Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 60

2022-07-15 20:19:49
1.7K viewsቤki, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:07:58
ጌታ እየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን መስሎታል ?
Anonymous Quiz
7%
ሀ,በሰናፍንጭ ቅንጣት
3%
ለ,በእርሾ
31%
ሐ,በሙሽራ
59%
መ,ሁሉም
412 voters1.7K viewsmeron, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 19:07:58
እየሱስም ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፥ ርኵስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው፤አንተ ርኵስ መንፈስ፥ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና።ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው። ብዙዎች ነንና ስሜ ____ ነው አለው፥
Anonymous Quiz
11%
ሀ,ዲያቢሎስ
6%
ለ,ሌዋታን
77%
ሐ,ሌጌዎን
6%
መ,መልስ የለም
385 voters1.6K viewsmeron, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 12:30:44 ለምን ተከተላችሁት?

በአንድ ወቅት እየሱስ ክርስቶስን ብዙ ህዝብ ይከተለው ነበር ምክንያቱ ደግሞ እርሱ አምላክ ስለሆነ የጠፉትን በጎች ፍለጋ የመጣ እውነተኛ እረኛ ስለሆነ የሰውን ልጅ ሊያድን ከሲኦል ሊያስመልጥ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ሊጠራ ዙፋኑን ክብሩን ትቶ ከሴት ማህፀን ተወልዶ ለከፋለው ዋጋ አልነበረም!

ታድያ ለምን ተከተሉት ከሆነ ጥያቄያችሁ ይሀው መልሱ
“ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።”
— ዮሐንስ 6፥26
ይከተሉት የነበረው እየሱስ አምስቱን የገብስ እንጀራ እና ሁለቱን ዓሳ አብዝቶ ያንን ሁሉ ህዝብ ስለመገበ በተአምራቱ ተደንቀው ሳይሆን በልተው ስለጠገቡ ነበር የተከተሉት ለምግብ! ከዛስ? አትሉም ምግቡን ሲያጡ ትተውት ሄዱ ከሱ የሚያገኙትን ጥቅማጥቅም ሲያጡ ትተውት ሄዱ

እናንተስ እየሱስን ለምን ተከተላችሁት? ትታችሁትስ ትሄዳላችሁ? የእናንተን መልስ አላውቅም እኔ ግን እንደዚህ እላለሁ

ዮሐንስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶⁸ ስምዖን ጴጥሮስ፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
⁶⁹ እኛስ አንተ ክርስቶስ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ አምነናል አውቀናልም ብሎ መለሰለት።

እኔ የተከተልኩት ለዚህ ነው የህይወት ቃል ስላለው!

ነፃነት ዋቲሮ
ተባረኩ!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
#share #share #share
2.0K viewsቤki, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 06:01:23
#የማለዳ_ቃል

“በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።”
— ዕንባቆም 2፥1

“I will stand upon my watch, and set me upon the tower, and will watch to see what he will say unto me, and what I shall answer when I am reproved.”
— Habakkuk 2፥1

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው

SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.1K viewsቤki, 03:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:44:05 #አዲስ_ነገር

አነጋጋሪ የነበረው የዘማሪ ሳሙኤል አበበ ነገር መፍትሔ ያገኘ ይመስላል....

" ቤተክርስቲያን እና ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ዘማሪ ሳሙኤል አበበ

ሙሉ መረጃውን በAudio ተያይዞል ይመልከቱ።
Audio : 11.0 MB

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
2.6K viewsቤki, edited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:39:22
#አዲስ_ነገር

አነጋጋሪ የነበረው የዘማሪ ሳሙኤል አበበ ነገር መፍትሔ ያገኘ ይመስላል....

" ቤተክርስቲያን እና ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ዘማሪ ሳሙኤል አበበ

ሙሉ መረጃውን በVideo ተያይዞል ይመልከቱ።
Low Quality : 9.5 MB

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
2.5K viewsቤki, edited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:12:21
#አዲስ_ነገር

አነጋጋሪ የነበረው የዘማሪ ሳሙኤል አበበ ነገር መፍትሔ ያገኘ ይመስላል....

