Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-18 14:28:03 #Spiritual_speech
❝ እያንዳንዱ ቀን ጠቃሚ ዕለት ነው እያንዳንዱ ሰኮንድ ደግሞ ባህርይ ስር የሰደደ እንዲሆን ፍቅርን እንድትገልጥ ወይም በእግዚአብሔር ላይ እንድትደገፍ የሚያደርግ ዕድል ነው አንዳንድ ፈተና ከባድ ሲመስሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ልብ የማትላቸው ናቸው ሁሉም ግን ዘለዓለማዊ አንድምታ አላቸው! ❝
ፓስተር ሪክ ዋረን

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
➥ @CHRIST_TUBE
➥@CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.2K viewsMeron, edited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 06:55:27
#የማለዳ_ቃል

" ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።"
-1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10: 13

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.2K viewsMeron, edited  03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 20:00:09 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=52
ሳባ ካሳሁን

ልቤ ለሁለት ተተረተረ የምሳሳላት ቡቻዬ በእነዚያ አስፈሪ ልጆች ተከባ ሳያት የምገባበት ጠፋኝ በጣም እየተቃረቧት መጡ ይህን ጊዜ እየተርበተበትኩ "ሊዱዱዱ!!" ብዬ ወደሷ መሮጥ ጀመርኩ ሊዱዬ ባለችበት እንደደረቀች ነው ሶስቱም ዙሪያዋት ሊከቧት ሲሉ ከመካከላቸው የአንዱ ስልክ ጠራ ትንሽ ቆይቶም አነሳውና እሱ ምንም ድምፅ ሳያወጣ የደዋዩን ቃል ብቻ አዳምጦ ወደ ኋላው አፈገፈገ የከበቡት ጓደኞቹንም እንዲመለሱ ምልክት ሰጣቸው እንዴት እንደሮጥኩ ስልኬንና ካርዱን የት እንደጣልኩ ባላውቅም ብቻ ተወርውሬ ሊዱን ሸፈንኳት በጣም ፈርታ ስለነበር እሷም ጥብቅ አድርጋ ይዛኝ እምባዋን ወደ ውስጥ ትምገዋለች። ታድያ ይህን ጊዜ ሰውዬው ወደኔ ቀረብ አለና "Sorry Sorry ጀለሶች በስህተት ነው" ብሎ በጫት የላሸቀ ጥርሱን እያሳየን እጅግ አስፈሪ በሆነ አስተያየት አይቶን ሄደ የአፉ ሽታ ራስ ያስት ስለነበር መስሎ የታየኝ ሰው ማሳቀቅ ጀብድ አድርገው ከሚያስቡት ከእነሱ ልክ እንደ አንዱ ስራ ፈቶ ሲጠጣና ሲቅብ ያደረ ሰው ነው ቆም ብዬ ማስተዋሉን ትቼ ሊዱዬን እቅፍ አደረኳት እሷም ሽጉጥ አለችብኝና "በቃ ሜሪዬ አሁን እኮ ሄደዋል ደግሞ ተሳስተው ነው አስጨነኩሽ አይደል?" ብላ በስስ አንደበቷ በውብ ዐይኖቿ እየተቁለጨለጨች አየችኝ እኔ ግን ደንግጬ ስለነበር ከእምባ በስተቀር የውስጤን ምገልፅበት ይሄ ነው ብዬ ማወራው ቃል አጠረኝ "ሊዱዬን አንድ ነገር አድርገዋት ቢሆንስ ምን እሆን ነበር? እንዴ ብርሀኔን? የታናሽ ታላቄን? አይይይ በቃ ህይወት እንዲህ ናት ማለት ነው? ህይወትም ልክ እንደ ቤተሰቦቻችን ተለዋዋጭ?" እያልኩ በተደበላለቀ ስሜት ተረበሽኩ ሊዱዬ ቀስ ብላ ከአንድ ታስቦ የተዘጋጀ ይመስል ምቹ በሆነ ድንጋይ ላይ አስቀመጠችኝና ወዲያና ወዲህ የበታተንኩትን ተሰባብሮ አገልግሎቱን ሊያቆም ቀናቶች የቀሩትን ስልኬን ከጣልኳት ብጫቂ ካርድ ጋር ይዛ መጣች ከእግሬ ስርም በርከክ አለችና እምባዬን በለስላሳ እጆቿ እየጠራረገችልኝ "አይ ሜሪዬ እንዲህ በቀላሉ እጅ ትሰጫለሽ?" ብላ እኔ እንድረጋጋላት ስትል ብቻ ስሜቷን ከኔ እየደበቀች ፈገግ አለችልኝ እኔም ሳቅ አልኩና "ምን ነካሽ ቡቹ ስለት እኮ ይዘው ነበር!" አልኳት ታድያ ይህን ጊዜ ሀገር በሚያውቀው ፍልቅልቅነቷ ዲምፕሎቿን ብቅ አድርጋቸው በቅብጠት ተሞልታ "እሱማ ልክ ነሽ ያስደነግጣል እኔምኮ ፈርቼ ነበር ግን አልፏል ለዛ ነው ደሞኮ በስለቱ ገፋ ቢል ቢወጉኝ ነው ከዛ በጣም እድለ ቢስ ከሆንኩ ደሞ ብሞ..." ስትል አላስጨረስኳትም እንዲህ ስትለኝ
ከሰውነቴ አንዱ ክፍሌ የወለቀ ያህል አሳመመኝ ስሰማት ልክ እንደ እብድ አክለፈለፈኝ ብቻ ተስፈንጥሬ ተነስቼ እጇን በእጄ ጥብቅ አድርጌ ያዝኩና "ቡቹ!! በቃ ዝም በይ!! ነይ ነይ በቃ እንሂድ! ያምሻል እንዴ? ህፃን! ነይ!" እያልኩ ሳይታወቀኝ እጎትታት ጀመር።

