Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-27 20:00:29 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=አንድ
ክፍል=39
ሳባ ካሳሁን

እጇን እያፋተገች ወደእኔ ተመልክታ ትንሽ ለመረጋጋት ሞከረች እኔም እንድትነግራቸው በአይኔ ምልክት ሰጠኋት "እንዴ ልጆች ምን ሆናችሁ ነው?" እያሉ መታገስ አቃታቸው እኔና ሊዱም ተባብረን በእሷ እና በአክስቷ መካከል የተፈጠረውን ነገር ሁሉ በዝርዝር ነገርናቸው እማ በጣም ተናደደች በመረጋጋት የሚያምነው አባዬ ግን ነገሩን ቀለል አድርጋ መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው በጭንቀትና በንዴት ምንም እንደማያመጡ እየነገራት ሀሳቡን ሰብሰብ አድርጎ "በቃ ቡቻዬ እኛ እናናግራታለን ለምን እንደዚህ እንዳለች ብናውቅ ደግሞ አሪፍ ይሆናል ለማንኛውም ግን እናንተ ተረጋጉ" ብሎን "ደግም ይህን የመሰለ የፍቅር ቤትሽን ትተሽ እዛ ባዶ ቤት ከመመላለስ ተርፈሻል" አላትና ፈገግ አለ ሊዱዬም መልሳ ሳቅ አለችለት እማ ንዴቷ ባይለቃትም ለአባዬ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው ለማሳወቅ ጠቀስ አድርጋው "በሉ በቃ ቡቻዬ እኛ ልንወጣ ነው ዛሬ ቶሎ ነው የምንመለሰው እሺ!" ብላ ቁልጭ ቁልጭ እያልን በተቀመጥንበት ሳም አድርገውን ወጡ ሊዱዬም በስስት እያየችኝ "ሜሪ ግን አክስቴ የምትረጋጋ ይመስልሻል?" አለችኝ እኔም ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ በሙሉ መተማመን "እንዴ አዋ ታውቂያታለሽ እሷ አፏ እንጂ ልቧ ምንም አያውቅ" ብዬ ስናገረው በጣም በቀለለኝ በእሷ ልብ ግን ሰርጎ ሙሉ ተስፋ የሆናትን መልስ ሰጠኋት እሷም በጣም ፍንክንክ እያለች "እሱማ ልክ ነሽ!" ብላ ተስፈንጥራ ተነሳች ከውጭ እስከሚሰማ ድረስ እየተጯጯህን ውሀ ስትረጨኝ እሱን ሽሽት ስደበቅ ትራስ ስትወረውርብኝ ልክ አይጥ የምታሯሩጥ ድመት አይነት ድርጊት ስታሳየኝ እኔም አኳኋኗ ሲያስቀኝ በሳቅ ብዛት ማውራትና እጆቼን ማዘዝ ሲያቅተኝ ከልባችን ስንፈነድቅ ቆየን በስተመጨረሻ ሊዱ ዬ ድክም ሲላት በረጅሙ እየተነፈሰች "ኡ..ፍ እህ ደከመኝ" ብላ በሶፋው ልክ በተነጠፈው ወፍራም ቀይ ምንጣፍ ላይ ተዘረረች እኔ ሳቄን ላቆም ባለመቻሌ እየተገረምኩ "አየሽ አቅምሽን ማወቅ ነበረብሽ አትችይኝም እያልኩሽ ሳይቸግርሽ" ብዬ የወዳደቁትን ትራሶች አነሳሳሁ ሊዱም ትንሽ አረፍ ብላ ተነሳችና ቤት ውስጥ የሚሰሩትን ስራዎች እየተጋገዝን ሰራን በመሀል የቤታችን በር ተንኳኳ ጓዲያ እንዳለሁ ጮክ ብዬ "ሊዱ በር