Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-06 19:12:48 #Spiritual_Speech
❝ትላንትና በጣም አስቸጋሪ የምትለውን ፈተና አልፈህ ዛሬ ሌላ ፈተና ቢመጣ አትደነቅ ከባለፈው ጥንካሬ በይበልጥ ሊጨምርልህና በችግርህ ጊዜ ይበልጥ እግዚአብሔርን እንድትፈልግ ያበረታሀልና ፈፅሞ ፈተናን አትጥላው! ❝

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥@CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.9K viewsMeron, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 07:11:49
#የማለዳ_ቃል

" ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤"
-መጽሐፈ ምሳሌ 23: 17

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.0K viewsMeron, edited  04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 08:58:56
#የማለዳ_ቃል

" በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።"
-ወደ ሮሜ ሰዎች 5: 5

" And hope maketh not ashamed; because the love of God is shed abroad in our hearts by the Holy Ghost which is given unto us."
-Romans 5: 5

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.9K viewsMeron, 05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 20:01:58 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
         ምዕራፍ=አንድ
          ክፍል=34
     ሳባ ካሳሁን

እነ ሊያን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ተዋወኩበት ወደዛ ንቄ ወደተውኩት አስጠሊታ ብዬ ወዳወራሁት ቦታ መሄድ ጀመርን ። ሁላችንንም ሊያ እና ኬብሮን በወሬ ወጥረውናል ሳይታወቀንም ቢሆን ደረስን ልክ የመግቢያው በር ጋር ስንደርስ ወደ አዕምሮዬ በአንድ እሁድ ቀን አገልግሎት እያለብን ማህሌት ሶሲን ካልገባን ብላት አስገብታን እነ ሊያን የተዋወኩበት ቅፅበት ድቅን አለብኝ በጣም እየተርበተበትኩ "እንዴ ምን እያደረኩ ነው መግባትማ የለብኝም!" ብዬ ከአጠገባቸው ራቅ አልኩ ነገር ግን ሊያ በዚህ ሰዐት ምን እየሆነች እንደሆን ሊገባኝ አልቻለም የቀራት ነገር ቢኖር እኛን  ወርውሮ መክተት ብቻ ነው "እንዴ ሜሪ ነይ እንጂ ደሞ መኪና አትዳፈሪ እኔ ዛሬ የምሮጥበት አቅም የለኝም በደስታ ብዛት ጦዣለሁ!!" ብላ ሀይለኛ ግን ደስ የሚል ሳቅ ሳቀች ልክ እንደዚህ ስትለኝ ደግሞ ከራሴ ጋር ሳወራ የነበረውን ሀሳብ ወደ ጎን ጥዬ ትኩረቴ አዲሱ የህይወቴ ምዕራፍ ሊሆን ወዳለው ከሞት ወደ ታደገችኝና በውለታዋ የታሰርኩባት ወደሊያ ሆነ እንደምንም የውሸት ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ የሊዱን እጅ ያዝ አደረኩት ኬብሮኔም እነ ቢኒን ገፋ እያደረጋቸው "በሉ በቃ እንግባ" አለን ተያይዘው ሁሉም ገቡ እኔና ሊዱ በሯ ላይ ቆም ብለን ቀረን ሊዱ ዬ በውብ እና ኳስ በሚመስሉ አይኖቿ ቀና ብላ እያየችኝ እርምጃዬን ትጠባበቃለች ለምን እንደሆን ባላውቅም በቃል ከምገልፀው በላይ ውስጤ ተረብሾ ነበር አይኔን በስሱ ጨፈን አደረኩና ራሴን በቀስታ ለማዳመጥ ሞከርኩ ግን እነ ናሆሜ "ሜሪ ሜሪ" እያሉ ፋታ ነሱኝ ቀስ ብዬ ልክ  የሆነ ነገር ይወጋኝ ይመስል በስሱ የፊት እግሬን ወደ ውስጥ ጣል አደረኩት ከዚያም ለመረጋጋት እየሞከርኩ አይኔን ገለጥኩ ስገልጥ ጭራሽ ያልጠበኩት ነገር ነበር እዛ ያሉት ልጆች በሙሉ ስርዐት ያለው አለባበስ ስርዐት ያለው አቀማመጥ በቃ ሀኔታው ምንም የበፊቱን አይመስልም እኔም ከግራ ወደ ቀኝ ከላይ ታች በአይኖቼ እያማተርኩ በቦታው ሰላም ተሰማኝ ይህን ጊዜ ለቡቻዬ እጄን ዘረጋሁላት እና ወደዚህ ሰላም ወደመሰለኝ አለም አስገባኋት! እሷም በአንድ እጇ የሸሚዜን ጫፍ  በሌላኛው ደሞ እጄን ጥብቅ አድርጋ ይዛኝ ግራ ቀኝ እንደኔ አማተረች ስታያቸው ግን ቀለል እያላት መጣ. እነ ቢኒም ወደተቀመጡበት ቦታ ሄደን ከእነሱ ጋር ልንቀመጥ ስንል ሊያ እሷ ወዳለችበት መቀመጫ ያለውን ቦታ አሳይታን "ኸረረ!! የምን መጣበብ ነው ኑ እዚህ ጋር ሰፊ ቦታ እያለ ምን እዛ አስኬዳችሁ!?" ብላ ጢማችንን አበረረችው እኔና ሊዱም ድንግጥ ብለን እንዳለችን ከጎኗ ተቀመጥን የሚገርመው በቢኒና ናሆሜ መሀል ኬብሮን ቁጭ ብሎ ነበር። ሊያ ቁም ነገር የማይባል ግን በጣም ደስስ የሚል ወሬ እያወራችልን እኛም እየሰማናት፣ ኬብሮኔም ቀበል ብሎ ስለ ታሪካቸው ሲነግረን እኛም ስንስቅ
ትንሽ ስንቆይ አካባቢውን እየተላመድነው ፈገግ ማለት እየጀመርን ከማዳመጥ አልፈን ስናወራ ከማውራት አልፈን ስንሳሳቅ፣ እዛ ያሉት ሰዎች ስርዐታቸው ደስ ሲለን፣ አንዳንዶቹ ሰላምታቸው ሲማርከን ሳይታወቀን ልክ እንደ ቤታችን ፈታ ብለን ቁጭ አልን በዚያ ሁሉ መሀል ሊያ ከመካከላችን "መጣሁ"ብላ ተነሳች አሻግሬ በአይኔ ለመከታተል ስሞክር ውስጥ ብዙ ሆነው ከተቀመጡት አንዱን ተጠግታ አወራችው ከዚያም አጠገቡ ካለችው ሴት ጋር ልክ የሆነ ነገር አስበን ስንስማማ እጅ እና እጃችንን "እስቲ ግጨው/ኸረ ግቢለት" እንደምንባባለው ልክ እንደዚያ አድርገው በሙሉ ፈገግታ ከእነሱ ተለይታ ወደ አንዷ አስተናጋጅ ሄደች እኔም እይታዬን ለመቀጠል ስታገል ኬብሮን "እሽሽሽ ሜሪ ሄድሽ እኮ ፒስ ነው ግን?" ብሎ አሳፈረኝ እኔም ድንግጥ ብዬ "አዎ ነው" አልኩት እነ ቢኒ ዝም ብለው ያዩኛል ግን ሊያወሩኝ አልቻሉም አስባው ይሁን ሳታስበው ሊያ ነጣጥላናለች ብዙም ሳትቆይ መጣች "ይቅርታ ጥያችሁ ጠፋሁ" ብላ ደስ በሚለው ፈገግታዋ ፈገግ አለች እኛም ቀለል አድርገን ችግር እንደሌለው ነገርናት ትንሽ እንደተጫወትን አስተናጋጇ ወደኛ መጥታ የምንፈልገውን ነገር ጠየቀችን ቢኒ ቶሎ ብሎ "እ ለኔ ለስላሳ ነገር ይሁንልኝ ለሜሪና ለቡቹ. ." ሲል ሊያ አላስጨረሰችውም "እንዴ!!! የምን ሜሪና ቡቹ ነው እነሱ ለራሳቸው አያዙም? ህፃን አይደሉ ምን