በጣም በሚያስቅ አስተያየትና ድምፅ "ሂድ አንተ!" ሲለው እማ ሳቋ አምልጧት ሳቀች እኔና ሊዱ ልክ እንደ ፊልም ማየታችንን ልናቆም አልቻልንም ቢኒ በሳቅ ብዛት እያለቀሰ "ውይ እማይዬ እንዲህ ስትስቂ ነውኮ ደስ የምትይው" እያለ ጭምቅ አድርጎ አቀፋት የቀረው አባዬ ነበር ሁላችንም ግራና ቀኝ ከበን ብዙ ስንለፈልፍበት ለመገላገል ይመስል "እሺ እሺ በቃ አሁን ኑ አግዙኝ" አለን ሶሲም ልክ እንደነ እማ ፊቷን ጥላው መጥታ እነ ናሆሜን ስታያቸው ኩርፊያዋን ረስታው ተጠመጠመችባቸው መቅሰስ ቀራርቦ ነበር ቤቱ በፍቅር ደስታ ተሞልቷል ሁላችንም እየተነሳን ስንጎራረስ ናሆሜና ሊዱ ሲጨቃጨቁ እኛ ስንስቅ ቢኒ ሲገላግላቸው ጨዋታችን ቀጠለ ሁላችንም ስለ ውሏችን እያወራን በስተመጨረሻ ሶሲ ጋር ደረሰ ውሎዋን እንዲህ ብላ ጀመረችልን "እሺ እንግዲህ ትምህርት ቤት ከማሂ ጋር ሄድን ፈተናዬን ፀልዬ ጀመርኩ በሰላም አለቀ ሰዐት ገና ስለነበር ጌታን ለማመስገን ወደ ቸርች ሄድኩ የሚገርመው ወጣቶች ፕሮግራም ነበር ከዛ. . ." ስትል ሁላችንም ልባችን ትርትር አለ በድንጋጤ አይናችን ላይ ታች ግራ ቀኝ አማተረ ናሆሜ ተርበትብቶ ቆንጠጥ አደረገኝ የፈራነው አልቀረም አባዬ ያን ከመሰለ ሳቅ ወደ ሚያስፈረጥጥ ኩስታሬው ተመልሶ "ቆይ ቆይ እናንተ ቸርች ሄደናል ብላችሁኝ አልነበር?. . .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
746 views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:58:37 Live stream finished (1 hour)
19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