Get Mystery Box with random crypto!

CHRIST TUBE - ETH🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹 C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christ_tube — CHRIST TUBE - ETH🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @christ_tube
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.14K
የሰርጥ መግለጫ

"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-02 09:18:39
ሠብረህ/ሽ ግባ/ቢ
ስምዖን ተከፍቶ ተቀምጦ ይሁዳ።
የገንዘቡን መጠን፣ተመን ሲያወጣ፤
የከበረ እንቁውን በመዳብ ለውጦት
በመጨረሻው በ 30 ብር ሲሞት

እሷ ግን......
የገባት ገብቷቷል_
#ሠብራ_የገባች_ተሰብሮላት_ወጣች

የሰው እምነት ንዋይ ነው።
የሷ እምነት እየሱስ ነው።
የሁለት አለም ሰዎች።

~ ~ተሠርዮል | | (ሻል)~ ~(ሃል) ።
ከዚህ በኅላ ውርደት የለም።
የእግዚአብሔር ልጅ~| | ~ነፃ አውጥቶናል።

እብድም ልባል መንገዱ አንድ ነው
ብሎ ስላመነ ተሳካለት ሄኖክ።
አልሞተም አለ የዕምነቱን ወረሠ።
እያዩት ሄደ

ኖህ መቶ ሃያ ዓመት መርከብ ሲሰራ
ሲያበጃጅ ቆይቶ
አልፎ ሄደ ከሞት ከሚጠፉት ተርፎ

ዝናቡ የኖህን መርከብ ሲያነሳ
በክብር ከፍ ፣ ከፍ ፣
በሞገስ ከፍ ፣ ከፍ፣
እያረገ ሲሄድ....
ለግፈኞች መጥፍያ መቀበርያ ሆነ።

የሀና አምላክ ቢዘገይም አይቀርም።
ምልልስሽን አታቋርጪ፥
መምጣቱ አይቀርም፣

የነ ፍናና ማሽሟጠጥ
ሚያበቃበት ቀን አለ።
እነ ኤሊ ምላሳቸው~ሌላም ሌላ ይሁን፦
~ ~ | | ከኪዳንህ ቀድሞ | | ~ ~ | |

የሠዎች አንደበት አይስበር ልብህን
አምላካችን ግን በጊዜው.....
ከፍ ያደርግሃል፣ቀና ያደርግሃል

መልካም እሁድ
@CHRIST_TUBE
@CHRIST_FAMILY

#ተፃፈ_በአና_ንጉሴ(ንሻ)
1.7K viewsAna, edited  06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 07:24:25
#የማለዳ_ቃል

" በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።"
-መጽሐፈ ምሳሌ 27: 18

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.5K viewsMeron, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 19:59:18 ምዕራፋችንን እንዲህ አድርገው አስጀመሩን: ከብዙ መዝለልና መጮህ መደሰት በኋላ ሁላችንም ሙቀቱ አፍኖን እያለከለክን በስሶቹ ፍራሽ ላይ ቁጭ አልን በቤት ውስጥ ያለው ድባብ ፍፁም ወደ ቀድሞው ተመልሷል ከልደቱ ሙዚቃ በኋላ በወቅቱ ወጣ ያለ ተብሎ የሚታወቅ ዘፈን ሞቅ ባለ ድምፅ ተከፈተ ሊያና ሳሮን ከተቀመጡበት ተነስተው በሳጥን የታሸገ መጠጥ አመጡ ይባስ እነ ኬብሮንም የተለመደውን ጫትና ለመቃም የሚያስፈልጋቸውን የለስላሳ አይነት ይዘው ብቅ አሉ ከወትሮው ለየት ብሎ ግን ሳየው ምንም አይነት ስሜት አልተሰማኝ ከራሴ ጋር ያነታርከኝ የነበረው ያ ትግልም ዝምታን ምላሽ አደረገልኝ አንድ ድምፅ ግን በተደጋጋሚ ወደ ልቤ ይመጣል እኔ ግን ምርጫዬ ያደረኩት ቆም ብዬ አዕምሮዬን ከፍቼ ማዳመጥ ሳይሆን የጓደኞቼን አይን መቃኘትን ነበር ናሆሜ ከሱራፌል ጋር በወሬ የተጠመደ ለማስመሰል ይጥራል ሊደዬም አብራቸው መጫወቱን ተያይዛዋለች ቢኒ ግን አይኖቹን ከታሸገው ጠርሙስ ላይ ተክሎ በሀሳብ ተውጧል የዘፈኑ ጫጫታ የተሰበሰቡት ልጆች ሳቅ ሁኔታውና ድባቡ በሙሉ ከራስ ጋር ለማውራት ፋታን አይሰጥም ሊያም መጠጡን ለሁላችንም ቀዳች ሁሉም እየተነሱ በቀዳችላቸው ላይ ካልጨመርሽ ብለው እየተሻሙ የመጠጡን ብርጭቆ አጥብቀው ያዙ አይን አይናቸውን እያየን ሳለ ሳሮን በትሪ ላይ አራት በትንሹ የተቀዱ ይዛልን መጣች በፈገግታ ተሞልታ እንድንይዝ ወደኛ ሰደድ አደረገችው ሁሉም ዞረው ያዩን ጀመር እኛም በእፍረት እየተያየን ሊያ አንድ ሀይል ባለው ቃል "እንዴ!! ጓደኞች ያዙ እንጂ ባለፈው የጠጣነው እኮ ነው ትወዱታላችሁ!!" አለችን ወዲያው አዕምሮዬ "አየሽ አንዴ ገብተሽበታል እኮ!" ብሎ አሾፈብኝ በእፍረት ተሞልቼ ልቤን ላናግረው ስል ". .አይ በቃ አሁንማ ሌላ ሰው ነሽ" ብሎ ፊት ነሳኝ በዚህ ሁላ ግን ወደ ውስጤ የሚመላለሰው ድምፅ መጮሁን እኔን ለመመለስ መታገሉን አልተወም ከራሳችን ጋር ብዙ ብንታገልም ደስታ የተሞላ ፍቅር ብለን ያሰብነውን ምዕራፍ ጀመርን በእጆቻችን ያጠበቅነውን መጠጥ ለመጨለጥ እየተስገበገብን ጀብድ እንሰራ ይመስል በፉጨትና በጩኸት ታጅበን ለሳሮን በአንድ ድምፅ መልካም ልደትን ተመኝተንላት ፋሽንና የዘመኑ ነገር Normal ብለን ያሰብነውን አለም ተዘፈቅንበት!! ከዚህ ቀን ወዲህ ነው እኛነታችን የተቀበረው የጠጣነውን ስንጨርስ ሌላ ለመጨመር ተክለፈለፍን በስተመጨረሻ እኛ ልክ እንደ ሆንን አምነን ልባችንን ከአዕምሯችን ጋር ሸምግለን አስማማነው ቀናት ቀናትን እየወለዱ እኛም አዲሱ ህይወታችንን እየተላመድነው የሙሉ ቀን ውሏችን ከዚህ ቤት መሆኑን ቀጠለ ከራሳችን ጋር ተላልፈን ሌላ የማናውቀው አለም ውስጥ ዘቀጥን ለወትሮው ሀሳባችን፣ መንገዳችን፣ እያንዳንዱ እርምጃችን፣ ከናፍሮቻችን *ከጌታ ጋር በጌታ ቤት ለጌታ ክብር እንዳልነበር አሁን ለጓደኝነት፣ ለጊዜያዊ ነፃነት፣ ለዘመኑ ፋሽን ሆነ በቀናት ላይ ቀናት በተጨመሩ ቁጥር ከቤት አታለን እየወጣን ከመጠጣት አልፎ ወደ መቃም ከመቃም ብሶ ወደ ማጨስ ገባን
...ይቀጥላል...
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
ቻናሉን ይቀላቀሉ
➥ @CHRIST_TUBE
➥ @CHRIST_TUBE
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!
1.6K views@Maranata, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 19:59:18 ከራስ ጋር ትግል
ተከታታይ ልብወለድ
ምዕራፍ=ሁለት
ክፍል=47
ሳባ ካሳሁን

