Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-06-03 08:07:15
#የማለዳ_ቃል

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4
16 ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
17-18 የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.5K viewsMeron, edited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 13:30:25 #Spiritual_Speech
❝ ጎዶሎነትህ የማይታይህ ሙሉ ስለሆነክ ሳይሆን የተሰጠህ ህይወት ዘለዓለማዊ ስለሆነና በምድር ብቻ ተወስኖ የማይቀር ትልቅ መኖሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ተዘጋጀልህ ነው በምድር አንደምትኖረው 80 ዓመት እንደሚኖር ሰው ብቻ ሳይሆን ዘለዓለም እንደሚኖር እያሰብክ ስለምትኖር ጭምር ነው ! ❝

ልኖርለት የተገባው ህይወት ይህ ይሁ
ን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥@CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.6K viewsMeron, edited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 07:01:26
#የማለዳ_ቃል

" ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፤ በቃልህም ታመንሁ።"
-መዝሙረ ዳዊት 119: 81

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.6K viewsMeron, edited  04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:00:07 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
         ምዕራፍ=አንድ
          ክፍል=40
ሳባ ካሳሁን

ሊያ በሩን ስትከፍተው ፍፁም ያላሰብነውና ያልጠበቅነው ነገር ነበር ያ ቤት ጭስ በጭስ ከመሆኑ የተነሳ ውስጡ አይታይም በድንጋጤ ብዛት እንደምንም በአይናችን አሻግረን ለማየት ስንሞክር ብዙ ልጆች ሽርጣቸውን አሸርጠው ቤቱን ሞልተውታል ግማሹ በእጁ ጫት ይዟል ግማሹ ሺሻና አሻሽ. ከልባቸው በሚመስል በደስታ ይሽካካሉ በበሩ መከፈት የተነሳ የታፈነው ጭስ ገለል ሲልና አስተውለን ስናይ በሙሉ እኛ ትምህርት ቤት በአይን ብቻ የምናውቃቸው እጅግ በጣም የሀብታም ልጅ የሆኑ በግቢው ዘናጭና ሰቃይ ተማሪ ተብለው የሚጠሩ ልጆች ናቸው ፊታቸው በቦክስ ተመቶ እንዳበጠ ሰዉ የጫቱ መአት ጉንጫቸውን ወጥሮ ይዞታል እኛ ደንግጠን በር ላይ እንደቆምን ነን ሁላችንም በሁኔታው አፋችንን ከፍተን እያየናቸው ሊያ ገባ አለችና "Heyyyyyyyyy ቤተሰብ" አለቻቸው ልክ እንዳዩንም ሁሉም ወደኛ ዞረው "ሊያዬ፣ ምርጥ ሰው!