ይንኳኳል!" አልኳት እሷም "እሺ እከፍታለሁ!" ብላኝ እየሮጠች ሄዳ ከፈተች እኔም በትንሹ ከማርጀታቸው ብዛት ለመዝጋት የሚያታግሉትን የቤቱ ክፍሎች በር እየዘጋጋሁ እነ ናሆሜ ሲንጫጩ ሰማኋቸው በጣም ናፍቀውኝ ስለነበር ተው ግጠም አትግጠም የያዝኩትን በር ወዲያው ትቼ እየሮጥኩ ወደነሱ ሄድኩ "ሜሪሪሪ!!" ብለው ሁለቱም አቀፋኝ እኔም "ጓደኞቼ!!" ብዬ ተጠመጠምኩባቸው በእውነት ለካስ ምን ያህል ደስታ በእውነተኛ ጓደኛሞች መሀል አለ በእቅፋቸው በገባሁና ሳቃቸውን ባየሁ ቁጥር ሰላም ይሰማኛል ሊዱ ጎሮሮዋን እየጠራረገች በዚያ ደስ በሚል ቅብጠቷ "እህ..እህ ኸረ ሰው ረስታችኋል" አለችን ናሆሜም እሷን ለማብሸቅ ወደኛ ዞሮ ብሎ "ውይይ እንጃ ቢኒ! ሜሪ! እዚህ አከባቢ ከእኛ ሌላሰው ይታያችኋል?" አለን እኔና ቢኒ እየሳቅን ሊዱ ደሞ እያኮረፈች "እንዴ! ነው ናሆሜ ነው?" አለችው ቢኒም መለስ ብሎ "አዎ አንተ.ግን አንድ እርግብ እንዴት ማውራት እንደቻለች ባላውቅም ከፊት ለፊቴ ልክ እንደልጅነታችን እጅ በደረት አጣምራ ለንቦጯን ጣል አድርጋ አሁን ደሞ እኔን ቁርጥ የድመት በሚመስሉት አይኖቿ የጎሪጥ እያየችኝ ነው" አለን ሊዱ ይህን ጊዜ ሳቋ አመለጣት ናሆሜ እሷን ማብሸቅ ሱሱ ነው "ኸረ ቢኒ ተሳስተሀል እኔ ቢራቢሮ ነው የሚታየኝ" አለው ሊዱ ዬ በቀላሉ ስትሸነፍ ቢኒ ሲያግዛት ደግሞ ስታሳዝነው ናሆሜ ለእሷ ሲደረብ ሊዱ "Yes አገኘሁህ!!" እያለች እሱን ለማናደድ ለቢኒ ስታግዝ እኔ የህይወቴ ትልቁ ክፍል የሆነው የሀሳብ ትካዜ ውስጥ ገብቼ ልቤንና ውስጤን ወደነሱ ጣል እንዳደረኩ አስተውላቸው ጀመር "ግን እኛ ተለያይተን መኖር እንችል ይሆን?? ኸረ እንዴት ሆኖ ግን የወደፊት ህልሞቻችን እውን ይሆናሉ? ሊዱ ዬስ እድሜዋን በሙሉ ስታልም የነበረውን ነገር ሁሉ ሲሳካ ስናይ ምን እንል ይሆን?" እያልኩ ከሀሳቤ መለስ ስል ሁሉም በደስታና በሳቅ ያነቡትን እንባ እየጠራረጉ ነው ቶሎ ብሎ ናሆሜ "ኸረ በቃ ሜሪ ልብሳችሁን ቀይሩ እና እንውጣ ዳጊ(እነ ሊያን ሳናውቃቸው በፊት አንድ ጊዜ ልደቱን ሆቴል ያከበርንለት ልጅ) እኮ ደውሎልን እንገናኝ ብሎን ነው የመጣነው" አለን እውነትም ከተገናኘን በጣም ቆይተን ነበር "እውይይ! አይ ዳጊ ምን ይለን ይሆን ብዙ ጊዜ ደውሎልኝ ነበርኮ እየረሳሁት ሳልደውልለት" አልኳቸው ሊዱም ድንግጥ ብላ እንደኔ እጆቿን በአፏ ይዛ "ወይኔ በጌታ ምን ይለናል?" አለችን ቢኒ ነገሩን ቀለል አድርጎት "ኸረ ችግር የለውም እሱን ታውቁታላችሁ ነገር አያካብድም ግን በቃ እየጠበቀን ነው ቶሎ እንውጣ" አለን እኛም እሺ ብለን ልብሳችንን ቀያየርን ፀጉራችንንም እንደቅጡ አስይዘን ቤቱን ዘጋጋንና መንገዳችንን ወደ ምንወደው