2022-09-23 11:31:56
ዝቅ በል!ሁሉም ስኬት ውጣ ውረድ ቢበዛበትም እስከመጨረሻው ድረስ የማይነቃነቅ መሠረት በሁሉም ዘንድ ሊኖር የሚገባ ጉዳይ ነው።
አንድ ቤት ሲሰራ መሠረት ይኖረዋል ቤቱን የሚወስነው መሠረቱ ነው በጣም ወደታች ከተቆፈረ የቤቱ ይዘት ና ከፍታ እየጨመረ መምጣት ይጠበቅበታል አለበለዚያ ግን ለግራውንድ ቤት በጥልቀት መቆፈር አያስፈልግም ምክኒያቱም የመሸከም አቅሙ ዝቅተኛ ስለሆነ ማለት ነው።
ስለዚህ እኛም በህይወታችን በጣም ዝቅ ካልን እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያደርገናል ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነው።
እግዚአብሔር አምላክ እየሱስን ያለ ልክ ከፍ ከፍ ያደረገው ያለ ልክ ዝቅ ዝቅ ስላለ ነው።
- ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2
7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥
8 በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤"
ይህ ማለት አምላክ ሆኖ ሳለ ወደ ምድር ወይም ወደ ሰው ልጆች በመጣ ጊዜ መለኮታዊ መብቶችን ትቶ የሰውን ልጅ ቅጣት በሰው (በእኔ ,በአንተ) ሁኔታ ለመቀበል ሲባል የራሱን ክብር በፈቃደኝነት አውልቆታል አየህ ከእየሱስ ምን እንማራለን የቱንም ያህል ክብር ቢኖርህ ፣ዝና ፣ሀብት የምትላቸው ነገሮች ቢኖርህም ዝቅ ብለህ ለሌላው ካልተገዛህ ክብርህን ይዘህ በእግዚአብሔር ሳትከበር ስፍራህን ሳታገኝ ትኖራለህ ።"
በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥"
(የማርቆስ ወንጌል 10: 43) ስለዚህም ለሌሎች ዝቅ ብለን የከፍታን ስኬትን እንወርሳለን።
# ዝቅታ አለማወቅ አይደለም
# ዝቅታ ትንሽነት አይደለም
# ዝቅታ የበታች መሆን አይደለም
# ዝቅታ ከፍታን የሚያመጣ ትልቅ መሳሪያ ነው
" ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 23: 12)
Meron
ተባረኩ!
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.6K viewsmeron, edited 08:31