ነካህ!?" ብላ በሀይል ተቆጣችው በቢኒ አስተናጋጇ ሳትቀር ሳቀችበት እሱም በእፍረት ዝም አለ ናሆሜ ለማረሳሳት ቶሎ ብሎ "ይቅርታ እማ አስቆምንሽ በቃ አራት ለስላሳ አምጪልን" ብሎ ነገሩን ደመደመው ኬብሮንም ሳቅ እያለ "በቃ ለኛም ለስላሳ ይሁን" ብሎ ሸኛት በሊያ አስተባባሪነት ጨዋታው እየተጋጋለ እዛ የተሰበሰቡት ወጣቶች ድምፃቸው ወጣ እያለ እኛም በሁኔታው እየተዋጥን ከትንሽዬ ፈገግታ ሞቅ ወዳለ ሁካታ ገባን ወዲያውም በዘመኑ በጣም ወጣ ያለ የተባለና በጭፈራ ቤቶች የሚከፈት ዘፈን ተከፈተ እኛም ብዙም ለሁኔታው ትኩረት ሳንሰጥ የያዝነውን ለስላሳ እየተጎነጨን ቆየን የቡድናችን መሪ መካሪያችን የሆነው ቢኒ በእጁ ላይ ያለውን ሰዐት እያየ "በቃ እንሂድ" ብሎ እንድንነሳ ነገረን ኬብሮን ግን ኮስተር ብሎ "እንዴ ሰዐቱ እኮ ገና ነው በእናትህ ቢኒ ሙዳችንን አትበጥብጠው አትርሳው እንጂ ዛሬ የኛ ቀን ነው!!" አለው ፋታ አልሰጡትም ሊያም ቀልቀል ብላ "አዎ ኬብሮኔ ልክ ነው እስቲ አስቡት ሺ አመት እኮ አንኖርም እስቲ ፏፏፏፏፏ ለማለት ሞክር ሀሳብህን ሁሉ ጣል አድርገህ Enjoy አድርግ" ብላ በተከፈተው ዘፈን የሚያስቅ አጨፋፈር እንደመጨፈር እያለች ሁላችንንም ፈታ አደረገችን የቢኒን ሀሳብ ውድቅ አድርገን እንዳለችው ሰፋ ብለን ሀሳባችንን ጥለን ተቀመጥን ቢኒ እንዳይደብረው በምልክት "ትንሽ ቆይተን እንወጣለን" አልኩት ናሆሜንም እንደዛው እሱ እኔ ባልለውም ተመችቶታል የመውጣት ሀሳብ አልነበረውም ተያይተን በሁኔታው ፈገግ ብዬበት ዞር ስል
ከፊት ለፊታችን ተሰባስበው የነበሩት ሊያ ሄዳ ያዋራቻቸው ልጆች በእጆቻቸው እኛ የምንጠጣውን የለስላሳ አይነት ይዘው ወደኛ መጡ ከመሀከላቸው ገዘፍ የሚለው አንዱ በጨዋ መልክ "ሰላም እንዴት ናችሁ እናንተን መቀላቀል ይቻላል?" አለን ሁላችንም እርስ በእርሳችን እየተያየን እያለ ሊያ "ኸረ አዎ ይቻላል!!" ብላ የኛን ሀሳብ ሳትጠይቅ ፈቀደችላቸው እነሱም ወንበሮች ጨምረው ዙሪችንን ከበቡን እኛ በመሀል ቤት ጦጣ ሆነን ቀረን ግን ከሚባለው በላይ ጨዋታቸው ይስብ ነበር ትንሽ እየቆየን ሲያወሩ ደስ ሲሉን በወሬያቸው ስንማረክ ከነሱ የባሰ እኛ ቀወጥነው እዚህ ግባ የማይባል ወሬ ግን ደሞ በደስታ እየተጨዋወትን የዘፈኑ ድምፅ እየተጨመረ የከበቡን ልጆች እውነተኛ ስሜታቸው እየወጣ ቤቱ እየተቀየረ እየተቀየረ መጣ ሁሉም በሙሉ ድምፅ ወደኛ እያዩ "ጋይስ ለምን የሚጠጣ ነገር አይመጣም??" አሉን ሊዱም የያዘችውን ለስላሳ ወጣ አድርጋ ለሁሉም እያሳየቻቸው "ይኸው ይዘናል" አለቻቸው የዚህን ቀን በሊዱ ላይ የሳቁት ሳቅ ከአዕምሮ የሚጠፋ አልነበረም ሁሉም ከትትትት ብለው ሳቁባት እና አንድ ደስ የምትል ልጅ በሚያምር ድምፅ "ኸረ የኔ ቆንጆ ኪኪኪኪ አሳቅሽን እኮ እኔ እንደዛሬ ስቄ አላውቅም የሚጠጣ ያልነው እኮ Likeአልኮል  ነገር ለማለት ነው" አለቻት ይህን ጊዜ ሁላችንም ልባችን ለሁለት ተከፈለ. .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.9K views@Maranata, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 07:05:30
#የማለዳ_ቃል

" ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።"
-ዮሐንስ ወንጌል 14: 27

በተጨነቃችሁበት ሁሉ የእግዚአብሔር ሰላም ይፍሰስላችሁ
መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.9K viewsMeron, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 20:02:14 የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

የቀደሙ ክፍሎች ቻናሉ ውስጥ አሉ

ክፍል-3
የሲዖል የግራ እግር

መጀመርያ ያየኋት ትልቅ ሴት ከኋላ ታየችኝ አሁን ሳያት ያስተዋልኩት ግን አንድ እግር ብቻ እንዳላት ነበር። በአጥንቶቿ ቀዳዳዎች ይታዩኛል። "...ምንድነው ጌታ ሆይ ?" ብዬ ጠየቅኩ። ጌታም " በምድር ሳለች ካንሰር በሚባለው በሽታ በጣም ታማሚ ነበረች። ህይወቷን ለማዳን ቀዶ ጥገና ተደርጎላት ነበር። ከተደረገላት በኋላ ግን ለአመታት መራር ሴት ሆና አረጀች። ብዙ የኔ ሰዎች ሊፀልዩላት ይመጡ ነበር። ትፈወሻለሽ ሲሏት " እግዚአብሔር ራሱ ነው ይህንን ያደረገብኝ " ብላ ታባርራቸውና ወንጌሌንም ታጥላላ ነበር።ንስሀ አልገባችም ነበር። ቀድሞ ታውቀኝ ነበር ኋላ ላይ ግን ጠላችኝ። እግዚአብሔር አያስፈልገኝም ፈውሱንም አልፈልግም ትል ነበር። ስለምናት ጀርባዋን ሰጠችኝ። አልፈልግህም አለችኝ። መንፈሴ ወደኔ እንድትመጣ አጥብቆ ለመናት አትሰማም ነበር። ኋላ ሞተችና ወደዚህ ስፍራ መጣች።
ሴትየዋን ጥቂት ስንጠጋት " ጌታሆይ አሁንስ ይቅር አትለኝም? በምድር ሳለሁ ንስሀ ባለመግባቴ እባክህ ጌታ ይቅርታ አድርግልኝ።" እያለች አለቀሰች። " ምናለ ድሮ ንስሀ ገብቼ ቢሆን ኖሮ። አሁንማ በጣም ረፈደብኝ። ግን ጌታዬ ከዚ አውጣኝ እባክህ ካወጣኸኝ አገለግልሀለሁ ጥሩ እሆናለሁ......የእስካሁኑ ስቃዬ አይበቃም ጌታ ሆይ እባክህ"
".....ወይኔ ለምን እስኪረፍድብኝ ድረስ ቆየሁኝ ለምን መንፈስህ እስኪተወኝ ከአንተ ራቅኩ....."
ብላ አለቀሰች። ጌታም መለሰላት " በኔ አምነሽ ንስሀ ገብተሽ እንድታገለግይኝ በተደጋጋሚ ብዙ እድል ነበረሽ።...." በጌታ