ጓደኛችን አቀናን ሊዱን እየተነጫነጭን ብናስቸግራትም ጋሼን ሳናይ አናልፍም ብላ ወሰደችን ትንሽ ከእነሱ ጋር ቆይተንም ዳጊ ጋር ሄድን ከሩቅ ስናየው አንገቱን ሙሉ የሚሸፍን ለሰሞኑን አየር የሚሆን ወፍራም ሹራብ ከሚያምር ቱታ ጋር አድርጎ የመብራት ፓል ደገፍ እንዳለ ስልክ እያወራ ቆሟል እኛም እንደለመድነው እየተንጫጫን ወደሱ ሄድን ልክ እንዳየን እኛን በመጠበቅ በጣም ስለሰለቸው ድምፁን ዝቅ አድርጎ "እናንተ ግን ለኔ እንዲህ ናችሁ? ቆይ ብቻ" ብሎ በፍቅር አስፈራራን እኛም ይበለን እያልን እስኪጨርስ ጠበቅነው ልክ አውርቶ እንደጨረሰ ዞር ብሎ ሲያየን ሁላችንም በአንዴ "ዳጊ ሊዱ እኮ ነች ያስቆየችን! ዳጊዬ ስትደውል እኮ ያላነሳነው ስላላየነው ነው! ዳጊሻ ይቅርታ! እ ዳጊ እ!" እያልን ሳንደማመጥ ጮህንበት እሱም ልንደበድበው አይነት አስመስሎ "ኸረ በቃ ሰላም በሉኝ" አለን እኛም ሁኔታችንንና የሱን አባባል ስናስበው ከት ብለን እየሳቅን አቀፍነው በእውነት የማንረሳውን ጊዜ እያሳለፍን በእውነተኛ ፍቅር ተከበብን ሰዐቱ እንደወትሮው ሳናስበው ሄደ የሶሲም መምጫ ስለደረሰ የግድ ቤት መሄድ ነበረብን እነ ናሆሜም ይህን ስለሚያውቁ ከዳጊ ጋር ሊሸኙን አብረን ተያይዘን ወደ ቤት መጣን ሊዱ በፈገግታ ተሞልታ "በእውነት ዳጊ ናፍቀከን ነበር እንኳን አገኘንህ" አለችው እሱም ደስስ እያለው "ጓደኞቼ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል" አለንና እነ ቢኒንም አውርተናቸው ተቃቅፈን ተለያየን ወደ ቤት ስንገባ እማ ልብሷን ቀያይራ ቤት ውስጥ ጉድ ጉድ እያለች ነበር "እማ! እማይዬ" እያልን ገባን ስናያት ግን ፊቷ ጥቁር ብሎ በዚያ ቅላቷ ላይ ጉንጮቿ የፋመ ከሰል መስለው ነበር ልክ እንዳየችንም ዞር ብላ ፊቷን አሻሽታ "ልጆቼ መጣችሁ?" አለችን ሊዱ ድንግጥ ብላ "እንዴ እማ ምን ሆነሽ ነው?" አለቻት እማም እኛን እንዳይከፋን በሚመስል ሳቅ እየሳቀች "አይ ልጄ ድካሙ ነው" አለችን እኛም ቀለል አድርገነው "በቃ እማ እናግዝሽ" ብለን ከስር ከስሯ አብረናት ሆንን ሶሲ መምጫዋ ደርሷል ቡናችንን አቀራርበን መቅሰስ አዘጋጀን ቤቱን ፏ ብናደርገውም ግን የወትሮው የእማ ሳቅ ተለይቶናል ብዙም ሳይቆዩ ሶሲና አባዬ አብረው መጡ አባዬ ይባስ አይኖቹ ደም ከመምሰላቸው የተነሳ ያስፈራል እኔና ሊዱ እሮጠን ሄደን ስለፈተናው ጠየቅናት ይህን ጊዜ እማ ሹልክ ብላ አልፋን አባዬን ይዛው ወጣች..
...ይቀጥላል
➥ @CHRIST_TUBE
2.3K views@Maranata, edited  17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 07:05:04
#የማለዳ_ቃል

" እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።"
-መዝሙረ ዳዊት 11: 4

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
963 viewsMeron, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 21:46:12 #Spiritual_Speech

❝በሕይወትህ ውጫዊ ክፍል የሚሆነውን ነገር እውስጥህ የሚሆነውን ያህል ጠቃሚ አይደለም ምክኒያቱም ያለህበት ሁኔታ ጊዜያዊ ሲሆን ባህርይህ ግን ለዘለዓለም ይኖራል! ❝
ፓስተር ሪክ ዋረን

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥@CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.1K viewsMeron, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:01:19 #ምን_ያስባሉ?

◌ እግዚአብሔርን በፅድቅ ብንመላለስ ልናየው እንችላለን? ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ያላችሁን ሀሳብ ግለፁ? ብለን በጠየቅናችሁ መሰረት መልሶቻችሁን ልካችሁልን ነበር ለተሳትፎአችሁ እያመሰገንን ያልተደጋገሙ እና የተመረጡ ሀሳቦችን እንዲህ ባለ መልኩ አቀረብንላችሁ:-

➲ Мιᴄкєу ᴇℓ:አይመስለኝም .... በፅድቅ መመላለስ ማለት ተግባር ነው እንደ እኔ ሀሳብ ከሆነ እግዝአብሔርን ሚናየው በ መንፈስ ስንሆን ነው 10ቱን ትዕዛዝ ስለጠብቅን አልያም ከስጋ ምኞት ስለራቅን ሳይሆን በመንፈስ ሀሳብ ስንሞላ ስለ እግዝአብሔር ሀሳብ ብቻ ስናስብ ነው

➲Tsega Dera: ልናየው አንችልም ምክንያቱም እ/ር ያየዉ የለም ለሙሴ ራሱ ፊቱን አልገለጠም ጀርባውን እንጂግን ልናየው የሚለው ቃል ግራ ያጋባል ምክንያቱም እ/ር ፊት ለፊት አየዉት ይለናል ማቲ 5 ፣ 8 ላይ እንዲህ ይላል ልበ ንፁሆች ብፁዋን ናቸው እ/ር ያዩታልና ይላልነገር ግን በአካል ግን ማንም ሊያየው አይችልም

➲ Efi Mak: ዮሐንስ 14¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁸ ፊልጶስ- ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።⁹ ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?በመጀመሪያ ደረጃ በራስ ምልልስ የሚገኝ ጽድቅ የለም እግዚአብሔርን ለማየት ደግሞ በክርስቶስ ልናምን ይገባል ምክንያቱም ያለ ክርስቶስ አይደለም እግዚአብሔርን ልናይ ይቅርና በአብ ፊት ልንቆም አንችልም።ዋናዉ ነገር በክርስቶስ ከሆንን ደግሞ በክርስቶስ ጽድቅ መመላለስ የግድ ነዉ።ክርስቶስን ከየነዉ እግዚአብሔርን አይተናል ብቻ ሳይሆን እናሳያለንም።

➲Bezawit Mengesha:አዎ እናየዋለን ። እግዚአብሔር አየን ስንል እኮ መንፈሱ ከእኛ ጋር ስተባበር በህልውናው ውስጥ ነፍሳችን ስትዋኝ ስትረሰርስ ነው እና እግዚአብሔር ከፅድቅ ጎን ሁል ጊዜ አለ ዳዊት ራሱ ''እኔ ግን በጽድቅ ፍትህን አያለው ክብርህን ሳይ ጠግባለው ።'' መዝ 17:15 ነው ያለው