ቡቻዬ በሁኔታዬ ይባስ እየሳቀችብኝ "እሺ!እሺ ሜሪዬ በቃ አይላመደኝም በናትሽ እጄን አሳመምሽኝ" ብላ አንጀቴን በላችው እኔም ቆም አልኩና "ሊዱ ድጋሚ ተሳስተሽም ቢሆን እንዲህ አይነት ወሬ እንዳታወሪልኝ የእውነቴን ነው እንጣላለን!" አልኳት ይህን ጊዜ ቡቻዬ ቀረብ አለችኝና ፊቴን በእጆቿ ያዝ አድርጋኝ "አይ ሜሪዬ ታድያ መሞቴ እንደው አይቀርም ሞት እኮ ረፍት ነው ከዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ አስጠሊታ ትግል እንደሆነ ግልግል ነው ደሞ ልጅ እያለን ልባቸው አንድ የሆኑ ሰዎች ነብሳቸው አብረው ያርፋል ትይኝ አልነበር? እመኝኝ ደግሞ እኔ አልሞትብሽም እሺ!" አለችኝ የምታወራኝ ከልቧ ነበር የኔ ዐይኖች በእምባ ተሞልተው ፊቴን አርሰውታል ልቤ ቡቹን ማጣትን ፍፁም ሊቀበል እንደማይችል ሳላሰበው ቀድሜያት መሞት እንዳለብኝ አስባለሁ ሊዱዬ መሀል ላይ ፍዝዝ ብላ ታየኛለች ከዛ እንዳየኋት ስታውቅ ሌላ ዐለም ውስጥ ገብታ እኔ እንዳልጨነቅ ትስቅልኛለች እንዲህ ስትለኝ ተይ አትተይ በቃ አይብቃሽ ለማለት ቃል አጠረኝ አንደበቴ ተሳስሮብኝ ዞር ብዬ ከሩቅ ሳይ ቢኒና ናሆሜ ህፃንነታቸው ያለቀቃቸው ይመስል እየተሯሯጡ እየመጡ ነው ያለኝ አማራጭ ነገሩን ሁሉ መርሳት ስለነበር መምጣታቸውን ለሊዱ ልነግራት ስል ለካስ ቀድማ አይታቸዋለች ጠጋ አለችኝና "አደራ ሜሪዬ የተፈጠረውን እንዳትነግሪያቸው ደሞ በተራ ነገር እነሱን ማስጨነቅ ነው የሚሆንብን" አለችኝ እኔም ቀድሜ ስላሰብኩት በአንድ አፍ ተስማምቼ እምባዬን እየጠራረኩ ልቤ ሳይፈልግ ፊቴ እየሳቀ እንደሆን ለማስመሰል ሞከርኩ ድክም ብሏቸው እያለከለኩ እቅፍ አድርገው ሰላም አሉን ቢኒ ትክ ብሎ አየኝና "ምነው ሜሪዬ ፊትሽ ልክ አይደለም" አለኝ ወዲያው ቀና ብዬ ሊዱን ሳያት እንዳልነግራቸው አንገቷን እየነቀነቀች ምልክት ሰጠችኝ እንደምንም ፈታ ለማለት እየሞከርኩ "አይ ቢኒዬ ምንም አልሆንኩ ባክህ ዝም ብሎ ደብሮኝ ነው" አልኩት ናሆሜ ድንገት ጮክ አለና "እንዴ የምን ድብርት!! ኸረ ነይ ሜሪ መሮጥ ነው ያለብሽ" እያለ እጄን ይዞ በፍጥነት ወደ ፊት ያስሮጠኝ ጀመር ቢኒና ሊዱም ተያይዘው እኛ ጋር ለመድረስ ሲሮጡ እኛ እንዳይደርሱብን ስንታገል ከልባችን እየሳቅን በደስታ ቦርቀን ተያይዘን ወደዚያ ስፍራ ደረስን ሁሌ የሚዘጋው በር ከበፊቱ በሚለይ መልኩ ገርበብ ብሎ ተከፍቷል እኛም በሁኔታው እየተገረምን ወደ ውስጥ ገባን ስንገባ ግን ከወትሮው ፍፁም ተለይቶ ቤት ውስጥ አንድም ሰው የለም ሊዱዬ ከሁላችንም ግራ ተጋብታ በቀስታ "ሊ..ያ ኬ...ብሮን" እያለች መጣራት ጀመረች እኛም ዕርስ በዕርስ እየተያየን ሳለ የገባንበት በር ከውጪ ሲቀረቀር ሰማን ይህን ጊዜ ድንጋጤያችን ጨመረ ሊዱ የሸሚዜን ጫፍ ጥብቅ አድርጋ ያዘችው ቢኒም ፍርሀታችን እንዲቀንስ መሀላችን ገብቶ ቆም አለ አሁንም በድጋሚ በቤቱ ውስጥ በርተው የነበሩት አምፓሎች በቅፅበት ጠፉ ከቤቱ መጥበብ የተነሳ የሚታየው ጭላንጭል ብርሀን በበሩ ቀዳዳ የሚገባው ብቻ ነበር እርሱንም ማንነቱን የማናውቀው ሰው ከውጪ ግጥም አድርጎ ጠቀጠቀው ጭራሽም ድቅድቅ ጨለማ ሆነ ይባስ ልብ ምታችን ጨመረ ከመደንገጥ ብዛት መቆም እያቃተን ሳለ ድንገት የሆነ ሰው ከኋላዬ መጥቶ በሀይል አነቀኝ ነፍሴ ከስጋዬ የተለየ እስኪመስለኝ ደንግጬ ልጮህ ስል አፌን ጥብቅ አድርጎ ያዘኝ እጆቼን ሳወራጭ ሊዱዬ ናሆሜና ቢኒ አጠገቤ የሉም. . .
. . . ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.7K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-15 07:06:37
#የማለዳ_ቃል

“የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤”
  — ኤፌሶን 5፥9-10

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
2.5K viewsቤki , edited  04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 20:00:32 ከዚያ አስፈሪ ሸለቆ እንደደረስንም "ቡቹዬ ቆይ ካርድ ልግዛ" ብያት ተገነጠልኩ እሷም በፈገግታ "እሺ ሜሪዬ እየሄድኩ እጠብቅሻለሁ" ብላኝ ልክ እንደ ህፃን ልጅ እየቦረቀች ሄደች ገዝቼ ስመለስ ግን ማንነታቸውን ያላወኳቸው ሶስት በጣም አስፈሪ እጅግ ግዙፍ የሆኑ ሰዎች ወደሷ ሲቀርቡ አየሁ ድንግጥ ብዬ ልሄድላት ስል እሷ ከኔ እየራቀች እነሱ እየቀረቧት ፍፁም ያልጠበኩትን ነገር አየሁ ከመካከላቸው አንዱ በግራ ወገቡ በኩል ስለት ያለው ጩቤ ይዟል ልቤ ለሁለት ተተረተረ
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
2.6K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-13 20:00:32 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=51
ሳባ ካሳሁን

በመንገዳችን ላይ ብዙ የቤተክርስትያናችንን ወጣቶች እነ ኤልሻዳይን ጭምር ብናገኛቸውም ከየት መጣ በሚባል ሁኔታ እየደበረን ስናወራቸው ቆይተን ኤልሻዳይና ዳኒ ካለን ቅርበት አንፃር ሁኔታችን ግር ብሏቸው ትንሽ ካወሩን በኋላ "ቆይ ግን ምን ሆናችሁ ነው? ይህን ሰሞን እኮ አይተናችሁ አናውቅም በዛ ላይ ከአገልግሎትም ርቃችኋል" አለችን ታድያ ይህን ጊዜ "ኡፍፍ ጀመረች ደሞ" ብለን በመሰላቸት ዐይናችንን ከወዲያ ወዲህ ጣል እያደረግን ትንሽ ከተቅበዘበዝን በኋላ ቢኒ ቶሎ እንድንገላገላቸው በማሰብ "አዎ ሰሞኑን እኮ መካነ-ኢየሱስ አዲስ የተጀመረውን የክረምት ትምህርት መከታተል ጀምረን ነው እንጂማ አንጠፋም ነበር ደሞ ከሜሪ ጋር ብዙ ጊዜ ስንመጣ እናንተ አትኖሩም ያው እየተላለፍን ይሆናል" ብሎ በሚደብር ሙሉውን ውሸት እንደሆነ በሚያስታውቅበት ማልገጥ አወራቸው። የሚገርመው ነገር ግን እነ ኤልሹ ከልባቸው አመኑን ምክንያቱ ደግሞ የእኛ መታወቂያችን ስለኛ ብዙ መከራና ስቃይን አይቶ እርሱ ዝቅ ብሎ ለኛ ሲል የተዋረደው የፍቅር አምላክ ክርስቶስ በሁሉም ነገር ውስጥ ያስተማረንን *ሀቅ ፍቅር ትህትና መልካምነት* ወትሮው እንደነበር ዛሬ እንደከዳነው አላወቁም አሁን ላይ ልክ አይኑን በጨርቅ እንደታሰረ ሰው ከፊታችን ያለውን እሳት እንፋሎቱ ልቦናችንን እየታወቀው ስንገባበትም እንደሚያቃጥለን እያስጠነቀቀን ዝም ብሎ በሌላ ዐለም መጓዝን መርጠናል ከነዳኒ ጋር እንደቆምን በተደጋጋሚ የእነ ሊያ የስልክ ደውል ሰላማችንን ነሳን ልባችንን አንጠልጥሎት የምንወዳቸውና አብረናቸው ያደግን በጌታ ቤት ፀንተው ያሉት እህትና ወንድማችን የሚያጋሩንን ሰማይና ምድርን ያፀና ወጀብ ማዕበሉን ፀጥ ያደረገን ሀይል ስለዚያ ቃል በሚያወሩት ሁሉ ሲያካፍሉን ልባችን እየታወቀው አዕምሮና ስሜታችን ግን አቀለለብን ክርስትናችንን ልክ እንደ ልማድ ማየቱን አለማመደን አላስችል ያለው ናሆም በስሜቱ ተገፋፍቶ በውሸት ሳቅ ተሞልቶ "...