" ቤተክርስቲያን እና ህዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ " ዘማሪ ሳሙኤል አበበ

ሙሉ መረጃውን በVideo ተያይዞል ይመልከቱ።
High Quality : 31.9 MB

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
2.4K viewsቤki, edited  17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 20:00:52 በራስ መንገድ
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=2
ክፍል=19
ነፃነት ዋቲሮ

ምሽቱ ነግቶ ከተኛሁበት ስነቃ አልጋ ላይ የነበርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ ሁሌ ከእነሱ ጋር ብተኛ የወጣልኝ ሰነፍ ነበር የምሆነው ብዬ እራሴን እየታዘብኩ ከአልጋዬ ወረድኩ እማዬ ቁርስ እየሰራች ነበር አባዬም እየወጣ ነበር "" ተነሳሽ የኔ ቆንጆ ደህና ዋይልኝ "" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ሄደ "" የእኔ ትንሽዬ ልጅ ለምን ተነሳሽ ተኚ ብርድ ይመታሻል "" አለችኝ "" አይ ቡና አፍልቼ አግዝሻለሁ "" አልኳት "" አይሆንም ግቢና ተኚ ብርዱ ላንቺ ጥሩ አይሆንም "" አለችኝ እኔም እሺ ብዬ ተመልሼ ተኛሁ "" ሰላም ሰላም ለዚህ ቤት "" አለች መቅዲ ነበረች "" መጣሽ የኔ ልጅ "" አለቻት እማዬ "" ሰላም ነው እቴቴ ፀጋስ? "" አለች መቼም የኔ ነገር አይሆንላትም "" ተኝታለች "" አለች "" እስከአሁን! ፈተና ጨርሻለሁ ብላ ነዋ? ""ብላ ወደ እኔ መጣች የለበስኩትን አንሶላ ከላዬ ላይ በአንዴ ብድግ አድርጋ "" ተነሺ እንጂ! "" አለችኝ "" እንዴ ለምን? "" አልኳት ብርድልብሱን መልሼ እየለበስኩ "" ለምን ትላለች እንዴ ትላንት ምን ብዬሽ ነበር?""

አለችኝ "" እሱማ አዎ ግን እኮ ሰአቱ ገና ነው "" አልኳት "" ገና ነው? ሰአቱን አይተሽዋል? "" አለችኝ ስልኳን ወደ እኔ አዙራ አራት ሰአት ሆኗል "" ውይ እኔ እኮ ደመና ሲሆን ሰአቱ ገና ነው ብዬ እኮ ነው "" አልኳት በድንጋጤ ከአልጋዬ ላይ እየወረድኩ "" በቃ ለባብሺ እኔ እቴቴን አናግራታለሁ "" አለችኝ "" መቅዲ! "" አልኳት እሷም እርምጃዋን ገታ አድርጋ ወደ እኔ ዞረች "" አምሮብሻል "" አልኳት "" አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ "" ብላኝ ሄደች እኔም በልቤ እግዚአር ይከተልሽ ብዬ ልብሴ መለባበሴን ቀጠልኩ
"" ፀጋዬ እቴቴ እኮ ተስማማች! "" አለችኝ ፊቷ በደስታ አብርቶ "" እኔ አላምንም! ወይኔ "" ብዬ በደስታ አቀፍኳት "" እና ምን ትጠብቂያለሽ አለባብሻት እንጂ "" አለችኝ እሺ ብዬ ሄድኩኝ "" እማ ይሄን ብትለብሺ በጣም ያምራል "" እያልኩ የምመርጥላትን ልብሶች በሙሉ አሻፈረኝ እያለችኝ በልመና አለበስኳት እውነት ለመናገር እማዬን ችግር አጎሳቁላሏት እንጂ በእድሜ ገና ናት በዛ ላይ ቆንጅዬ