፣ ፍቅር" እያሉ እያሞካሹ ጠሯት እኛ ባለንበት እንደደረቅን ነው ሊያም ወደ ውስጥ ገባችና ወደ እኛ ዞር ብላ "እንዴ! እስካሁን ቆማችኋል ግቡ እንጂ!" አለችን እኛም ከአለንበት ፍዘት ብን ብለን እየተያየን ወደ ኋላ አንድ እርምጃ አፈገፈግን በውስጡ ያሉት ልጆች ግን "ኸረ ሊያዬ እንግዳ ይዘሽልን መተሻል እንዴ ኑ ግቡ!" ብለው በትልቅ አክብሮት ከመቀመጫቸው ተነሱ ፊታቸው ላይ የለመድነውን የእውነተኛ ፍቅር ሳቅ እየሳቁልን በእኛ ደንግጦ መቆም ተገርመው "ኸረ አትፍሩ ግቡ እኛንም አታቁሙን ኑ" አሉን አቀባበላቸው ልባችንን ነካው እነሱን ረግጦ መሄድ ከበደንና በአይናችን ተያይተን ወደ ውስጥ ገባን እንደገባንም "ኑ እዚህ ጋር" ብላ ሊያ ቦታ አመቻቸችልን እኛም በቤቱ ያሉት ልጆችም ቁጭ አልን አቀማመጣቸው ዝርግትግት ብለው ሀሳባቸውን ጣል አድርገው ነበር እኛ ኩርምት እንዳልን ልክ እንደሆቴሉ ታሪክ እርስ በእርስ እንድናወራ ፋታ አልሰጡንም ትኩረታቸውን ሁሉ እኛ ላይ ጥለዋል እኛም ያለን አማራጭ ቤቱን በአይናችን መቃኘት ስለነበር አንዴ ወለሉን ከዚያ ጣሪያውን 'ድም ድም' ደሞ 'ቡልቅ ቡልቅ' የሚል አይነት ድምፅ ያለው ስሙን በቅጡ የማናውቀውን የሚጨስ ነገር  ብርቅ አድርገን እያየን ሊያ ለብሳ የነበረውን ልብስ ቀይራ በሽቲ መጣችና ደስ በሚለን አስተያየት "እንዴ ፈታ በሉ እንጂ ምንድነው እንዲ ምትጨባበጡት ደግሞ አይሞቃችሁም እንዴ? አለችን በቤት ውስጥ ያለው ሙቀት በእውነቱ ለጉድ ነበር ሊዱ ዬ"አዎ ልክ ነሽ ይሞቃል" ብላ ኮቷን አወለቀችና ራቅ ብለን በተቀመጥንባት ስስ ፍራሽ ላይ እኔና ቢኒን መርኮዝ ብላ ጋደም አለች ትንሽ እንደቆየንም ከልጆቹ ጋር ማውራት ጀመርን በጣም ከምንገልፀው በላይ ደስ የሚሉ ልጆች ነበሩ ቀልዳቸው አወራራቸው የሚሰጡት አክብሮት ሁሉ ይማርካል በሰዐቱ ከሚጠቀሙት አስጠሊታ አደንዛዥ በስተቀር ምንም እንከን ስላላየንባቸው ከልባችን እየሳቅን ሀሳባችንን ጥለን ማውራት ቀጠልን በዙሪያችን ጫት፣ሲጋራ፣አሺሽ፣ ጋንጃ ከልማዳችን ወጥቶ ከቦናል በዚህ ጊዜ የጎደለንና የተደፈነብን አንድ ነገር ብቻ ነበር *ማስተዋል* ይህ ለኛ አለማችን ላይ እንደጠፋ ዳይነሶር በእኛ ልብ ውስጥ አልነበረም ማን ወሰደው? እንዴት አጣነው? እነዚህ ለኛም ያልተመለሱ ጥያቄዎች ናቸው በጓደኛችን እየተነዳን በገባንበት ሰላማዊ በተባለው ቤት ውስጥ ያን ያህል ደስታ ባናገኝም ግን ከልጆቹ መማረክ ሌላ ስሜታችን እየሳበ ያለው የአሺሹ ጭስ ሽታው አፍንጫችንን ሲያውደው አዕምሮኣችን ማጉት ማጉት እያለን ልባችን "በእየሱስ ስም! ሆ" ብሎ ቀልባችንን እየመታው አዕምሮኣችን "ምን ችግር አለው normal ነው አታካብዱ!" ብሎ ሲያርበተብተን ከራሳችን ጋር እየታገልንም ቢሆን አብረናቸው ዋልን ያለንበትን ቦታ አይናችን እና ልባችን ሳይወደው አዕምሮአችን ግን እንደ ተራ እና ቀላል ነገር እያሳየን ቆየን በመሀል ሞቅ ያለ ጨዋታ ይዘን ቢኒ ሊዱ እንድትነሳ እጇን መታ እያደረጋት እኔንም በአይኖቹ ምልክት እየሰጠኝ "mother ደወለች በቃ እኛ እንሂዳ?" አላቸው ሊዱ ልጆቹን ከልብ ስለወደደቻቸው ያለችበትንና የነበረችበትን ነገር ሳታስተውል "ኸረ ትንሽ እንቆይ!" አለችን በአባባሏ ብዙም ሳልገረም ቤት መሄድ ስላለብን ብቻ "ውይ ሊዱዬ እንሂድ" አልኳት ናሆሜም ላለመሄድ አቅማማ ልባችንን ሊገዙ የሚጥሩት እነዚያ ፍቅር አዳዳሲ ጓደኞቻችንም ፊታቸውን ጣል አድረጉት ከመካከላቸው አንድ የሚያምር በሚባል ደረጃ ያለ ልጅ ቀና ብሎ በስስት እያየን "እንዴ መች መጣችሁና ነው የምትሄዱት ምነው ቢና ደበርንህ እንዴ ይቅርታ በእውነት አስደበርንህ መሰለኝ" አለው ቢኒ እንሂድ በማለቱ እፍር እያለም ቢሆን "ኸረ በእውነት እንደሱ አይደለም እንዴ ብትደብሩን ይህን ያህል እንቆያለን?" አላቸው እና ሁላችንም ለመውጣት ተነሳን ሊያ ልታስጨንቀን ስላልፈለገች "ተዋቸው ዋናው መተዋወቃችን ነውኮ ነገም ቀን አለ" ብላ ፈገግ አለች ያወራችው ነገር ትልቅ ሀይል ቢኖረውም እኛ ሀሳባችን ቤት መሄድ አለብን እንጂ ይህ ቦታ አይመጥነንም አይሆነንም የሚለው ስላልነበረ ሳቅ ሳቅ እያልን የተከለለውን መጋረጃ ገለጥ አደረግነው ሊያም በአፏ የተወጠረውን ጫት ለማማግ አጠገቧ የተቀመጠውን ኮካ እየተጎነጨች የለበሰችውን ሽቲ አውልቃ ተነሳች የሚገርመው ሁሉም ስንገባ እንደነበረው ከመቀመጫቸው ተነስተው "በቃ እንወዳችኋለና ይሜ! በዚሁ እንዳትሰለቡብን ታድያ"' ብለው አንዴ በፉጩት ሲያሻቸው በጩኸት ፍቅራቸውን እየገለፁልን በክብር ሸኝተውን እኛም ደስ ብሎን አብረናቸው መቆየቱን ብንፈልገውም ግድ ስለሆነ ወጥተን ብዙም ሰው በማይታይበት በዚያ ጉራንጉር እየተሽሎከሎክን መንገዳችንን ቀጠልን ሁሉም ደስተኛ ሆነዋል በተለይ ሊዱ መንገዱን ሙሉ ስትስቅና ስለ ልጆቹ ስታወራልን የቀለዱትን ቀልዶች ደግማ እያሰበቻቸው ስታስቀን ሊያ በመሀል በመሀል አንዴ ሳቅ ደሞ ጥርሶቿን ነከስ ወዲያው ፈገግ ደሞ መለስ እያለች አንድም ቁም ነገር ሳናወራ እንዲሁ ስንሳሳቅ እኛ ቤት ደረስንና ቻው ብለናቸው ገባን ቤት ስንገባ እማ እና ሶሲ ነበሩ ሶሲ ረፍት ለማድረግ ሶፋ ላይ ጋደም ብላለች እማ ደግሞ ቡና እያፈላች ነበር እኛም "ቤቶች!! ሰላም ለዚህ ቤት" እያልን ገባን እማም ፈገግ እያለች "ውይ ጎረምሶች ሰላማችሁ ይብዛ" አለችን እኛም "ውይ ፀሀዩ እያልን ላብ ላብ ብሎን ስለነበር ቲሸርታችንን እያራገብን ወደ ክፍላችን ገባን ልብሳችንንም ቀያይረን ፊታችን ታጥበን ነፈስ ብሎብን ወደ ሳሎን ሄድን ሶሲን እንዳየናት እሮጠን አጠገቧ ቁጭ አልና "እ ሶሲ እንዴት ነበር?" አልናት እሷም አይኖቿን እንደጨፎነች "ብቻ ምንም አይል" አለችን በዚች ሁለት ቀናቶች ውስጥ ምን እንደሆኑ ሊገባን ባይችልም እማ ፊቷ ኮስተር እንዳለ "ቆይ እኔ ምለው የት ነበራችሁ??  አለችን ሊዱም ቶሎ ብላ "ውይ እማይዬ ከጓደኞቻችን ጋር ነበርን አለቻት እማ ግን እንደወትሮው ልታልፈን አልቻለችም ፊቷ ይባስ ደም እመሰለ "ታዲያ ቅድም ወደዚያ ጉራንጉር ውስጥ ለምን ገባችሁ??". . .
   . . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.7K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 07:05:05
#የማለዳ_ቃል

" ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።"
-መዝሙረ ዳዊት 27: 9

" Hide not thy face ar from me; put not thy servant away in anger: thou hast been my help; leave me not, neither forsake me, O God of my salvation."
-Psalms 27: 9

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.7K viewsMeron, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 07:04:47
#የማለዳ_ቃል

የማቴዎስ ወንጌል 24
42 ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።
43 ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር።
44 ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.9K viewsMeron, edited  04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 20:24:21 በዚያ ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ እየተሽሎከሎክን ሄድን ልክ ጨረስን ብለን ስንቆም አንድ ደሞ ከቅድሙ ለየት ያለ ጠባብ ዳገታማ ጉራንጉር ገባን ቢኒ በጣም ድክም ብሎት እያለከለከ "እንዴ ሊያ አንደርስም እንዴ?" አላት እሷም ከት ብላ እየሳቀችብን "ትንሽ ብቻ ነው የቀረን ደርሰናል" ብላ አነቃቃችን የአከባቢው ሽታ ለየት ያለ ስለነበር አፍንጫችንን ያዝ አድርገን ጉዟችንን ቀጠልን በጉራንጉር ውስጥ የሚያስፈራ ሸለቆ ልክ ሸለቆው ሲያልቅ ትናንሽ ከፍታዎች አላልቅ ሲሉን ሁላችንም ሊያ ላይ ጮህንባት "ጌታን በቃ ትንሽ ነው የቀረን ኑ" ብላ እጃችንን ይዛን መራመዳችንን ቀጠልን ትንሽ እንደሄድንም ከአንድ ትንሽዬ ብዙ ከመቆየት ብዛት ልትፈርስ ያለች ቤት ጋር ቆም አለች ናሆሜ ልክ እንደ ቢኒ ትንፋሹን እየሰበሰበ "ለምን ቆምን?" አላት ሊያም በፈገግታ "ደርሰናል!" ብላ ከፊት ለፊታችን እያየናት ያለችውን ቤት በር በረገደችው. . .
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.8K views@Maranata, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 20:22:52 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=አንድ
ክፍል=39
ሳባ ካሳሁን

እማ ሹልክ ብላ አልፋን አባዬን ይዛው ወጣች እኛ ግን ትኩረታችን ወደ ሶሲ መሆኑ ስለቀጠለ ሊዱ በጣም ጉጉት ብላ "እ ሶሲ እንዴት ነበር ድግሱ?" አለቻት ሶሲም በዚያ ሁሉ ጥያቄ የተወጣጠረውን ጭንቅላቷን ቀርቀር ደሞ ዘንበል በእጇ ያዝ ነሳ እያደረገች ተሳሳበችና ልታወራን ስትል ሊዱ ዬ ከላይ እስከታች አገላብጣ አይታት "ዴዴዴዴ (በሚገርም የመገረም ድምፅ) እውነትሽን ነው የኔ እናት እረዳሻለሁ መወጣጠር ሲያንስ ነው" አለቻት ሶሲ ድክም ቢላትም እሷ ከፈተናው በላይ ስለሆነችና በጥያቄ የተሞሉት ወረቀቶች ህይወቷን ስለማይቀይሩት በሶፋው ላይ ዝርር ብላ "ፈተናው አሪፍ ነበር ያው ትንሽ ጠጠር ያለ ነው። ጥያቄው ሲጠፋብኝ ከልዑል አምላኬ ጋር እየተነገገርኩ ጥሩ ሰርቻለሁ" አለችን እኔ የደስታ ፊት አሳይቻት እማ ትታ የሄደችው ቡና እንዳይገነፍል እየተዋከብኩ ሳለ ሊዱ በጣም ጮክ ብላ "እንዴ እንዴ! ሙስና ጭራሽ ኩረጃም ነበር?" አለቻት ልክ እንደሰማናት ፈገግ ብለን ልናልፈው ስንል ያለችው በደንብ ሲገባን ከት ብለን ሳቅን እማና አባም ትንሽ ቆይተው ፊታቸውን እንደጣሉት መጡ ሶሲ እንደ ትልቅ ሰው ረጋ ብላ "ምነው እማይዬ ሰላም አይደለም እንዴ? እ አባ" እያለች በአይኖቿ ከዚያ ከዚህ አገላብጣ ሁለቱንም አየቻቸው ይህን ጊዜ እማ ፊቷን እንዳናየው ራሷን በስራ ለመወጠር ሞከረች አባዬም በዛው ልክ ተረጋግቶ "No ልጆች ሁሉ ሰላም ትንሽ ስራ ቦታ ስሜታዊ ሆነን ነው" አለን እማም "ጎሽ ገላገልከኝ" የምትል ይመስል አንገቷን ቀና አደረገች ሊዱ ዬ ሮጣ አጠገቧ ሽጉጥ አለችና ጭንቅላቷን በእግሮቿ ላይ ዘመም አድርጋ በሚያሳዝን ድምፅ "እውይይይ ውዷ እናቴ ታድያ ምን ችግር አለው እኛ አለንላችሁ አለቻት እማም ልቧ ስፍስፍ ብሎ በላዮ ላይ ጣል ባደረገቻት ስስ ሻርፕ ፊቷን ዞር አድርጋ እንባዋን እየጠራረገች በፈገግታ ተሞልታ "እሰይ የኔ ውሻ በቃ ሌላ ምን እፈልጋለሁ እሰይ!" እያለች ጭምቅ አድርጋ ሳመቻት እኔና ሶሲ ግራ እንደተጋባን አባዬ ከመቀመጫው ብድግ አለና "እንዴ እናንተ ከመች ጀምሮ ነው እኛ ቤት ድብርትና ትካዜ በሉ በሉ ተነሱ እንጂ! ነቃ በሉ ሶሲም እንደኛ አልሆነችኮ!" ብሎ ሳቁን ጀመረው እኛም እየተሳሳቅን ተነስተን ቤት ውስጥ መንጎዳጎድ ጀመርን ሶሲ ልብሷን ልትቀያይር ገባች እማ ዝም ብላ እየገነፈለች ያስቸገረቻትን ጀበና ማከም ቀጠለች እኔና ሊዱ ራት አቀራረብንና በቲቪው ላይ ያለውን መዝሙር ሞቅ አድርጋው ቤቱ በአንዴው ወደዚያ ደስታው ተመለሰ በሁላችንም ውስጥ ሳቅ አለ በአንድ ገበታ ላይ እየበላን ሁሉም ሲያጎርሱን ስናጎርሳቸው ደስ እያለን በፍቅር ምሽታችንን አመሸን። ሶሲ ቶሎ መተኛት ስላለባት እኔና ሊዱ አጅበን አስገብተናት እኛም ወደ ክፍላችን ገብተን ከአልጋው ላይ ጣል ያደረኩትን እኔና ሊዱ ስንሯሯጥ ሰብሬው እስክሪኗ ስንጥቅጥቅ ያለችውን ስልኬን ሳነሳው የኬብሮን እና የሊያ መልዕክት