➲ BEKA KAKA:ሰላም እህት ውንድሞቼ ይሄ ጥያቄ እኔ እንደገባኝ መጠንስናገር ልናየው እንችላለን ሳይሆን እናየዋለን ነው እኔ ምለው ምክንያቱም ይሀ 14፡21 ሲናገር ትእዛዜ በእርሱ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለው ራሴንም እገልጥለታለው ይላል ይሄ እኮ ስለ እየሱስ ነው ሚናገረው ሚል ጥይቅ ውስጣችሁ ሊኖር ይችላል ግን ድጋሚ ወደ bible ልመልሳችሁ እዛው ዩሀ12:35 ላይ ሲናገር እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል ይላል ስለዚህ እግዝእብሔርን በእየሱስ ማየት ምንችለው ስንወደዉ ብቻ ነው መውደዳችንን ደግሞ ምናሳየው ትዛዙን በመጠበቅ ነው ምክንያቱም bible ላይ ሲናገር ዩሀ14:15 ሲናገር ብትወዱኝ ትዛዜን ጠብቁ ይላል እኔ የመለስኩበት መንገድ እግዚአብሔርን በእየሱስ ማየት እንደምንችል ነው ግን እግዚአብሔርን በእየሱስ ማየት ምንችለው ስንወድውን እና መውደዳችንን ትዛዙን በመጠበቅ ስንመላለስ ነው ተባረኩ

➲ ኗarega Daniel:መዝ 10:4

➲ መዝሙር 91 (Psalms) 1፤ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል። 2፤:እግዚአብሄርን ያየው አንድም እንኳን የለም አንድ ልጁ እየሱስ ተርኮታልአምነን በጽድቅ ብንመላለስ እናየዋለን እየሱስን እግዛብሔርን አሳየን ብለው ጠይቀውት ነበር እኔን ያየ አባቴን አይቷል ብሎ መለሰላቸውእኛ በቅድስና ብንኖር አይተነዋል እያየነው ነው ምህረቱን ቸርነቱን ቀምሰናል አይተናል ደግሞም እናያለንከኛ የሚጠበቀው በስጋ አይን ሳይሆን መንፈሳዊ አይኖቻችን ሲከፈት እሱን ብቻ ማየት ይሆንልናል

➲ Cheru Aman:ዘጻ 33-20 ደግሞም።ሰው አይቶኝ አይድንምና ፍቴን ማየት አይቻልህም አለ ።ስለዚህ ልናየው አንችልም፣ እስካሁን ድረስ መላእክትም አላየም።

የዛሬን እንደዚህ አቀረብን ሁላችሁም ላደረሳችሁን ሀሳብ እያመሰገንን። ሙሉ መልሶችን ከላይ በአያያዝነው ጥያቄ Comment መስጫው ውስጥ በመግባት ማየት ይችላሉ። ምን ያስባሉ? የሚለው ዝግጅታችን የሚቀጥል ይሆናል።
ተባረኩ

ለኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
197 viewsMeron, 13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 07:33:51
#የማለዳ_ቃል

" መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።"
-የዮሐንስ ወንጌል 10: 14-15

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.0K viewsMeron, edited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 20:42:23 ለእንድ ሳምንት ያክል
1.3K viewsMeron, 17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 20:38:20 ከራስ ጋር ትግል በአንዳንድ ምክኒያት ለትንሽ ጊዜ ብቻ የማይቀርብ መሆኑን በጌታ ፍቅር አንገልፅላችኋለን

ተባረኩ
1.3K viewsMeron, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 19:40:36 ምን ያስባሉ?
➲እግዚአብሔርን በፅድቅ ብንመላለስ ልናየው እንችላለን? ከመፅሐፍ ቅዱስ አንፃር ያላችሁን ሀሳብ ግለፁ?

ያስተውሉ በእርሷ መልስ ብዙዎች ይታነፃሉ ያልገባቸውን እውቀት ይረዳሉ። የእርሶን መልስ 1 ቃል ቢሆንም የተረዱትን በ Comment Section(መስጫው) ያስቀምጡ። ሲፅፉ በ አማርኛ Keyboard ቢሆን ይመረጣል።
1.3K viewsMeron, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 07:04:50
#የማለዳ_ቃል

" እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።"
-ትንቢተ ዕንባቆም 2: 20

" But the LORD is in his holy temple: let all the earth keep silence before him."
-Habakkuk 2: 20

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.5K viewsMeron, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-07 07:05:06
#የማለዳ_ቃል

" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።"
-ወደ ዕብራውያን 9: 28

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.8K viewsMeron, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