ለጓደኞቻችሁ ሼር

@CHRIST_TUBE

https://www.youtube.com/@melonamelos2

#ተራኪ_አና_ንጉሴ
1.9K viewsMeron, edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 07:08:56
#የማለዳ_ቃል

መዝሙረ ዳዊት 94
18 እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ምሕረትህ ረዳኝ።
19 አቤቱ፥ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
22 እግዚአብሔር መጠጊያ ሆነኝ፥ አምላኬ የተስፋዬም ረዳት ነው።

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.0K viewsMeron, edited  04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:00:18 " ብሎ በጩኸት ተናገረ እኔም በተራዬ በፈገግታ ተሞልቼ ሄድኩ ቲቸርም በደስታ ጨብጦ ሰጠኝ እኔም እጅ ነስቼ በትህትና ተቀበልኩት በተራው ቢኒ ለጉድ አፏጨልኝ ቲቸርም ቀጥሎ "ሶስተኛ የወጣችው ተማሪ ሊድያያያያ!!!" ብሎ ከሁላችንም ይበልጥ ደስ አለው ሊዱ ከመቀመጫዋ እስክትነሳ ራሱ ሳይጠብቅ እቅፍ አደረጋት እሷም ሰው ሁሉ በሚያውቃት ፍልቅልቅነቷ በውብ ሳቅ እየሳቀች "አመሰግናለሁ ቲቸርዬ" ብላ እሷም አቀፈችው ሁሉም መምህራኖቻችን ሊዱን ከሚባለው በላይ ነው የሚወዷት የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ቆመው በፉጨት እና በጩኸት አደመቋት እኛም ቲቸር እና ሊዱ ወደቆሙበት ቀርበን አቀፍናት ናሆሜ በጣምምም ደስ ብሎት ነበር ሊዱ በሰዎች ጎበዝ እና ጠንካራ ሆና እንድትጠራ ከሁላችንም ይበልጥ ህልሙ ነው ደስታውን መቆጣጠር አቅቶት እምባው ዱብ ዱብ እያለ አቀፋት ሁሉም የክላሳችን ተማሪዎች ሊዱን ለማቀፍ ሰበብ ነው የሚፈልጉት እነሱም እየመጡ አቀፏት የመጨረሻ መገናኛችንም እንደመሆኑ መጠን የክላሱ ተማሪዎች በሙሉ አብረውን ሆነው አይረሴ ፎቶዎችን ተነሳን ትንሽ እንደቆየንም ሊያ እና ኬብሮኔ በደስታ ተሞልተው እየሮጡ መጡ ልክ እንዳዩንም "በእናታችሁ ኑና እቁፉን" ብለው እጃቸውን ዘረጉልን እኛም ምን ተገኘ?? ውጤት እንዴት ነበር?? እያልን አቀፍናቸው እነሱም ውጤቱ በጣም አሪፍ እንደሆነ እና ከምንጊዜውም በላይ ደስ እንዳላቸው ደጋግመው ነገሩን እኛም ደስ እያለን ወረቀታችንን አሳየናቸው ነገር ግን በሰዐቱ የእነሱን ወረቀት አላሳዩንም ነበር እኛም ስለነገሩን እንጂ ስለ ማረጋገጫው ትኩረት ሳንሰጥ አለፍነው ሊያ ደስታዋ አልተቻለም በጣምም እየተፍለቀለቀች "በጌታ ጓደኞቼ ዛሬ ልጋብዛችሁ!!" አለችን እኛም እርስ በርስ ተያይተን ቢኒ "ውይ ሊያያ ዛሬ እንኳን ምንችል አይመስለኝም ቸርች መሄድ አለብን" አላት እሷም ወዲያው ቀበል ብላ "እኮ ትሄዳላችሁ እኮ ትንሽ ነው የምንቆየው" አለችን ኬብሮንም ከእሷ በላይ ጎተጎተን በስተመጨረሻ እሷን ማስከፋት ስላልፈለግን ሁላችንም ተስማምተን ጉዟችንን እኔና ሊያ መጀመሪያ ወደ ተዋወቅንበት ወደዛ አስጠሊታ ብዬ ወደናኩት የወጣቶች መዋያ ቦታ አደረግን. .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.0K views@Maranata, edited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 20:00:18 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
      ምዕራፍ=አንድ
       ክፍል=33
    ሳባ ካሳሁን