ለጉድ ነበር "ውይይ ሊዱ ሊያ ፅፋልኝ ነበር ሳላየው" አልኳት እሷም ከቁም ሳጥናችን ፊት ለፊት ቆማ "አዎ አንቺ ለኔም ደውላ ነበር ቆይ እንደውልላት" አለችኝና በሀሳቧ ተስማምቼ ደወልን ሊያም በዚያ በሚናፈቀው የቅብጠት ድምጿ "ሄሎ ሊድ ዬ" አለቻት ሊዱም "ወዬ ሊያዬ ይቅርታ ስላላየነው ነው ያላነሳነው" ብላት ንግግሯን በይቅርታ ጀመረች ሊያም ችግር እንደሌለው ግን ዛሬ ሙሉ ቀን ልታገኘን ፈልጋ እንደነበርና ነገ በጣም እንደምትፈልገን መቅረትና ማርፈድ በፍፁም እንደማይቻል አጥብቃ ስታስጠነቅቃት ሊዱም ተስማምታ እንደምንደውልላት ነገረቻት ሁለታችንም ስልካችንን እንደያዝን አልጋችን ውስጥ ገባን ከነቢኒ ጋር ስናወራ ከዳጊ ጋር ቅድም በእሱ ስልክ የተነሳናቸውን ሲልክልን ሊዱ ማስታወሻ እያለች ሳልዘጋጅ አስፈሪና አስቂኝ ፎቶዎችን ስታነሳ በስተመጨረሻ ራሳችንን በሶሲና በአባዬ ተከበን ስልካችን በደረታችን ላይ ተፈንችሮ አገኘነው ሶሲ በጣም ጮክ ብላ "ቡቹ! ኸረ ሜሪ!" እያለች ቀሰቀሰችን አባዬም ከረባቱን ይዞ "እስካሁን አልተነሱም?! አይ ቡቹ ጉድ ሰራሽኝ" እያለ ወጣ ገባ ብሎ ያየናል እኔና ሊዱም ስንነቃ በሁኔታችን እየሳቅን በግድ ተነስተን የወትሮው ሩጫችንን ጀመርን ልክ እንደ ትናንቱ ቁርሳችንን በልተን ሶሲን
ፀልየን ሞቅ አድርገን ሸኘናት እማዬና አባ ፊታቸው ላይ የይምሰል ሳቅ ከወትሮው ለየት ብሎ ይታይባቸዋል ሊዱም ይህን ስላስተዋለች እነሱን እያየች መለስ ብላ በአይኖቿ ምልክት ሰጠችኝ ትንሽ እንደቆየንም እማ ለት ከዕለት ይዛት የምትወጣትን የእጅ ቦርሳ በእጆቿ ያዝ አድርጋ "በሉ በቃ ልጆች ልንወጣ ነው ሰላም ዋሉ እንደውልላችኋለን" አለችን አባዬም ያላጠለቀውን የሱፉን ኮት ነገብ አድርጎ ቀና ብሎ እንኳን ሳያየን አብሯት ወጣ በስራ ያሳበቡትን ንዴት ስላመንን ቦታ ሳንሰጠው ተበታትነው የተዝረከረኩትን ዕቃዎች አነሳሳን ወዲያውም የሊያ ማስጠንቀቂያ ትዝ ሲለን ቶሎ እየተሯሯጥን ልብሳችንን ቀያየርን ፀጉራችንንም ለእጅ በሚከብድ ማበጠሪያ ከመስታወታችን ፊት ለፊት ቆመን በመወራጨት ተስተካከልን የቤቱንም በሮች እንደምንም ዘጋግተን እየተቻኮልን ወጣን ሊዱ "ሜሪ ለነናሆሜ ልደውልዋቸዋ?" አለችኝ እኔም ምን ጥያቄ አለው ብዬ "አዎ አዎ" አልኳትና ደወለችላቸው ሁልጊዜ የምንገናኝበት የእኛና የእነሱ ቤት እኩሌታ ኮብል ላይ ቆም ብለን ጠበቅናቸው። እነሱም ብዙ ሳይቆዩ ከላይ እስከ ታች አምሮባቸው ብቅ አሉ ልክ እንደተያየንም በደስታ ተቃቀፍንና ተያይዘን መንገዳችንን ቀጠልን ሊዱ ችኩል ብላ "እና ሜሪ ለሊያ ደውይላታ መቼስ እንዳላረፈድን ተስፋ አደርጋለሁ" አለችኝ እኔም ስልኬን አውጥቼ ልደውል ስል ናሆሜና ቢኒ በግራ መጋባት መንፈስ ተምታተው ኮስተር ብለው እያዩን ናሆሜ "እንዴ ሊያ ጋር ነው እንዴ የምንሄደው?" ብሎ ጠየቀን ሊዱም ንድድ ብላ በሚያስቅ አስተያየት አይታው "እና የት ነው የምትሄደው?" አለችው