እ... በቃ ኤልሹዬ እነ ፋዘር እዛ እየጠበቁን ስለሆነ እናናግራቸው በኋላ እንገናኛለን" ብሎ ከአፋቸው የያዙትን እንኳ እስኪጨርሱ ሳይጠብቅ እንድንሄድ ገፋፋን እኔና ቢኒም እንደሰማነው ሳቅ ፈገግ ብለን ከነበረን ድብርት ቶሎ ነቃን ሊዱዬ ግን ወደኋላ ዳግም ሌላ ትግል ውስጥ እንደሆነች ታስታውቃለች የሚያወሩትን፣ የሚነግሩንን፣ የምናውቀውን፣ የቀመስነውን፣ ያደግንበትንና የኖርንበትን ሁሉ ከሁኔታችን ጋር ስታስተያየው ሌላ ራሱን የቻለ እኛ በብዙ ያለፍንበትን ትግል ልክ እንደ አዲስ ትጀምረዋለች። ናሆም ስላቋረጣቸው ድንግጥ ብላ ዝም እንዲል ቆንጠጥ አደረገችው እሱ ግን ትግሉን ጨርሶ መደምደሙ ላይ ስለደረሰ ምንም ሳይሰማው ጠጋ ብሏት በቀስታ "ታድያ እዚህ ቆመን ስንት የሰለቸንን ስብከት ይጀምራሉ እንዴ?" አላት አሁንም ቡቻ ዬ ነገሩ አስደንግጧት ቀና ብላ አየችውና ከልቧ አፈረች ኤልሹና ዳኒም በፈገግታ ተሞልተው "እሺ! እሺ! በቃ ሂዱ አናስቁማችሁ የምትወዱትና የመረጣችሁ ጌታ በሄዳችሁበት ሁሉ ይከተላችሁ!" አሉን እኛም ተያይዘን በፍጥነት ከቦታው ለመራቅ አሁንም ተስፋ የቆረጥንባቸው የእኛ ጥፋት ትክክልነትና ዘመናዊነት መስሎን እነሱን ክፉ ያደረግናቸው ቤተሰቦቻችን በቦታው መገኘታችንን እንዲያዩ እነሱ በቆሙበት ሁሉ እየተንጎራደድን በደንብ እንዳዩን ካስተዋልን በኋላ ወደዚያ እረፍት እናገኝበታለን ወደምንለው ቦታ ጉዟችንን ቀጠልን በተደጋጋሚ ግን መጣ ሄድ ደሞ መለስ እያለ ቅድም ኤልሻዳይ የተናገረችው ነገር እረፍት አሳጣኝ "የመረጠን ጌታ??...እ!.. በሄዳችሁበት ይከተላችሁ!? ምን ለማለት ፈልጋ ነው?...አይይ ዝም ብዬ እንጂ ይሄኮ normal ነገር ነው" ብዬ ራሴን በራሴ እየሸነገልኩ በዝምታ ተዋጥኩ ከሊዱ በስተቀር ሁላችንም ልክ የፈረስ ጋሪ ይመስል ውብ አድርገን ፊት ለፊታችን ያስቀመጥነውን እሳትማ አለም ብቻ እያየን ኋላችንን የመጣንበትን ሳናስተውል ያለፍንበትን ሳናገናዝብ ክብራችንን ጥለን የማይመጥነንን እያሳደድን ነው ሊዱ ዬ ግን በምንሄድበት ሁሉ ቆም ትልና ለማሰብ ትሞክራለች ታድያ ይህን ጊዜ ስናፈጥባት አፍራን መንገዷን ትቀጥላለች ሰሞኑን በተደጋጋሚ እንድንመለስ መወስወሷን አልተወችም በዚህ ሰዐት ቢኒ "ያልተነካ ግልግል ያቃል" ብሎ የሚሰማትን በነፃነት እዳታዋየን ፋታ ይነሳታል ይባስ እኔና ናሆምም እየተነጫነጭንና ዝም እንድትል እየተቆጣናት እንደ ታላቅ ማስተዋል ሲገባን "አንቺ አልገባሽም!" እያልን ወደ እሳቱ እንገፋፋታለን። ያንን አስጠሊታ በከተማይቱ ላይ መሆናችንን እስክንጠራጠር ድረስ ፍፁም አስፈሪውን ሌቦችና ወንበዴዎች ተብለው የሚጠሩ ብቻ የሚንቀሳቀሱበትን ሸለቆና ጉራንጉር ካለፍን በኋላ ከዚያ ከተዘጋው ዐለማችን ደረስን ያ ሁሉ መንቀጥቀጣችን ፈራ ተባ ማለቱ ቀርቶ ዛሬ እንደ ቤታችን ከፍተነው ገባን