ቢኒን ዞር ብዬ ሳየው አይኑ ደም መስሎ የፊቱ ቅላት በሰከንዶች ጠፍተው ጉንጮቹ ቲማቲም መስለዋል ደምስሩ የፍጥኝ ተወጣጥረው ሲታይ ያስፈራል አይኔን ከእሱ አንስቼ ወደ ናሆሜ ጣል ሳደርገው  አስተያየቱ የመወዛገብ ነው ልክ አንድ ነገርን ላድርገው አላድርገው እያልን እሱን እያየን በሀሳብ እንደምንተክዘው እሱም ፍዝዝ ብሎ ተውጧል የኔም ስሜት ተወዛግቦ ሊዱን ሳያት ፍዝዝ ብላ ታያቸዋለች እነሱም "እስቲ ማን ይቅደም!! ማን ይቅደም!?" እየተባባሉ ሁለት ሲጋራ በመማግ ቀድሞ የጨረሰ ይፎካከራሉ በእጆቻቸው የያዟቸውን ሲጋራዎች በጣም በፍጥነት እያፈራረቁ እያጨሱ ይሳሳቃሉ ከልባቸው ደስተኛ ሆነው ነበር እኛ እንደ ሀውልት ደርቀን ቀረን "ኡፍፍፍፍ ጥሜ ረካ እስቲ ኮኬኑን አቀብለኝ" እያለች መሳብ ጀመረች ቀጠልም አድርጋ "እሰይይይይ ይብላኝ ለማያጨሱ life አመለጣቸው" አለች በጣም ጮክ ብላ ወዲያው በሀሳቤ "ቆይ ለምን አልሞክረውም ለምን??? ምን ችግር አለው normal ነውኮ ባይሆን አንዴ ሞክሬ አቆመዋለሁ" ብዬ አሰብኩ ወዲያው ልቤ ግን "በጌታ ስም ምን ስትይ አሰብሽው እንዴት ሆኖ አንቺ ልጅ ሁለተኛ ጊዜሽ ነው እንዲህ አይነት የቀሽም ሀሳብ ስታስቢ" አለኝ አዕምሮዬም ቀበል ብሎ "አይይይ የምን የቀሽም ሀሳብ ደሞ ምን ምን እንደሚል ማወቁ እኮ አይከፋም ከዘመኑ ጋር መጓዝ አለብሽ እኮ የምን መፍዘዝ ነው?" አለኝ እጆቼ እና እግሮቹ ለመሞከር መስገብገብ ጀመሩ ልቤ "ጌታ! ጌታ!" ይለኛል አዕምሮዬ "normal normal" ይለኛል ሱስ ውስጥ እንዳልገባ ይህን ነገር መሞከርና ማሰብ እንደሌለበኝ ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩት ሊያ በጣም ጮክ ብላ "ኦው የኔ ፍቅሮች!!! መጣችሁ እንዴ?" አለችን ከመቼውም በላይ ደስተኛ ሆናለች ቢኒም ቲሚቲም መስሎ ያስፈራው ፊቱ ላይ ሀይለኛ ኩስታሬ ተሞልቶ "አዎ ሊያ ኑ በቃ እንሂድ!" ብሎ ከአጠገባችን በፍጥነት ሄደ ሁሉም ምን ሆኖ ነው? ብለው ዞር እያሉ አዩት እኔም ግራ ተጋብቼ ሮጥ ብዬ ተከተልኩት "ምነው ቢኒዬ ምን ሆነህ ነው?" አልኩት ቢኒም አሻግሮ በጥልቅ ስሜት ተመስጦ አይኔን እንኳን ሊያየኝ በማይችልበት ሁኔታ ሆኖ "ከራሴ ጋር እየታገልኩ" አለኝ ይህን ቃሉን መቼም ልረሳው አልችልም ከዚች ቀን ጀምሮ በልቤ ታትማለች "ከራስ ጋር ትግልልል?? ምን ለማለት ፈልጎ ነው?" ብዬ ከራሴ ህይወት ጋር ላገናኘው ፈለኩ በዚህ መሀል በደንብ ልጠይቀው ስል ሁሉም ተሰባስበው ወደኛ መጡ ከቢኒ ጋር ምንም ሳናወራ አብረን መጓዝ ጀመርን ሊያና ኬብሮን  ደስተኛ ሆነዋል ዛሬ የኛ ደስታ በትንሹ ክፍተት እንደገባው ተሰምቶኝ ነገሩን ሳስበው ማስቆም እንዳለብኝ ተሰማኝ ግን ልክ አንድን የቲቪ ጣብያ ሳንፈልገው ስንቀር እንደምንቀይረው አዕምሮዬ ረፍት ነሳኝ በልቤ የሚያንዣብበው ጥያቄን መልስ ለመስጠት "ከራሳችን ጋር ያለውን ትግል እንዴት ማስቆም አለብን? እነ ሊያ ምን ለማድረግ እየሞከሩ ነው??" ብዬ ሳስብ ወዲያው ደሞ ይህ አዕምሮዬ "አያይ ዝም ብለሽ ትግል ምናምን እያልሽ ራስሽን አታጨናንቂ ደሞ አትርሺ ሊያ ላንቺ ህይወቷን ልትሰጥሽ የነበረች ከጥሩም በላይ ጥሩ ጓደኛሽ ነች" ብሎ ከመልስም የሚያፀፅት መልስ ይሰጠኛል ሳላስበው በጣም ፍዝዝ እንዳልኩ "ኡፍፍፍፍፍ" ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ የሚገርመው ነገር ግን ማንም አልሰማኝም እነ ሊዱ በራሳቸው አለም ውስጥ በሀሳብ ተነክረዋል ቢኒም በጥልቀት ማብሰልሰል ውስጥ ነው
እነ ሊያ አንዴም እንኳን እንዲህ ስንብሰለሰል "ምን ሆናችሁ ነው??" ሊሉን አልፈለጉም ከኬብሮን ጋር የሆነ ነገር እየተባባሉ ፊታቸው በደስታ ተሞልቷል እኔም እንደምንም ከዚህ ሀሳብ ለመውጣት ስለፈለኩ ራሴን ለማነቃቃት ሞከርኩ ሌላ የሚገርመው ነገር እነሊያ አብረውን እየሄዱ ነው ለወትሮው ከትምህርት ቤት በር የምንለያየው ዛሬ እንዴት? ብዬ እያሰብኩ "እንዴ ሊያ ዛሬ የት እየሄዳችሁ ነው?" አልኳት እነ ሊዱም ቀና ብለው መልሷን ጠበቁ "አይ ዛሬ ሌላ ቦታ ነው የምንሄደው" አለች በመቆዘም መልኩ በሰዐቱ ምንም ልላት አልቻልኩም "እሺ" ብያት እኔና ሊዱ ስለደረስን ተሰናብተናቸው መንገዳችንን ቀጠልን ሊዱም እጄን ያዝ አድርጋኝ "ምነው ሜሪዬ ደህና አይደለሽማ?" አለችኝ "ምን ልበላት? መቼስ ትግል ምናምን ብዬ ምንም የማታውቀውን ልጅ ጭንቀት አልፈጥርባትም" ብዬ "እ  አዎ ባክሽ ትንሽ ራሴን አሞኝ ነው" አልኳት "እሺ ሜሪዬ በቃ እንገናኛለን ቤት ልሂድ" አለችኝ እንዲህ ስትለኝ አንድ ነገር ከአይኖቿ አነበብኩ እሷም በትክክል የኔና የቢኒ ትግል አግኝቷታል ምንም መልስ ልሰጣት አልቻልኩም በውዝግብ ብዛት የታመመውን ራሴን ይዤ እሺ ብያት እቅፍ አድርጌ ተሰናብቻት