ቢኒም ቀበል ብሎ "ቸርች ነዋ! (ፊቱን ወደኔ መልሶ) ደሞ ሜሪ እነ ዳኒ ደጋግመው እየደወሉ ነው" አለን በዚህ ሰዐት ሀሳብ ባቀርብ ጦርነት አስነሳለሁ ብዬ ስላሰብኩ ሁለቱንም ልደግፍ አልቻልኩም ትንሽ ከተጨቃጨቁ በኋላ በስተመጨረሻ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሱ መጀመሪያ ሊያን እናገኛት እና ከዛ ወደ ቸርች መሄድ. በዚህ ተስማምተን ዞር ስንል ሊያ ከምን ጊዜውም በላይ አምሮባት እየተፍለቀለቀች ወደኛ ስትመጣ አየናት ልክ ስታየንም "የኔ ፍቅሮችችችች!!" ብላ ተጠመጠመችብን እኛም እቅፍ አደረግናትና በወሬ ጠምዳን መንገዳችንን ቀጠልን የሚገርመው የት እንደምንሄድ ሳናውቀው ግን አብረናት እየሄድን ነበር ሞቅ ባለ ጨዋታ ላይ እያለን ናሆሜ "ኸረ ሊያ የት እየሄድን ነው?" አላት ሊያም ከልብ በማይጠፋ ፈገግታ ሁላችንንም ዞር ብላ እያየችን "አንድ ጊዜ የት ነው የምትሄጂው? ብላችሁኝ ሰላምና እረፍት ወደማገኝበት ችግሬን ወደምረሳበት ቦታ ብያችሁ ነበር.." አለችን እኛም ትዝ ሲለን "አዎ አዎ እና?" አልናት እሷም ፈገግታዋ ቀጥሎ "እናማ አሁን እዛ ወደሚገባችሁ ቦታ እወስዳችኋለሁ" አለችን ሁላችንም በጣም ደስ ብሎን በጉጉት ምንም ሳናመነታ ተስማምተን ከሊያ ጋር በአዕምሯችን ተስሎ ወደነበረው ወደዚያ ሰላማዊ እና ድንቅ ለኛ ወደሚገባን ቦታ መንገዳችንን አቀናን በጣም ብዙ ባይባልም በዋናው መንገድ ርቀን እንደሄድን ከአንድ ቀጭን ሸለቆ ጋር ደረስን ሊያም "ኑ ኑ" ብላ እያበረታታችን
1.8K views@Maranata, 17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-30 09:28:41 “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።”
  — ኢሳይያስ 41፥10

                      አሜን!

ቀናችሁን የእግዚአብሔር አብሮነት የሚሰማችሁ፤
እግዚአብሔር ከድንጋጤ የሚሰውራችሁ፤
በድካማችሁ የሚያግዛችሁ፤
በጉድለታችሁ የሚረዳችሁ፤
በቀኙ ክንድ ደግፎ የሚይዛችሁ የተወደደ ቀን ያድርግላችሁ!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRIST_TUBE
1.8K viewsቤki , 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 07:08:03
#የማለዳ_ቃል

" የሚመካ ግን በጌታ ይመካ፤ እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።"
-2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10: 17-18

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.2K viewsMeron, edited  04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