እንዳስለመዱን እነዚያ የፍቅር ልጆች ሁሉም ቅልጥ ባለ ጩኸትና ቅላፄ ባለው ፉጨታቸው በደስታ ተቀበሉን እኛም ከልባችን ደስስስ እያለን እቅፍ አድርገን ሰላም አልናቸው ቤቱ ሁሉ በደስታ ተሞላ ልክ እንደ ትልቅ ሰው አክብረውን መቀመጫቸውን ለቀቁልን እኛም "እንዲህ ያለ ፍቅር ከየት ይገኛል?" እያልን ተቀመጥን ትንሽ ከተጨዋወትን በኋላ ሊያ በተደጋጋሚ ስልክ ሲደውሉ ለምን እንዳላነሳን ጠየቀችን እኛም ከዚያ ሁሉ ሳቅ መለስ አልንና የተፈጠረውን ሁሉ ምንም ሳናስቀር ነገርናቸው በደንብ ካደመጡን በኋላ ሊያ ሳቅ አለችና "አይይ ጓደኞች እዚህ ያለነው ሁሉ ቤተሰቦቻችን የሚፈልጉን ይመስላችኋል?" እንደዚያ ካሰባችሁ ትልቅ ስህተት ነው ለወትሮው ቤተሰቦቻችን ፍፁም ሰላማዊና የእኛን ደስታ ብቻ ፈላጊ ቢሆኑም ከጊዜ ጊዜያት ግን ጭራሹን እያስጠላናቸው ሲመጣ ምንም ሳያመነቱ ከቤታቸው አባረሩን ታድያ የእናንተ ምን ይገርማል?" አለችን እንዲህ ስትለን ደንገጥ ብዬ "አያይ እነ አባዬ ምንም ጨካኝ ቢሆኑም እንደዚህማ አያደርጉም" ብዬ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ነገሩ በሊያ አላበቃም ሁሉም አንድ በአንድ ታሪካቸውን ሲያወሩን ቤተሰብ የሚባል ነገር ፍፁም እንድጠላ ሊያደርግ የሚችል ሌላ ራሱን የቻለ ትግል ፈጠረብን ብዙ ነገር ካጫወቱን በኋላ በዐይናችን ስር እምባ ሲሞላ በኮልታፋነቱ የሚታወቀው ሱራፌል እምባውን እየጠራረገ "በቃ በቃ በናታችሁ አታስለቅሱኝ ምንድነው ድብርት በቃ ከዢህ ሙድ እንውጣ" ብሎ በሚጣፍጥ ንግግሩ ለመነን እኛም ከዚያ አስጠሊታ ሀዘን ለመውጣት ተስማምተን የምናወራውን ወሬ ቀየርን ርዕሳችን የጭፈራ ቤት ሙድ የምርቃና ጣዕምና የማበድ ጥግ የሚሉ እኛን መመጠን አይደለም ለአፋችን የማይገቡ ነገሮችን እያወራን በደስታ ተሞላን ቀን ከቀን ውሏችን እንዲህ መሆኑን ተለመደ ጠዋት ተነስተን ከቁርስ በኋላ እነ ሊያ ጋር እንሄዳለን እንደፈለግን ከሆንን በኋላ ቤት ሄደን ምሳ ሰዐት ሲያልፍ ከእነሱ ጋር ከተማ ከተማውን እንዞራለን እንዲህ እንዲህ እያለ ክረምቱ ተጋመሰ ዛሬም እንደሰሞኑን ደውለውልን ልንሄድ ሊዱ በተደጋጋሚ ለነቢኒ እንንገራቸው ስትለኝ እኔ እንደምንሄድ ስለሚያውቁ ይመጣሉ ብያት ብቻችንን ከቤት ወጣን
2.3K views@Maranata, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 13:34:02 አጭር ፀሎት!!!

አብረው ይጸልዩ

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
193 viewsMeron, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 08:12:52
#የማለዳ_ቃል

" ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።"
-1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3: 23

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
576 viewsMeron, edited  05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 19:59:47 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=48
ሳባ ካሳሁን

ከመጠጣት አልፎ መቃምን ከመቃምም አልፎ ማጨስን እየተለማመድነውን መጣን ከብዙ ትግል በኋላ ለጠላት እጅ ወደመስጠት፣ከዘላለማዊ ደስታ ወደ አለማዊ አስፈሪ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መውደቅን ፍፁም ሰላም ከምናገኝበት የቤተክርስትያን አገልግሎት ወደ አዲሱ የፍቅር መንደር መመላለስን አዘወተርን። በዚህ ሰዐት ልባቸው ውስጥ የሚመላለሰውን ድምፅ እየገፉ ራሳቸውን ግን በአለም ደስታ ሊሸፍኑ የሚፈልጉ ሌላ ልጆች ሆነናል። ዛሬ ሌላ አዲስ ቀን ነው እኔና ሊዱ በተኛንበት ሰዐቱ ሳይታወቀን መጋረጃችንን አልፋ ውቧ ፀሀይ ክፍላችንን በብርሀኗ አድምቃ መንጋቱን አበሰረችን እኔና ሊዱም እየተቀላለድን በደስታ ተሞልተን ከአልጋችን ወረድን ለወትሮው መንጋቱን ስናውቅ አንገታችንን ደፍተን ልዑል አምላካችንን ሰላም ስለመንጋቱ እንዳላመሰገንን ዛሬ ሁለታችንም እየታቻኮልን ከትራሳችን ጀርባ የምንጠብቀውን የስልክ ጥሪ እንደተደወለ ስናይ ኬብሮንና ሊያ ተደጋጋሚ ጊዜ ደውለውልናል ይህን ጊዜ ራሳችንን ማወቅ እስኪከብደን ልክ የሎተሪይ ዕድል እንደደረሰው ሰው "Yes!! Yes"" እያልን በደስታ ፈነጠዝን
እዚህ ጋር ያስደሰተን ሄደን የምንጠጣውና እንደ አንዲት ፍየል ይመስል ከአንድም ሁለት ቀን የበላነው የቅጠል አለም አልነበረም።