"" አሁን እኔ እንደ ሀያ አመት ወጣት እንደዚህ ለብሼ ልውጣ አንቺን አድርሼ "" አለችኝ "" አረ እቴቴ በጣም ነው የሚያምርብሽ "" አለቻት መቅዲ ስንወጣ በር ላይ መኪና ቆሟል "" ጭራሽ መኪናም ይዘሽ ነው የመጣሽው ሀብታም..."" አላስጨረሰችኝም "" አፍሽን ዝጊ ስታናድድ "" ብላ እማዬን አስገብታ እሷም መኪና ውስጥ ገባች "" ጊቢ እንጂ እንደ ዮፍታ በሩን ከፍቼ እስካስገባሽ እየጠበቅሽ ባልሆነ "" አለችኝ አሽሙር መሆኑ ነው እየሳቅኩ ገባሁ የሚያምር ሆቴል ይዛን ገብታ ጋበዘችን እስካስአትውጡ አትውጡ ያስብላል ከግብዣው በኋላ እማዬን ለምነናት ፎቶ ቤት ሄድን ለትውስታ የሚሆኑ ፎቶዎችን በዛ አድርገን ተነስተን ወደ ቤት ተመለስን

እኔ እና መቅዲ ተያይዘን በዛው ቸርች ሄድን እሁድ አገልግሎት የእኛ ስለሆነ ከወትሮ በተለየ ሳምንቱን ሙሉ የመዝሙር ጥናታችንን እናደርጋለን አቤል ከእኛ ጋር አንድ ኳየር ባይሆንም ቸርች ሲመጣ የውስጡ ሰላም ስለሚበዛለት አይቀርም አሁን ደግሞ በጣም ደስ የሚያሰኘው እና ሁሌ ሳስበው ነብሴ ሀሴት የምታደርግበት ነገር ቢኖር የቲና ጌታን መቀበል እንዲሁም ቸርች አዘውትራ መምጣቷ ነው ከኳየር መልስ ናቲ እና መቅዲ እየተነጋሩ ነው እኔም ደግሞ ከአቤል እና ከቲና ጋር እያወራሁ ነበር በመሀል ለአቤል ተደወለለት እና ተሰናብቶን ሄደ "" ፀጋ! "" አለችኝ ቲና ነበረች ልቤ ሲቀደድ እየታወቀኝ ነበር "" አቤት ቲና "" አልኳት ጌታን በመቀበሏጓደኛሞች በማህበረሰቡ በበፊት ጓደኞቿ እየደረሰባት ያለውን ተፅዕኖ ነገረችኝ "" አንቺ እና መቅዲ በጣም የምታስቀኑ ናችሁ እኔ ደግሞ አሁን በዚህ ሰአት ማንም ከጎኔ የለም ጓደኛችሁ መሆን እችላለሁ? "" አለችኝ "" አይእንጂ ተሳስተሻል ጓደኛሞች ሳንሆን እህትማማች ነን እኔ እና መቅዲ ጋር ጓደኛ የሚባል ነገር አይሰራም እህት እንጂ ስለዚህ አንቺም ብትሆኚ እህታችን እንጂ ጓደኛችን ልትሆኚ አትችይም "" አልኳተለቀቀ በጣም አመሰግናለሁ "" ብላ አቀፈችኝ

ከአንድ ወር በኋላ ውጤት ተለቀቀ ሁላችንም በጠዋቱ በጠዋቱ ተደዋውለን ለማየት ወደ ትምህርት ቤት ሄድን....ይቀጥላል

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
#share #share #share #share
2.4K viewsNetsi, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:10:42 ኢየሱስ ያለህበት
ሰላሜ ያለበት
አንተ የዋልክበት
ደስታዬ ያለበት
አንተ የከበርክበት
ስኬቴ ያለበት
የተጠራህበት
መድሀኒቴ ያለበት

ነፍሴ የምትወድህ ሆይ
ሁሉም ይቅርና አንተ ዋል ከበቴ
ነፍሴ የምትናፍቅህ ሆይ
ሌላው ይቅርና ብቻ ዋል ከቤቴ
የምፈልገው አንተን ነው
ሁሌ ምመኘው አንተን ነው
እኔ ሚመቸኝ ቤትህ ነው
ምታስፈልገኝ አንተ ነህ
.
__
#ነፍሴ_የምትወድህ
ዘማሪት ፍሬህይወት አበባው

ⓈⒽⒶⓇⒺ ⓃⓄⓌ
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
2.5K viewsቤki, edited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