እኛም እየተቻኮልን ሰው አየኝ አላየኝ ከአሁን አሁን ጠሩን አልጠሩን ልቤ ምንድነው የሚጨቀጭቀኝ? ይህ ሰው ለምንድነው እንዲህ የሚያየኝ? እያልን ሰላምን ፍለጋ ሰላም አጥተን ወደዚያ ቦታ ደረስን ሁላችንም ለመግባት ተስገብግበን ከመጣደፍ ብዛት ለጉድ እያለከለክን በሩ ላይ ቆመን ቀረን የመቀርቀሪያውን አከፋፈት ቀድመው ስላሳዩን እኛ አይኖቻችንን እያማተርን ሰው ስንቃኝለት ናሆሜ ቀስ ብሎ ከፈተው። ሁላችንም ተያይዘን ወደ ውስጥ ገባን ልክ ሲገባበት ቤቱ ጭር ያለ ቢመስልም ከመጋረጃው ጀርባ ያለው ድባብ ያለው መጯጯህ ከልብ የሆነ ሳቅ ስሜትን ያጋባል ሊዱ ዬ ልክ እንደ ቤታችን ሆና መጋረጃውን ገለጥ ስታደርገው እነዚያ ከልብ የማይጠፉት ልጆች ክብ ሰርተው ተቀምጠው ፊታቸው በእምባ እርሷል ሆኖ የማያውቀውን ሊያና ኬብሮን የእንባቸው መውረድ አልቆም ብሏቸው ዞር ብለው ፊታቸውን ሲያሻሹ አስተዋልናቸው ሁኔታው ያልገባን እኛ በድንጋጤ እርስ በእርሳችን እየተያየን ሳለ ኬብሮኔ ከተቀመጠበት ብድግ አለና ፊቱን የቀያየረውን እንባ እየጠራረገ ""...ውይይ ጓደኞች መጣችሁ እንዴ? ኑ ኑ አረፍ በሉ" ብሎ ቦታውን ያጣበቡትን ትራሶች ገለል አድርጎ እንድንቀመጥ ጋበዘን ግራ መጋባታችን ቀጥሏል ምን እየተፈጠረ እንዳለ ምን እንደሆኑ ሳናውቀው አይናችን እያንከራተትን ባሳየን ቦታ ከአንድ የጠይም ቆንጆ በእኛ እድሜ ካለች ሴት እና በሊያ መካከል ዘርጋ ብለን ተቀመጥን ከሁሉም ይልቅ ይህች ልጅ አጥብቃ ማልቀሷን ልታቆም አልቻለችም የእኛ መወዛገብ ቀጥሏል ልክ ምግብ ሊሰጣት ለመብላት እንዳኮበኮበች ድመት አይናችንን እያቁለጨለጭን ስናያቸው ሁሉም አብራን የተቀመጠችውን ልጅ ከልባቸው ስሜታቸውን አውጥተው ዝም እንድትል ያፅናኗታል ነገሩን መያዝ ያቃተው ቢኒ ድምፁን ለስ አድርጎ ". .እ ጓደኞች ምን ሆናችሁ ነው ችግር አለ እንዴ?" አላቸው ይህን ጊዜ ሁሉም ከትካዜያቸው ነቃ አሉና አንድ በተፈጥሮው ሲያወራ የሚኮላተፍ ሱራፌል የሚባል ልጅ ደስ በሚል ድምፁ "አይ ዛሌ የሳሮን ልደት ነው እና ግን ቤተሰቦቿ አብለዋት ሊሆኑ አልቻሉም" እያለ ከአይን ሊጠፋ በማይችል አስተያየት አይቶን ትክዝ አለ እኛ መጠየቃችንን ልናቆም አልቻልንም በውስጣችን "ሞተው ይሆን እንዴ? አዎ በቃ እንደሱ ነው። እንጠይቃቸው እንዴ? አይ ይሄ ደግሞ ምን ተብሎ ይጠየቃል?" እያልን ስናጉረመርም ናሆሜ ". .እ ማለት አልገባኝም" ብሎ ነገሩን አፈረጠው ተራው የሊያ ነበር ሊያም በዚያ የቀበጥ ድምጿ ኳስ በሚመስሉት ቡኒ አይኖቿ እያየችን "እይላችሁ ጓደኞች ሳሪና ለረጅም ጊዜ የምናውቃት ጓደኛችን ናት እናትና አባቷ ጥለዋት ከጠፉ አመታትን አስቆጥረዋል አሁን ላይ የት እንዳሉ ይኑሩ ወይ ይሙቱ ማንም የሚያውቀው ነገር የለም. .እ. . አሁን ሳሪ ይሄ ትዝ ብሏት ነው የማይሆን ሙድ ውስጥ የገባነው" አለችን ቢኒና ናሆሜ ድንግጥ ብለው እኔን አዩኝ ስንሰማ ቶሎ ያሰብነው ስለ ሊዱ ነበር እጅግ ለሰው አሳቢዋ ከራሷ በላይ እኛን የምታስቀድመው ፍቅርን ያስተማረችን ያች ቡቻዬ በስሷ ፍራሽ ላይ ከእኔ ስር የሸሚዜን ጫፍ እንቅ አድርጋ ሽጉጥ ብላብኝ እጆቼ በእምባዋ ሲረጥቡ ተሰማኝ ወዲያው ልቤ በሀይል መታ ስፈራው የነበረው ነገር ደርሶ ስሜቷ ተነካ ሳሮን በእምባ እንደተለሞላች ታሪኳን ታጫውተን ጀመር ልደቷን እንዴት በደስታ ታከብር እንደነበር ምንም በማታውቀው ነገር ጭለማ ውስጥ ብቻዋን ጥለዋት እንደጠፉ ጭምር እያንዳንዱ ያሳለፈችውን ነገር ስታወራልን ሁላችንም ስሜታችንን መቆጣጠር አቃተን በሳሮን ውስጥ ሊዱን እያሰብኩ ይባስ አለቀስኩ ታሪኳ እጅግ ልብ ሰባሪ ነበር ሊዱ ድምፅ ሳታሰማ ሸሚዜን በጥርሶቿ ንክስ አድርጋ ስቅስቅ ብላ ማልቀሷን ልታቆም አልቻለችም ይህን ጊዜ እነ ሊያ ሁኔታችንን ሲያስተውሉ አጠገባችን መጥተው በጨዋታ ላይ ቡድኖች ሲመካከሩ እንደሚተቃቀፉት ሁላችንም ክብ ሰርተን ተቃቀፍንና ኬብሮኔ ከልብ በማይጠፋ ንግግር በትልቅ ድምፅ "ጓደኞቼ!! እኛ ቤተሰብ የለን ይሆናል ምድር ላይም እኛን ብሎ የሚፈልገን ዘመድ ላይኖር ይችላል ነገር ግን እኛ ዕርስበዕርሳችን አንዳችን ለአንዳችን ሀይል ነን እኛነታችን ለሌላችን አቅም ነን እዚህ ቤት ውስጥ ያለን ሁላችንም አንድ ነን!" ብሎ ልባችንን ጠገነልን ፊታችንን የሞላውን የትካዜና የሀዘን እምባ በአንድ ንግግር አበሰልን ይህን ጊዜ ሁላችንም በፈገግታ ተሞላን ከልባችን ደስ አለን ሁላችንም እየተነሳን የምስራች እንደሰማ ሰው ተቃቀፍን ሊዱዬና ሳሮንም ወደ ደስታ ተመለሱ ሊያ ፊት ለፊታችን ለተቀመጠው የሙዚቃ ማጫወቻ ድምፅ እየጨመረች "አዎ በቃ የምን መተከዝ ነው!! ሊዱ! ሳሪና! በቃ እንዲህ ስትስቁ ነው የሚያምርባችሁ ሳሪ ደሞ ዛሬ ልደትሽ መሆኑን አትርሺው!" ብላ በከፈተችው የልደት ሙዚቃ ቡቻዬንና ሳሮንን እጃቸውን ይዛ አስጨፈረቻቸው ሁሉም ተነስተው መደሰት ጀመሩ እንቅስቃሴያቸው ከልብ ያስቅ ነበር እኛ ስናጨበጭብላቸው እነሱ ሲሯሯጡ ደስ የሚል እብደት ውስጥ ገባን የሚገርመው ነገር ግን ሁሉም ትኩረታቸው በሊዱ ላይ ነው በወሬ መሀል ቀና ብዬ ሳያቸው ሊዱን ከበዋት እሷን ለማሳቅ ብዙ ይሞክራሉ ትንሽ ግራ አጋባኝ
*ሳሮንን ቢሆን እሺ ግን ለምን ሊዱን?
ብዬ ወዲያው ደሞ "አይ ምን ነካኝ ሊዱዬ እኮ የምትወደድ ልጅ ናት በቃ የዋህነቷ አስደስቷቸው እነሱም ሊያስደስቷት ፈልገው ነው" ብዬ ወደ ወሬዬ መለስ እላለሁ ከዚህ ቀን ጀምሮ ውሏችን እንዲህ መሆን ጀምሯል ጊዜው ቢሄድም አመላቸው ነውና የለመዱትን ዕፅ መውሰድ አለባቸው!
1.4K views@Maranata, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 09:10:39 እወድሃለሁ ጌታዬ
ፓስተር ተከስተ ጌትነት
ለኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
sʜᴀʀᴇ ◈ JOIN ◈ sʜᴀʀᴇ
◈ @CHRISTFAMILY ◈
▷ @CHRIST_TUBE ◁
△ Join Us △
1.5K viewsMeron, 06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 07:49:00
#የማለዳ_ቃል

" አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል፤"
-መዝሙረ ዳዊት 103: 13

መልካም ቀን!

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.5K viewsMeron, edited  04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 22:43:52 Live stream finished (43 minutes)
19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 22:00:18 Live stream started
19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 21:58:36 LIVE STREAM የሚደረገው የፀሎት ፕሮግራም አሁን ከ 4:00pm ጀምሮ ወደ እናንተ ይደርሳል ኑና በእግዚአብሔር ፊት እንውደቅ።
1.6K viewsAna, 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 21:55:35 ቀን 23/10/2015
የፀሎት መርሃ ግብር

በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”
— ኤፌሶን 6፥18


ኑ በእግዚአብሔር ፊት እንፀልይ
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY
1.6K viewsAna, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