ገባሁ። ቀኑ እንዲህ እንዲህ እያለ እነ ሊያን በተደጋጋሚ የዕፅ ብዛት ይዘው ማየቱን እየለመድነው ፈተናችንን በሰላም በጣም በሚገርም ውጤት ጨረስን ዛሬ ቀኑ ሌላ አዲስ ቀን ነው በጠዋቱ ተነስቼ ውጤት ለመቀበል እየተዘጋጀሁ ነው ቤት ሁሉም ጥሩ ውጤት እንዳመጣሁ ስለተማመኑብኝ ምንም አልጓጉም ሊዱዬን በር ላይ ወጣ ብዬ ጠበኳት እሷም እየተፍለቀለቀች ከሩቅ ስትመጣ አየኋት መቼስ እንደተለመደው እሷን መጠበቅ ከባድ ነው የበሩን ጠርዝ ደገፍ ብዬ ጠበኳት እሷ ጋሼ ጋር ሄዳ ከቤት የሰራችላቸውን ምግብ ሰጥታቸው እዛ ያሉትን ባለሱቆች ሄዳ ስማቸው እኔን ልታበሳጨኝ "በቃ በኋላ መጣለሁ ሜሪ ትገለኛለች!!" ብላ እየሳቀችብኝ መጣች ደሞ ከእሷም ብሶ "እማዬንማ ሰላም ሳልላት አልሄድም" አለችኝ እኔ ሀሳቤ ሁሉ ውጤቱን እስከምቀበል ስለሆነ "በእናትሽ ስትመለሽ ታገኛት የለ የት ትሄድብሻለች!" ስላት በሩን ክፍት አደረገችና በጣም ጮክ ብላ "እማ!!! እማዬ! በኋላ መጣለሁ እሺ! ውጤቴን ባንቺ ነው የማስከፍተው ወድሻለሁ" አለቻት እኔም እያቻኮልኩ አወጣኋት እና ወደ ትምህርት ቤት ሄድን እነ ናሆሜንም እዛው ክፍል አገኘናቸው በጣም ደስ የሚለው ነገር የክፍላችን ተጠሪ የሆነ መምህር በፈገግታ ተሞልቶ  "እሺ እንግዲህ ውጤቱ እንደታወቀ ነው በጣም አኩርታችሁኛል ከትምህርት ቤቱ አንደኛ የወጣው እንደተለመደው ቢኒያም ነው" ብሎ የቢኒን ውጤት ለመስጠት ጋበዘው ሁላችንም ደስስ እያለን በጭብጨባ ከመቀመጫችን ተነስተን አጀብነው ናሆሜና ሊዱ ለጉድ አፏጩለት ቲቸርም ቀበል አለና  የተማሪዎቹን ልብ በትንሹ ለማንጠልጠል እየሞከረ  "ሁለተኛ የወጣችው. .  ሜሮን ሰለሞን!!!!
1.9K views@Maranata, edited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 08:15:50
#የማለዳ_ቃል

"በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘላለም ዓለምም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፤ ለታላቅነቱም ፍጻሜ የለውም።"
-መዝሙረ ዳዊት 145:2-3

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
312 viewsMeron, edited  05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