*ያ የምንሄድበት ራሳችንን አገኘንበት ብለን ያሰብነው የእውነተኛ ፍቅር ዕርስበዕርስ መከባበር ነፃነት ያለው በዘመኑ ሊገኝ የማይቻል ከልብ ሊጠፋ አይደለም በታሪክ ሊነገር የሚገባው ብለን ያሰብነው የጓደኝነት አለምን ነበር።

ሊዱዬ ከልቧ ተደስታ ከዐይን ሊጠፋ በማይችል በሳቀች ቁጥር በጉንጮቿ ላይ ስርጉድ ብለው በሚወጡት ዲምፕሎቿ ተሞልታ "Yess!! ሜሪዬ እንሄዳለን ማለት ነዋ?" አለችኝ እኔም ደስታዋን ሳይ ከልቤ እየተደሰትኩ "አዎ አዎ የኔ ውድ እንሄዳለን" ብዬ ልክ እንደ ህፃን ልጅ መቦረቅ ጀመርኩ። በቤት ውስጥ ያለው የተለመደው ድባብ አለ አባዬ እንደ ሁሌው ዛሬም በጠዋት ተነስቶ ከረባቱን በእጁ አንጠልጥሎ ሊዱን ጥበቃ ከሳሎን መኝታ ቤት ከመኝታ ቤት ሳሎን ይሯሯጣል እማም ሰለቸኝ ታከተኝ ሳትል እኛን የምትጦር ይመስል በቤት ውስጥ ያለውን ስራ ሙሉ ሰርታ በጠረጴዛው ላይ ከሩቅ የሚጣራውን ማዕዷን አቀራርባለች የእሱ ሲገርም የሀገራችን ሰዎች "የዶሮ ዐይን የመሰለ!!" ብለው የሚያሞካሹትን አይነት ቡና ፏ አድርጋ እያፈላች ነው። ሶሲዬ የአባዬን እምነት ትደግፋለች እሷም በጠዋቱ ተነስታ በራሷ ስራ ተጠምዳለች እኔና ቡቹም ክፍላችንን ካስተካከልን በኋላ ፊታችንን ለመታጠብ ገብተን ያጠለቅናት ስስ ነጠላ ጫማ እያሟለጨችን ተጣጥበን ወጣን አባዬ ልክ ሊዱን ሲያያት በቁም ነገር ኮስተር ብሎ ለሚያየው ሰው ግን በሚያስቅ ሁኔታ ሆኖ "ጎሽ!! ጎሽ!! ተነሳሽ? በይ ነይ ነይ እሰሪልኝ!" ብሎ እየተክለፈለፈ ሊዱ በጣም የምትወደውን ከረባት በእጇ አስያዛት። ሊዱዬም ምኗ ሞኝ ነው እንደቸኮለና ምንም አማራጭ እንደሌለው ስለምታውቅ ባላየ ባልሰማ ሆና እሱን ለማናደድ ሞከረች ያሰበችውም ተሳካላት አባዬም እየተቁለጨለጨ ባስ ስትልበት ኮስተር እያለ እኔና እማ እንባችን እስኪወጣ ስንስቅባቸው ሶሲ ስታገላግል ቤቱ እንደ ሁሌው በደስታ ተሞላ በስተመጨረሻ አባዬ ድክም ሲለው ቡቻ ዬንም ከኮሊደር ኮሊደር ማሳደድ ትንፋሹን ሲያሳጥረው "ውይይ በእናትሽ በቃ ረፍዶብኛል ተይ ግን አላሳዝንሽም?" ብሎ ሲያቅተው እጅ ሰጠ ሊዱዬም ድክም ስላላት ሳቋን ገታ ለማድረግ እየሞከረች ". . . .እህህ. . ኡፍፍ እሺ በቃ አባ ና ልሰርልህ" ብላ ሁሌ እንደምታደርገው በደንብ አድርጋ ማሰር ጀመረች በመሀል ግን የከረባቱን ጯፍ አዛዙራ አየችው አባዬም ግርም ብሎት "ምነው ቆሽሿል እንዴ?" ሲላት አይኖቿን ግር በሚያሰኝ ሁኔታ ዝቅዝቅ አድርጋቸው ". . .አይ አልቆሸሸም አባ ግን ይሄን ከረባትህን ከሁሉም አብልጬ ነው የምወደው አንተ ደሞ ሁሌ ስታደርገው እያለቀ ስለሚመስለኝ ከፍቶኝ ነው" አለችው ይሄ የሁልጊዜው የቡቻዬ ማሳሰቢያ ነው አባዬ ግን ይበልጥ እሷ ስለምትወደው ከሚያስቀምጠው ይልቅ ቢያጠልቀው ለሱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ያስባል ይህን ጊዜ ሁላችንም በአባዬ እየተናደድን እማ "ኑ ኑ! በቃ ቁርስ እንብላ እኔም ስራ ቶሎ ነው የምገባው" አለችን እኛም እሺ ብለን ወደ ማዕዱ ቀረብን ሶሲ እየተቻኮለች መጣችና ልክ ስታየን "እንዴ!! እናንተ እዚህ ምን ታደርጋላችሁ? ምን መሆናችሁ ነው?" አለችን እኔና ሊዱም እየተያየን "በቃ አበደች" ብለን "እህ ታድያ ስታዲየም ሄደን አንሮጥ ከቤታችን የት እንሂድ" ብዬ ግራ ያጋባኝን ጥያቄዋን በሹፈት መለስኩላት ለካስ ነገሩ ስር የሰደደ ሆኗል ኮስተር ብላ "እንዴ ዛሬ አይደል እንዴ 'ወንጌልን ለአለም' መርሀ ግብር የሚጀምረው ደሞስ አንደኛ ተመዝጋቢዎች ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ባለፈ ምክትሎች እነማን ሆኑና?"" አለችን ይህን ጊዜ እማና አባ የያዙትን ማዕድ ቆም አደረጉና በጥያቄ አይን የእኛን መልስ መጠባበቅ ጀመሩ የሚገርመው ነገር ግን አመቱን ሙሉ በጉጉት ስንጠብቀው የነበረ እውነትም ዋና ተመዝጋቢዎች ከመዝጋቢነት አልፎ ቀናትን ከቀናት ደረሰ አልደረሰ እኔ ነኝ እኔ እያሉ ለማስተባበር የሚሯሯጡ እንዳልነበርን ዛሬ ይህን ሳውቅ ከመኖርም ከመድረሱም ቅንጣት መቁጠር ተሳነኝ ልቤን ምንም አልሰማ ሲለኝ ሳላስበው "እ ባክሽ እኛ አይመቸንም" ብዬ ወደ ምግቤ መለስ አልኩ ይህን ጊዜ ሊዱ በጣም ደንግጣ በእግሯ ረገጥ አደረገችኝ ያለችው ቢገባኝም በራሴ አለም ታውሬ እሷንም "ኸረ ተይኝ!" ብዬ አጉረመረምኩባት አሁንም አላቆመች ይባስ በሀይል ተጫነችኝ ንዴቴን መቆጣጠር ሲያቅተኝ በእልህ ተሞልቼ ቀና ስል አባዬና እማ ዱላ ቀረሽ አስተያየት ላይ ናቸው ከስር ከስር ሶሲ በቁጣ ታጋግላቸዋለች አባዬ ፊቱ በአንዴው መለዋወጥ ጀመረ የያዘውን ሹካ በሀይል በጠረጴዛው ላይ "ጓ!!!" አድርጎ ከወንበሩ ብድግ አለ...
. . .ይቀጥላል. . .
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
933 views@Maranata, edited  16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:33:05
#የማለዳ_ቃል

"እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ፤ ከተስፋዬም አልፈር፥ እርዳኝ እድናለሁም፥ ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ።"
-መዝሙረ ዳዊት 119:116-117

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.2K viewsMeron, edited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